ኢሳት (ህዳር 9 ፥ 2009) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተከትሎ በአንዳንድ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ጨዋታ ቢቀጥልም፣ ጎንደር ላይ ጨዋታ እንዳይካሄድ ኮማንድ ፖስቱ መከልከሉን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። በዚህም መሰረተ የፊታችን ዕሁድ በጎንደር ሊካሄድ የታቀደ የእግር ኳስ ውድድር ተሰርዟል። የፊታችን ዕሁድ በፋሲል ከነማና በወላዩታ ደቻ መካከል በጎንደር ስታዲየም ሊካሄድ መርሃ ግብር የተያዘለት የእግር ኳስ ውድድር ኮማንድ ፖስቱ በሰጠው ትዕዛዝ ...
Read More »Author Archives: Central
13 የሃይማኖት አባቶችና ካህናት በረሃ ወርደው አርበኞች ግንቦት 7ትን ተቀላቅለው ህዝብን በማስተባባር ላይ መሆናቸውን ገለጹ ።
ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዋልድባ ገዳም እና በተለያዩ ቤተክርስቲያኖች ሲያገለግሉ የነበሩ 13ቱ አባቶች ወደ በረሃ ለመውረድ የወሰኑት አገዛዙ በህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ግፍ እያዩ ዝም ለማለት ህሊናቸውና ሃይማኖታቸው ስላልፈቀደ መሆኑን ተናግረዋል። ጠመንጃ ይዘን ባንዋጋም ፣ በረሃ ወርደን ህዝቡ ለነጻነቱ እንዲነሳ እየቀሰቀስነው ነው ያሉት አባቶች፣ በረሃ ውስጥ ከአርበኞች ግንቦት7 አደራጆች ጋር ከተገናኙ በሁዋላ የኢትዮጵያ ወጣት ትግሉን እንዲቀላቀል ...
Read More »በደቡብ ኢትዮጵያ ግድያውና እስራቱ ቀጥሎአል
ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ በደቡብ ኢትዮጵያ በፓርቲ መሪዎች፣ በፓርቲ አባላት እና በህዝብ ላይ ወታደራዊ የኃይል እርምጃን ጨምሮ ከፍተኛ የሰብዐዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ ህዳር 5 /2009 ዓ.ም የኦሞ ህዝቦች ዲሞክርሲዊ ኅብረት/ ኦህዲኅ/ ምክትል ሊቀመንበርና የዞኑ ጽ/ቤት ተጠሪ መምህር ዓለማዬሁ መኮንን ፣ የዞኑ ...
Read More »የብአዴን አባላት በባህርዳር ከተማ ያለአግባብ የታሰሩ ነጋዴዎች እንዲፈቱ በድጋሜ ተጠየቀ፡፡
ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የገዥው መንግስት በባህር ዳር ከተማ የሚገኙ የብአዴን አባላትን በየክፍለ ከተማው ሰብስቦ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያና በተከሰቱት ህዝባዊ ተቃውሞዎች ዙሪያ ሰሞኑን ባነጋገረበት ጊዜ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሰበብ የታሰሩት ነጋዴዎችን ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ አባላቱ ጠይቀዋል። ጥያቄውን ያቀረቡት የብአዴን አባላት እንደተናገሩት የታሰሩት ነጋዴዎች በአጋጣሚ የንግድ ድርጅታቸውን ከፈተው አገልግሎት ሲሰጡ የተገኙት ብቻ መሆናቸውን ገልጸው ...
Read More »ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ታሰሩ
ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ ሽሮሜዳ አካባቢ ጋደኛቸውን ለማየት ሲሄዱ የነበሩት ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ፣ አናኒያ ሶሪና የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አባል የነበረው አቶ ዳንኤል ሺበሺ ከመንገድ ላይ ተይዘው ታስረዋል። ጋዜጠኛ አናኒና ሶሪ እና ኤሊያስ ገብሩ ገርጂ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ የታሰሩበትን አድራሻ ለማወቅ አልተቻለም።
Read More »የትግራይ ክልል በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚፈለጉትን አቶ ወልዱ ወልደአረጋይ አሳልፌ አልሰጥም አለ
ኢሳት (ህዳር 8 ፥ 2009) በባህርዳር ከተማ የጊዮን ሆቴልን ያለጨረታ ተከራይተው ለ20 አመታት ሲጠቀሙበት የነበሩት አቶ ወልዱ ወልደአረጋይ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ቢታዘዙም የትግራይ ክልል አሳልፌ አልሰጥም ማለቱ ተነገረ። የአቶ መለስ ዜናዊ ዘመድ እንደሆኑ የሚታወቁት አቶ ወልዱ ወልደ አረጋይ ከ1987 ዓም ጀምሮ ለ 20 አመታት የመንግስት የነበረው የባህርዳር ጊዮን ሆቴል ያለጨረታ ተከራይተው ሲገለገሉ ቆይተዋል። ይሁንና አቶ መለስ ከሞቱ ...
Read More »የትግራይ ክልል በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚፈለጉትን አቶ ወልዱ ወልደአረጋይ አሳልፌ አልሰጥም አለ
ኢሳት (ህዳር 8 ፥ 2009) በባህርዳር ከተማ የጊዮን ሆቴልን ያለጨረታ ተከራይተው ለ20 አመታት ሲጠቀሙበት የነበሩት አቶ ወልዱ ወልደአረጋይ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ቢታዘዙም የትግራይ ክልል አሳልፌ አልሰጥም ማለቱ ተነገረ። የአቶ መለስ ዜናዊ ዘመድ እንደሆኑ የሚታወቁት አቶ ወልዱ ወልደ አረጋይ ከ1987 ዓም ጀምሮ ለ 20 አመታት የመንግስት የነበረው የባህርዳር ጊዮን ሆቴል ያለጨረታ ተከራይተው ሲገለገሉ ቆይተዋል። ይሁንና አቶ መለስ ከሞቱ ...
Read More »በየመን የሚገኙ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ለከፋ የሰብዓዊ ቀውስ ተጋልጠዋል ተባለ
ኢሳት (ህዳር 8 ፥ 2009) በየመን በስደት ላይ የሚገኙ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ለከፋ የሰብዓዊ ቀውስና በሃገሪቱ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ተጋላጭ መሆናቸው ስጋት እንዳሳደረበት የአለም አቀፍ የሰደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቀ። ሰሞኑን በሳውዲ አረቢያ የሚመራው ጥምር ሃይል ለተወሰነ ጊዜ የሚፈጸመውን የአየር ጥቃት ማቆሙን ተከትሎ ድርጅቱ መውጫን አጥተው የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ከሃገሪቱ ለማስወጣት ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል። ይሁንና የስደተኞቹ ቁጥር ከፍተኛ መሆኑንና ...
Read More »ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የከፋ ቁጥጥርና አፈናን ከሚያደርጉ ስድስት የአለም ሃገራት መካከል አንዷ ሆና ተፈረጀች
ኢሳት (ህዳር 8 ፥ 2009) ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የከፋ ቁጥጥርና አፈናን ከሚያደርጉ ስድስት የአለም ሃገራት መካከል አንዷ ሆና መፈረጇን በጉዳዩ ዙሪያ ጥናትን ያካሄደ ያካሄደ አንድ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም ገለጠ። መቀመጫውን በዚህ በአሜሪካ ያደረገውና ሪፖርቱን ይፋ ያደረገው ፍሪደም ሃውስ ኢትዮጵያን ጨምሮ በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ አፈናን የሚያደርጉ ሃገራት በመገናኛ ልውውጥ ላይ እንቅፋት መፍጠራቸውን አስታውቋል። በአለማችን ካሉ ሃገራት መካከል ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት ለእስር የዳረጋቸውን ሁሉንም ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈታ ሲፒጄ ጥሪ አቀረበ
ኢሳት (ህዳር 8 ፥ 2009) የአለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) ኮሚቴ ቱ ፕሮቴክት ጆዎርናሊስትስ የኢትዮጵያ መንግስት ለእስር የዳረጋቸውን ሁሉም ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈታ ሃሙስ ጥሪውን አቀረበ። በሃገሪቱ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ተከትሎ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ ወከባ እየተፈጸመባቸው መሆኑን ድርጅቱት ለመንግስት ባቀረበው የጸሁፍ መልዕክት አመልክቷል። ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ አንድ ጋዜጠኛን ጨምሮ ሁለት ጦማሪያን ለእስር መዳረጋቸውን ያወሳው ሲፒጄ ሌላ ...
Read More »