ኢሳት (መስከረም 10 ፥ 2009) ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በአባይ ግድብ ግንባታ ላይ ይግባኝ የማይኖረው ጥናት እንዲጀመር ማክሰኞ በሱዳን መዲና ካርቱም የመጨረሻ ስምምነት ደረሱ። ሁለት የፈረንሳይ ኩባንያዎች በቀጣዮቹ 11 ወራቶች ግድቡ በታችኛው ተፋሰስ ሃገራት ላይ የሚያመጣውን ተፅዕኖ በማጥናት ሪፖርታቸውን ለሶስቱ ሃገራት ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። አርቴሊያና BRL የተሰኙት ኩባንያዎች የሚያካሄዱ ጥናት ይግባኝ የማይኖረው ሲሆን፣ ሃገሮቹ ለጥናቱ ውጤት ተገዢ እንደሚሆኑ በተደረሰው ስምምነት መጠቀሱን ...
Read More »Author Archives: Central
በጎንደር እና ባህርዳር የሚካሄደው የስራ ማቆም አድማ ለሁለተኛ ቀን ሲቀጥል በአዲስ ዘመን ደግሞ አድማውን በአጋዚ ወታደሮች ለማስቆም ሙከራ እየተደረገ ነው
መስከረም ፲ (አሥር) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጎንደርና ባህርዳር ከተሞች የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ በከፍተኛ ደረጃ ተጠናክሮ እየቀጠለ ቢሆንም፣ አገዛዙ አድማው እንዲቆም የተለያዩ እርምጃዎን መውሰድ ጀምሯል። ነጋዴዎች እየታሰሩ፣ የንግድ ድርጅቶች እየታሸጉ እንዲሁም ከስራቸው የቀሩ የመንግስት ሰራተኞች እየተመዘገቡ ደሞዛቸው እንደሚቆረጥና ከስራ እንደሚባረሩ ማስጠንቀቂያ እየተጻፈላቸው ነው። በአዲስ ዘመን ደግሞ በሁለተኛው የተቃውሞ ቀን በርካታ የአጋዚ ወታደሮች ወደ ከተማው ገብተው በጉልበት ነጋዴዎች ...
Read More »ከ1 ሺ 500 በላይ ወጣቶች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ጫካ ውስጥ ታስረው ስቃይ እየደረሰባቸው ነው ተባለ
መስከረም ፲ (አሥር) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል የተካሄዱ ህዝባዊ ንቅናቄዎችን ተከትሎ ከታሰሩት ከ1 ሺ700 እስከ 2 ሺ የሚደረሱ ወጣቶች ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ታስረው ቀኑን ሙሉ ድንጋይ በመፍለጥ እየተቀጡ መሆኑን፣ ብዙዎች በበሽታ፣ በርሃብ እና በህመም ህይወታቸው እያለፈ መሆኑን፣ በእስር ቤቱ ታስሮ ያመለጠ አንድ የቀድሞ ወታደር ለኢሳት ገልጿል። በጠባቂ ጓደኞቹ ድጋፍ ያመለጠው ይህ የቀድሞ ...
Read More »በአውስትራልያ ኩዊንስ ላንድ ግዛት ብሪዝቤን ከተማ ዛሬ በህወሃት መራሹ መንግስት ሂወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያውያንን የማሰብና ለሌሎችም ወገኖቻቸው አጋርነትን የመገልጸ ስነስርዓት ተከናወነ።
መስከረም ፲ (አሥር) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኩዊንስ ላንድ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ባዘጋጀው በዚህ ዝግጅት ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን የታደሙ ሲሆን የደብረ ጸሃይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ካህንና አስተዳዳሪ ቄስ መንግስቱ ሃይሉ በዝግጅቱ ላይ በመገኘት ቡራኬና ትምህርት የሰጡ ሲሆን ለዕለቱ የተዘጋጀውንም ሻማ ለኩሰዋል። ልዩነቶቻችንን አቻችለን በጋራ በመቆም ሃገራችንንና ወገኖቻችንን መታደግ ይገባል ሲሉ ያሳሰቡት ቄስ መንግስቱ በህብረትና በጋራ መቆም ግዜው የሚጠይቀው ...
Read More »አትሌት ፈይሳ ሌሊሳና ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የአመቱ የኢሳት ምርጥ ሰዎች ተብለው ተመረጡ
ኢሳት (መስከረም 10 ፥ 2009) አትሌት ፈይሳ ለሊሳና ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የኢሳት የአመቱ ምርጥ ሰው በሚል ተመረጡ። የ2008 የአመቱ ምርጥ ሰው በሚል በአንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ስም የተሰየመውን ሽልማትም በተወካዮቻቸው አማካኝነት ተቀብለዋል። የኢሳት የአዲስ አመት ዝግጅት ባለፈው ዕሁድ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ በተካሄደበት የሽልማት ስነስርዓት የሃይማኖት አባቶች መንፈሳዊና ሃገራዊ መልዕክት አስተላልፈዋል። ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች ...
Read More »በጎንደርና ባህርዳር ከተሞች ለ6 ቀናት የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ ተጀመረ
ኢሳት (መስከረም 9 ፥ 2009) የጎንደርና ባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች ለሶስተኛ ጊዜ ለስድስት ቀን የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ ሰኞ ጀመሩ። የስራ ማቆም አድማ መጀመሩን ተከትሎ በሁለቱ ከተሞች የሚገኙ አብዛኛቹ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ስራ ማቆማቸውንና አድማው ነዋሪው ያለውን ተቃውሞ በተከታታይ ለማሳየት ያለመ መሆኑን ነዋሪዎች ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስረድተዋል። በባህርዳር ከተማ ሰፍረው የሚገኙ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በቀበሌ 11 እና 13 አገልግሎት መስጫ ...
Read More »በኢትዮጵያ በመፈጸም ላይ ያለውን አፈና በመቃወም በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ
ኢሳት (መስከረም 9 ፥ 2009) ነዋሪነታቸው በዚህ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማና የተለያዩ ግዛቶች የሆኑ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ መንግስት በመፈጸም ላይ ያሉ ግድያዎችንና አፈናዎችን በአስቸኳይ እንዲቆም በመጠየቅ ሰኞ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ። ከመቼውን ጊዜ በላይ በቁጥር ልቀው የታዩት ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የአሜሪካ መንግስት ተደጋጋሚ ስጋትን ከመግለጽ ያለፈ ጠንከራ እርምጃ እንዲወስድ ሲያሳስቡ አርፍደዋል። የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በተካሄደበት ወቅት ...
Read More »የህወሃት ወታደራዊ አመራሮች ለወርቅ ልማት በቤኒሻንጉል መስፈራቸው ተገለጸ
ኢሳት (መስከረም 9 ፥ 2009) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጊዛን ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ወደ አንድ ሺ የሚጠጉ የህወሃት ወታደራዊ አመራሮችና አባላት በአካባቢው ለወርቅ ልማት በሚል መስፍራቸው በነዋሪዎች ዘንድ ተቃውሞ መቀስቀሱ ተገለጸ። ጉዳዩን በመከታተል ላይ የሚገኘው የቤኒሻንጉል ህዝቦች የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም በጊዛን የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ወደ 300 አካባቢ የሚጠጉ ሰዎች ወደ አሶሳ እስር ቤት መወሰዳቸውን ለኢሳት አስታውቋል። የድርጅቱ ሃላፊ የሆኑት አቶ ...
Read More »በታንዛኒያ አንድ የኦማን ዜጋ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ ሁከት ፈጥሮ በረራ አስተጓጎለ
ኢሳት (መስከረም 9 ፥ 2009) ከታንዛኒያ ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ በዝግጅት ላይ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መንገደኞች አውሮፕላን በአንድ የአማን ዜጋ ተሳፋሪ ሁከት ተፈጥሮበት በረራው መስተጓጎሉን የታንዛኒያ የጸጥታ ሃይሎች ሰኞ አስታወቁ። በርካታ መገደኞች አሳፍሮ ወደ አዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ ሊያቀና የነበረው የመንገደኞች አውሮፕላን የአማን ዜጋ ተሳፋሪው እራሱን በመጸዳጃ ቤት በመቆለፍ አልወጣም ብሎ በማስቸገሩ በዳሬ ሰላም አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ከፍተኛ ...
Read More »በኒውዮርክ ሮሽስተር እና ካናዳ ኤድመንተን ለኢሳት የገቢ ማሰባሰብያ ዝግጅት ከ100ሺ ዶላር በላይ ተሰበሰበ
ኢሳት (መስከረም 9 ፥ 2009) ነዋሪነታቸው በዚህ በአሜሪካ ኒውዮርክ ግዛት ሮችስተር እና በካናዳ ኤድመንተን ከተማ የሆነ ኢትዮጵያውያን በሳምንቱ መገባደጃ ቅዳሜና እሁድ ኢሳትን ለመደገፍ ባካሄዱት ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ከ100ሺ ዶላር (ከሁለት ሚሊዮን ብር) በላይ ለገሱ። የኢሳትን ስድስተኛ አመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ በሁለቱ ከተሞች በተካሄደው በዚሁ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በርካታ ኢትዮጵያውያን በመታደም ኢሳትን ለመደገፍ ፈቃደኝነታቸውን እንዳሳዩ የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ለዜና ክፍላችን ...
Read More »