Author Archives: Central

የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ትምህርት ለመጀመር ፈቃደኛ አልሆኑም

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዩኒቨርስቲው ሴነት ተማሪዎች ጥቅምት 7 ትምህርት እንደሚጀምሩ አስታውቆ የነበረ ቢሆንም፣ ተማሪዎቹ ግን አንማርም በማለት ውጭ እንደሚውሉ የገለጸው  ወኪላችን፣ የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ፕ/ር ጨመዳ እና ምክትላቸው ዶ/ር በላይ ተማሪዎችን ሲለምኑ ታይተዋል። በርካታ የታጠቁ ወታደሮች በግቢው ዙሪያ በተጠንቀቅ እርምጃ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውንም ወኪላችን ገልጿል። በሃረር ከተማም ደግሞ ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩ ዲሽ ሲያስነቅሉ መዋላቸው ...

Read More »

ከጋንቤላ ታግተው ከተወሰዱት ሕጻናት የስድሳ ስምንቱ አድራሻ እስካሁን ድረስ  አልታወቀም

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መነሻቸውን ከደቡብ ሱዳን ያደርጉ የሙርሌ ጎሳ አባላት ድንበር ተሻገረው ወደ ኢትዮጵያ በመግባት በጋንቤላ ክልል ውስጥ ጥቃት መሰንዘራቸው ይታወሳል። በወቅቱ የሙርሌ ታጣቂዎች መኖሪያ መንደሮች በእሳት አቃጥለዋል፣ የጅምላ ግያዎችን ጨምሮ ሕጻናትና ታዳጊዎች አግተው ወስደዋል። በወቅቱ ታግተው ከተወሰዱት ሕጻናቶች ውስጥ የተወሰኑት የተመለሱ ቢሆንም እስካሁን ድረስም ያሉበት አድራሻ የማይታ ወቁና ወደ አገራቸው ተመልሰው ከወላጆቻቸው ጋር ...

Read More »

የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ እና የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላልተወሰነ ጊዜያት ተራዘሙ

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአስቸኳይ የጊዜ አዋጁን ተከትሎ የሕዝብ መሰባሰብ ስጋት የፈጠረበት ገዥው ህወሃት ኢህአዴግ  የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ እና የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ  ውድድሮችን ላልተወሰነ ጊዜያት ተራዘመ። በእግር ኳስ ደጋፊዎች መሃከል መንግስትን የሚቃወሙ መፈክሮች ይነሳል የሚል ስጋት ያደረባቸው የኮማንድ ፖስትቱ ባለስልጣናት እጅ እንዳለበት የሚገመተው ትእዛዝን ተግባራዊ ለማድረግ የእግር ኳስ ማኅበሩ ውድድሮች እንዳይካሄዱ መርሃግብሩን አግዶታል። እስካሁን ...

Read More »

በጎንደር ከተማ የስራ ማቆም አድማ ተጀመረ

ኢሳት (ጥቅምት 7 ፥ 2009) የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመቃወም ለሶስት ቀን የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ ሰኞ ጀመሩ። የከተማዋ ነዋሪዎች የወሰዱትን ዕርምጃ ተከትሎ በከተማዋ የሚገኙ በርካታ የንግድ ተቋማት በስራ ማቆሙ አድማ ተሳታፊ መሆናቸውን ከዜና ክፍላችን ጋር ቃለ-ምልልስን ያደረጉ ነዋሪዎች አስረድተዋል። ለሶስት ቀን የሚቆየው ይኸው አድማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ከመቃወም በተጨማሪ በቅርቡ በቢሾፍቱ ከተማ ከእሬቻ በዓል ...

Read More »

በሰበታ ከተማ ከህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ ከ 1ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ታሰሩ

ኢሳት (ጥቅምት 7 ፥ 2009) በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል ሰበታ ከተማ ተካሄዶ ከነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ ወደ 1ሺ አካባቢ ተጠርጣሪዎች በንብረት ላይ ውድመትን አድርሳችኋል ተብለው በቁጥጥር ስር ዋሉ። የከተማዋ አስተዳደር በቁጥጥር ስር የዋሉትን አብዛኞቹ ተጠርጣሪዎች ከሌሎች የኦሮሚያ አካባቢዎች የመጡ እንደሆነና ከ50 የማይበልጡት ብቻ የሰበታ ከተማ ነዋሪዎች መሆናቸውን ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን ገልጿል። የአስቸኳ ጊዜ አዋጁ ተግባራዊ መደረገን ተከትሎ በአንድ ከተማ ብቻ ...

Read More »

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ በማህበራዊ ድረገጾች ላይ ቁጥጥር መዘርጋቱ ታወቀ

ኢሳት (ጥቅምት 7 ፥ 2009) ባለፈው ሳምንት ተግባራዊ የተደረገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ መንግስት በማህበራዊ ድረገጾች ላይ ከፍተኛ ነው የተባለ ቁጥጥር መዘርጋቱን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ሰኞ ዘገቡ። የሃገሪቱ ዜጎች ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በድረገ-ጾች ላይ ምንም አይነት ጽሁፉ እንዳያሰፍሩ እገዳ እንደተጣለባቸውና ድርጊቱ ተጨማሪ ውጥረት ማንገሱን አፍሪካ ነውስ ኤጀንሲ በጉዳዩ ዙሪያ ባቀረበው ዘገባ አመልክቷል። በአዋጁ ተግባራዊነት ዙሪያ ዝርዝር መረጃን የሰጡ የመንግስት ...

Read More »

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንበት የድንበር ዙሪያ ወታደሮቿን አሰማራች

ኢሳት (ጥቅምት 7 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ወታደሮች እሁድ የኬንያ ድንበር አቋርጠው መግባታቸውን ተከትሎ ኬንያ ከኢትዮጵያ በምትዋሰንበት የድንበር ዙሪያ ወታደሮቿን አሰማራች። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ታጣቂዎችን ፍለጋ በሚል ወደ 100 አካባቢ የሚጠጉ የኢትዮጵያ ወታደሮች ዕሁድ ከሰዓት በኋላ ማርሳቤት ተብሎ ወደሚጠራ ግዛት መግባታቸውን የግዛቲቱ ባለስልጣናት ሰኞ ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። የማርሳቤት ግዛት ፖሊስ ኮማንደር የሆኑት ማርክ ዋንጀላ የኢትዮጵያ ወታደሮች የኬንያ ድንበርን ጥሰው በገቡ ...

Read More »

አፋኝ የተባለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በወጣ ማግስት የጎንደር ከተማ ህዝብ የመጀመሪያውን ቀን አድማ በተሳካ ሁኔታ አደረገ

ጥቅምት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አስተባባሪ ግብረሃይሉ ባለፈው አርብ የጠራውን የሥራ ማቆም አድማ ተከትሎ ዛሬ የከተማ ሱቆች፣ ሆቴሎች እና አገልግሎት ተቋማት ሁሉ ተዘግተው የዋሉ ሲሆን፣ አልፎ አልፎ ከሚንቀሳቀሱ ባጃጆች በስተቀር፣ አብዛኞቹ ተሽከርካሪዎች ስራ አቁመዋል። “ የሥራ ማቆም አድማ ማድረግ ክልክል ነው” የሚል አፋኝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከወጣ በሁዋላ፣ አዋጁን ከምንም ባለመቁጥር በክልሉ የሥራ ማቆም አድማ ሲደረግ ...

Read More »

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማክሸፍ ማለት የወያኔን ህልውና መጨረስ ማለት መሆኑን ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ

ጥቅምት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርበኞች ግንቦት7 ሊ/መንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ህወሃት መራሹ መንግስት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተመለከተ ዛሬ በሰጡት መግለጫ  አዋጁ “ ሰው ሆኖ መኖርን የናፈቀውና ካሁን በኋላ ያለነፃነት በፍጹም አልኖርም ብሎ ፍርሀትን በሚገርም ጀግንነት አሸንፎ ውድ ሕይወቱን እየከፈለና እየታገለ ያለውን፤ ከሞላ ጎደል መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ እንደገና በፍርሀት ቆፈን ውስጥ መልሶ በመክተት ከቀድሞውም በባሰ ...

Read More »

አዲሱ አፋኝ አዋጅ በወጣ ማግስት ዝርፊያ እየተጧጧፈ ነው

ጥቅምት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱን መረጃዎች እንደሚያሳዩት መላውን የአገሪቱን ህዝብ ለማፈን የወጣው አዋጅ ተግባራዊ ከሆነበት ቀን አንስቶ ፣ በእዙ ሰንሰለት ወይም ኮማንድ ፖስቱ ስር ነን ያሉ የተደራጁ የገዢው ፓርቲ አባላት በባለሃብቶች ቤት እየገቡ በማስፈራራት ዝርፊያ እየፈጸሙ ነው። እነዚሁ ታጣቂዎች፣ የኮማንድ ፖስቱ አባላት ነን በማለት ባለሃብቶችን “ የተቃዋሚ ደጋፊዎች መሆናችሁን ደርሰንብታል፣ ገንዘብ ካመጣችሁ አንነካችሁም ...

Read More »