ጥቅምት ፲ (አሥር) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዓለማችን ውስጥ በፖለቲካ ቀውስ ምክንያት ለቀጣይ እንደ አገር ለመቀጠል ከሚያሰጋቸው አገራት ውስጥ ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ አገር ኢትዮጵያ አንዷ ናት ሲል የአሜሪካ የጥናት ማእከል አስታውቋል። እያደገ ከመጣው የሕዝብ ብዛት እድገት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ እድገት የሌላት ድሃዋ አገር ኢትዮጵያ፣ ፍትሃዊ የሆነ አስተዳር ያልሰፈነባት አፋኝ ስርዓት ያላት መሆኑን ጥናታዊ ሪፖርቱ አመልክቷል። ይህን ጭቆና ተከትሎ በዓለማችን ...
Read More »Author Archives: Central
የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አባል ስንታየሁ ቸኮል በእስር ቤት ውስጥ ችግር እየደረሰበት መሆኑን ተናገረ
ጥቅምት ፲ (አሥር) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሕግ አግባብ ውጪ ታስሮ በእስር ላይ የሚንገላታው የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አባል ስንታየሁ ቸኮል በእስር ቤት ውስጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደተፈጸሙበት ለፍርድ ቤቱ በዝርዝር ተናግሯል። የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማእከላዊ በሚገኘው እስር ቤት ውስጥ በፌስታል እንዲፀዳዳ መደረጉን፣ ድብደባ እንደደረሰበት፣ በሃያ ስምንት ቀናት ቆይታው ለአንድ ቀን ብቻ እንዲናፈስ መደረጉን እና በጨለማ ክፍል ውስጥ ...
Read More »በደቡብ አፍሪካ አርበኞች ግንቦት7 ከፍተኛ የድጋፍ ማሰባሰብ ስራ መስራቱን አስተባባሪዎች ገለጹ
ጥቅምት ፲ (አሥር) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአገሪቱ የንቅናቄው ተወካዮች እንደገለጹት በተከታታይ ቀናት በተደረገው የገቢ ማሰባሰብ ስራ በደርባን 236 ሺ 400 ፣ በጆሃንስበርግ 252 ሺ ፣ በፕሪቶሪያ 180 ሺ፣ እንዲሁም በራስተምበርግ110 ሺ በአጠቃላይ በአራቱ ከተሞች በጨረታ ብቻ 778 ሺ 400 ራንድ ወይም 1 ሚሊዮን 334 ሺ 400 የኢትዮጵያ ብር አሰባስበዋል። በሁሉም ከተሞች በተደረገው የገቢ ማሰባሰብ ስራ የህዝቡ የትግል ...
Read More »ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ በማድረጓ ወደ 9 ሚሊዮን ዶላር (180 ሚሊዮን ብር) አካባቢ ማጣቷ ተገለጸ
ኢሳት (ጥቅምት 10 ፥ 2008) በኢትዮጵያ የተከሰተውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ሃገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ በማድረጓ ምክንያት ወደ 9 ሚሊዮን ዶላር (180 ሚሊዮን ብር) አካባቢ ማጣቷን አንድ አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ተቋም ይፋ አደረገ። ሃገሪቱ ለስድስት ወር የሚይቆየውን አዋጅ ተግባራዊ ካደረገች በኋላ የሞባይል ኔትወርክና ኢንተርኔት መዘጋት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ክፉኛ እየጎዳ እንደሚገኝ ካርትዝ አፍሪካ (Quartz Africa) የተሰኘ መጽሄት ዘግቧል። ገዢው የኢህአዴግ መንግስት ተግባራዊ ...
Read More »የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ የአፈናና ጭቆናን ሊያስፋፋ ይችላል ሲል ዘ-ጋርዲያን ጋዜጣ ዘገበ
ኢሳት (ጥቅምት 10 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሃገሪቱ ያሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ የአፈና እና ጭቆናን ሊያስፋፋ ይችላል ሲል በብሪታኒያ ተነባቢ የሆነው ዘ-ጋርዲያን ጋዜጣ ዘገበ። በወቅታዊ የሃገሪቱ የፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ልዩ ሪፖርትን ያቀረበው ጋዜጣው ገዥው የኢህአዴግ መንግስት በተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሱ ተቃውሞዎችን ለመቆጣጠር በወሰደው የሃይል ዕርምጃ በአመቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎችን መግደሉን አውስቷል። ህዝባዊ ተቃውሞችን ለመቆጣጠር ...
Read More »ህወሃት/ ኢህአዴግ እየወሰደ ያለው እርምጃ የተስፋ መቁረጥ እንደሆነ ተገለጸ
ኢሳት (ጥቅምት 10 ፥ 2008) በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ መንግስት እየወሰደ ያለው እርምጃ የተስፋ መቁረጥ ሁኔታ እንደሆነ የቀድሞ የአየር ሃይል አባላት ገለጹ። የቀድሞ አየር ወለድ 2041ኛ ብርጌድ የነበሩት ሻለቃ ሱራፌል ዘውዴና፣ የቀድሞ አየር ሃይል አብራሪና የበረራ መምህር የነበሩት ካፕቴን ተሾመ ተንኮሉ ለኢሳት እንደተናገሩት፣ ህዝብ ነጻነቱን ወደ እጁ ለማስገባት እየተዘጋጀ ባለበት ጊዜ ህወሃት እንደማንኛውም አምባገነን ስርዓት እየተፍጨረጨረ እንደሆነ ...
Read More »በኢትዮጵያ የተዘረጋው የአንድ ብሄር የበላይነት በአስቸኳይ መስተካከል ይኖርበታል ሲሉ የሶማሊላንድ ባለስልጣናት ጥሪ አቀረቡ
ኢሳት (ጥቅምት 9 ፥ 2009) በስልጣን ላይ ያለው ገዢው የኢህአዴግ መንግስት በሃገሪቱ የዘረጋውን የአንድ ብሄር የበላይነት የፓለቲካ ስርዓት በአስቸኳይ ማስተካከል ይኖርበታል ሲሉ የሶማሊላንድ ባለስልጣናት ጥሪ አቀረቡ። ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ የሶማሊላንድ ዲፕሎማት በተለያዩ ጊዜያት ከሃገሪቱ ጋር ለመምከር የሚመጡ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይና የመከላከያ ሚኒስቴር ሃላፊዎችን የአንድ ብሄር ብቻ ተወካይ መሆናቸውንና ጉዳዩ ጥያቄ እንዳሳደረባቸው መናገራቸውን ሶማሊላንድ ፕሬስ ጋዜጣ ዘግቧል። ራሷን እንደ ነጻ ሃገር ...
Read More »የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በፓርላማ መጽደቅ ቢኖርበትም ላለፉት ሁለት ሳምንታት አለመቅረቡ ተገለጸ
ኢሳት (ጥቅምት 9 ፥ 2009) የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያረቀቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በፓርላማ ቀርቦ መጽደቅ ቢኖርበትም አዋጁ ለሁለተኛ ሳምንት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አለመቅረቡ ታወቀ። የሚኒስትሮች ምክር ቤት አዋጁ ለፓርላማ ቀርቦ በቀናት ውስጥ ይጸድቃል ቢልም፣ የፓርላማ አባላት በጉዳዩ ዙሪያ አለመምከራቸው ለመረዳት ተችሏል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአዲሱ አመት ስራውን በቅርቡ ቢጀምርም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ መደበኛ የተባሉ የፓርላማ አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ...
Read More »አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለህዝባዊ ተቃውሞ ዕልባት ከመስጠት ይልቅ ሊያባብሰው እንደሚችል አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ
ኢሳት (ጥቅምት 9 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የአስችኳይ ጊዜ አዋጅ ከ800 በላይ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውን ህዝባዊ ተቃውሞ ዕልባት ከመስጠት ይልቅ ሊያባብሰው እንደሚችል አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። መቀመጫውን በብሪታኒያ ያደረገው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ አዋጁ መሰረታዊ የሚባሉ የሰብዓዊ መብቶችን አደጋ ውስጥ ከትቶ እንደሚገኝ ስጋቱን ገልጿል። በኦሮሚያ ክልል ለወራት ዘልቆ የቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ከ800 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑን ...
Read More »በጎንደር የሥራ ማቆም አድማው ለሶስተኛ ቀን ቀጥሎአል
ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከፍተኛ ማስፈራሪያ፣ እስርና እንግልት የደረሰባቸው በርካታ የጎንደር ከተማ ነጋዴዎች የመጨረሻውን ቀን የሥራ ማቆም አድማ ተግባራዊ አድርገዋል። የከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሄድባቸው አራዳና ሁለገብ የገበያ ማእከል እንደተዘጉ ውለዋል። በርካታ ነጋዴዎች ድማውን ተከትሎ ታስረዋል። ጎንደር እና ባህርዳር የሥራ ማቆም አድማውን በማድረግ አዋጁን ወድቅ ያደረጉ የመጀመሪያዎቹ ከተሞች ሆነዋል። በባህርዳር ተደርጎ ከነበረው የሥራ ማቆም አድማ በሁዋላ አገዛዙ ...
Read More »