Author Archives: Central

ተመድ በኢትዮጵያ የተፈጸመውን ግድያ የማጣራት ጥያቄ የልማት ኣጋሮች እንዲደግፉት ሂውማን ራይትስ ዎች ጠየቀ

ኢሳት (ነሃሴ 12 ፥ 2008) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ የተፈጸሙ ግድያዎች በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ያቀረበውን ጥሪ የሃገሪቱ የልማት አጋሮች እንዲደግፉት ሂውማን ራይትስ ዎች ጠየቀ። የሃገሪቱ የልማት አጋሮች የድርሻቸውን ተጽዕኖ ማሳደር ይኖርባቸው ሲል የገለጸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ድርጊቱ መንግስት ያለተጠያቂነት ሰላማዊ ሰልፈኞችን መግደል እንደማይችል ጠንካራ መልዕክትን የሚያስተላልፍ ነው ሲሉ አስታውቋል። የልማት አጋሮች የሚወስዱት እርምጃ ለመንግስት ከሚያስተላልፈው መልዕክት ...

Read More »

ኢትዮጵያ በቢጫ ወባ በሽታ ስርጭት ሰለባ ልትሆን እንደምትችል ተነገረ

ኢሳት (ነሃሴ 12 ፥ 2008) ኢትዮጵያን ጨምሮ የወባ በሽታ ተጋላጭ የሆኑ የአፍሪካ ሃገራት በአንጎላና ዴሞክራቲክ ሪፕሊክ ኮንጎ እየተስፋፋ ባለው የቢጫ ወባ በሽታ ስርጭት ሰለባ ሊሆኑ እንደሚችሉ የአለም ጤና ድርጅት ረቡዕ አሳሰበ። ካለፈው ወር ጀምሮ በሁለቱ ሃገራት ከ400 በላይ ሰዎች በበሽታው ስርጭት የሞቱ ሲሆን፣ ከስድስት ሺ የሚበልጡ ተጨማሪ ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን ሲ ኤን ኤን የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል። በወባ ትንኝ አማካኝነት የሚተላለፈው ...

Read More »

የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በመጪው ቅዳሜ ነጭ ልብስ በመልበስ በህወሃት/ኢህአዴግ የተገደሉትን ሰዎች እንደሚያስቡ አስታወቁ

ኢሳት (ነሃሴ 12 ፥ 2008) በተለያዩ የተቃውሞ ስልቶች ውስጥ የቆዩ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ከፊታችን ቅዳሜ ነሃሴ 14, 2008 ዓም ጀምሮ “ነጭ በመልበስ” እና በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተገደሉ ሰዎችን ለማሰብ አዲስ መርሃግብር መንደፋቸውን ሃሙስ አስታወቁ። ጥቁር በመልበስና ከቤት ባለመውጣት አድማ ውስጥ የቆዩት ነዋሪዎቹ ሙሉ በሙሉ ነጭ የመልበሱ ስነ-ስርዓት የቀድሞ ጠቃላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን የመታሰቢያ ዝጅግት በሚያካሄዱበት ቀን በተቀራኒ አለባበስ ተቃውሞን ለማንጸባረቅ ...

Read More »

በጎንደር አምባ ጊዮርጊስ ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ ጊዜ የታሰሩ 14 ሰዎችን አስለቀቁ

ኢሳት (ነሃሴ 12 ፥ 2008) በሰሜን ጎንደር ዞን ስር አምባ ጊዮርጊስ ከተማ የሚኖሩ ነዋሪዎች ሃሙስ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ በቅርቡ ለእስር የተዳረጉ 14 ነዋሪዎችን በከተማዋ ከሚገኝ እስር ቤት በሃይል ማስለቀቃቸውን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ። የከተማዋ ነዋሪዎች ሰኞ የመንግስት ባለስልጣናት ተገኘተው ያላቸው ጥያቄ እንዲሰሙ ያቀረቡትን ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ ምክንያት በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ሃሙስ ተቃውሞን ሲገልጹ መዋሉን ለመረዳት ተችሏል። ነዋሪዎቹ ሰኞ ለከተማው አስተዳደር ...

Read More »

የአምባጊዮርጊስ ከተማ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ነሃሴ  ፲፪ ( አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ አምባጊዮርጊስ ከተማ የሚኖሩ ነዋሪዎች ዛሬ ነሃሴ 12፣ 2008 ዓም ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ አርፍደዋል። በከተማዋም ሆነ በአካባቢው ምንም አይነት የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ያልነበረ ሲሆን፣ በአካባቢው የተሰማሩ ፖሊሶችም አንዳንድ ወጣቶችን ከመደብደባቸው በስተቀር ምንም እርምጃ አልወሰዱም። ህዝቡ “ወያኔ አይገዛንም፣ 25 አመታት የተቀለደብን ይበቃል፣ በቃን!” የሚሉና ሌሎችም ...

Read More »

ኢህአዴግ አባላቱንና የመንግስት ሰራተኞችን ስብሰባ እየጠራ ስርዓቱን ከመናድ ታደጉት እያለ ነው

ነሃሴ  ፲፪ ( አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ በተለያዩ ደረጃዎች ያሉ የመንግስት ሠራተኞችን በወቅታዊ  የጸጥታ ጉዳይ ዙሪያ እያነጋገረ ቢሆንም፣ የመንግሥት ሰራተኛው ድጋፍ ሊሰጠው አለመቻሉን ከያቅጣጫው የሚደርሱን ሪፖርቶች ያሳያሉ። በውይይት ወቅት የኢህአዴግ አባል ያልሆኑ ሠራተኞች በሁሉም የውይይት መድረኮች ላይ በአብዛኛው አስተያዬትና ሃሳብ ከመስጠት ዝምታን መርጠዋል። የኢህአዴግ አባሎች በስብሰባዎች ላይ “ህዝቡ እኛን  አድምጦ መልስ ከመመለስ ይልቅ ‘እናንተ ለህዝቡ ...

Read More »

በአውስትራሊያና ደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዜጎች ላይ እየደረሱ ያሉ ጭፍጨፋዎችን አወገዙ

ነሃሴ  ፲፪ ( አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በውስትራሊያ ሜልበርን ከተማ የተካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ ወንድማገኝ ጌታነህ ከስፍራው አዘጋጅቶታል። በደቡብ አፍሪካም እንዲሁ ከ97 በሁዋላ ያልታዬ የኢትዮጵያን ህዝብ በጋራ ያሳተፈ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። በስፍራው የተገኙ የተለያዩ ኢትዮጵያውያንን ስለሰልፉ አነጋግረናቸዋል ።

Read More »

በተለያዩ ከተሞች የኮሌራ በሽታ ተከስቶ እንደሚገኝ ተነገረ

ኢሳት (ነሃሴ 11 ፥ 2008) በአዲስ አበባ ከተማ በመሰራጨት ላይ ያለው የኮሌራ በሽታ በመቀሌ ከተማም መከሰቱን የክልሉ ጤና ቢሮ ረቡዕ አስታወቀ። በከተማዋ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች ተከስቷል በተባለው በዚሁ በሽታ አምስት ሰዎች ምልክቱ ተገኝቶባቸው በህክምና ላይ መሆናቸውን የጤና ባለሙያዎች ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። በሰኔ ወር በአዲስ አበባ ከተማ ስርጭቱን የጀመረው ይኸው የኮሌራ በሽታ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ጉዳትን ...

Read More »

በጎንደር ከተማ የፀሎትና የሻማ ማብራት ስነስርዓት በጸጥታ ሃይሎች ተስተጓጎለ

ኢሳት (ነሃሴ 11 ፥ 2008) ሰሞኑን በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተገደሉ ሰዎችን ለማሰብ ረቡዕ ምሽት በጎንደር ከተማ ሊካሄድ የነበረውን ልዩ የፀሎትና የሻማ ማብራት ስነስርዓት ከጸጥታ ሃይሎች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት መስተጓጎሉን ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ። ላለፉት ሶስት ቀናት ከቤት ባለመውጣት አድማ ውስጥ የቆዩት የከተማዋ ነዋሪዎች ዝግጅቱን ለመታደም ወደ አደባባይ ቢወጡም ከጸጥታ ሃይሎች ጋር አለመግባባት መፈጠሩን እማኞች አስረድተዋል። በከተማዋ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የፌዴራል ፖሊስ ...

Read More »

በደብረማርቆስ የተጀመረው አድማ ረቡዕ እንደቀጠለ ነው

ኢሳት (ነሃሴ 11 ፥ 2008) ማክሰኞች ከሰዓት በኋላ በደብረ ማርቆስ ከተማ የተጀመረው የሰራ ማቆም አድማ ረቡዕ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉንና ነዋሪው የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የሃይል እርምጃ እንዲያበቃ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ። የከተማዋ ነዋሪ ያነሱት ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ ምክንያት ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ መጀመራቸው ይታወሳል። ተቃውሞ ረቡዕ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉን የተናገሩት እማኞች በከተማዋ የሚገኙ ሁሉም የግል ...

Read More »