ኢሳት (ጥር 1 ፥ 2009) በኢትዮጵያ አዲስ የተከሰተውን የድርቅ አደጋ ተከትሎ ወደ አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሊያቋርጡ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ። የምግብ እና ውሃን እጥረት እንዲሁም የመማሪያ ቦታና የትምህርት ግብዓቶች በበቂ ሁኔታ አለመኖሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንዲርቁ አስተዋጽዖ በማድረግ ላይ መሆኑን ድርጅቱ በድርቁ ዙሪያ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል። በአፋር፣ ሶማሊ፣ ኦሮሚያና የደቡብ ክልሎች ስር በሚገኙ በርካታ ዞኖች ተከስቶ ...
Read More »Author Archives: Central
በኢትዮጵያ በድርቅ አደጋ አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት ትምህርታቸውን ሊያቋርጡ እንደሚችሉ ተመድ አሳሰበ
ኢሳት (ጥር 1 ፥ 2009) በኢትዮጵያ አዲስ የተከሰተውን የድርቅ አደጋ ተከትሎ ወደ አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሊያቋርጡ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ። የምግብ እና ውሃን እጥረት እንዲሁም የመማሪያ ቦታና የትምህርት ግብዓቶች በበቂ ሁኔታ አለመኖሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንዲርቁ አስተዋጽዖ በማድረግ ላይ መሆኑን ድርጅቱ በድርቁ ዙሪያ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል። በአፋር፣ ሶማሊ፣ ኦሮሚያና የደቡብ ክልሎች ስር በሚገኙ በርካታ ዞኖች ተከስቶ ...
Read More »የአሜሪካ ኢምባሲ ዜጎቹ ወደ ባህርዳር እንዳይጓዙ አስጠነቀቀ
ታኅሣሥ ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሁለት ቀናት በፊት በባህርዳር ግራንድ ሆቴል የደረሰውን ፍንዳታ ተከትሎ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ዜጎቹ ወደ ባህርዳር እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል። የኢምባሲው ሰራተኞች ወደ ባህርዳር እንዳይጓዙም እገዳ ጥሏል። ኢምባሲው በመግለጫው ወደ ኢትዮጵያ መጓዝ የሚያስከትለውን አደጋ እየተከታተለ በማስታወቅ ላይ መሆኑን ጠቅሷል። በባህርዳር የደረሰውን ፍንዳታ በተመለከተ ገዢው ፓርቲ የሰጠው መግለጫ የለም። ይሁን እንጅ በከተማዋ ፍተሻ ...
Read More »የቦሌ መደበኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ጦማሪ አቤል ዋበላ ላይ ወደ መደበኛ ስራው እንዳይመለስ ሲል ፈረደ
ታኅሣሥ ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከዞን 9 ጦማሪዎች ጋር አንድ ዓመት ከአምስት ወራት በእስራት ያሳለፈውና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ በቴክኒሻን መሃዲስነት ሙያ ሲያገለግል የነበረው ጦማሪ አቤል ዋበላ በጥቅምት ወር 2008 ዓ.ም ከእስር በነጻ ከተለቀቀ በኋላ በነጻ የተለቀቀበትን የፍርድ ቤት መረጃ በመያዝ ወደ መደበኛ ስራው ቢሄድም አየር መንገዱ ወደ ስራ ገበታው እንዳይመለስ እገዳ ጥሎበታል። የአየር መንገዱን ውሳኔ ...
Read More »በጉጂ ዞን በድርቁ ምክንያት ትምህርት ቤቶች ተዘጉ
ታኅሣሥ ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ አፍሪካ የሚታየውን የዝናብ እጥረት ተከትሎ ዳግም የከፋ የርሃብ አደጋ ማንዣበቡን የአየር ንብረት ትንበያ ባለሙያዎች አስታወቁ። በድርቁ ምክንያት በተለይ አርብቶ አደር አካባቢዎች ክፉኛ ተጠቂ ሆነዋል። የምግብ እጥረት፣ የሰብል መበላሸት እና የእንስሳት መጎዳት በአርብቶ አደሮች ሕይወት ላይ ከፍተኛ አደጋ ደቅኗል። በኡጋንዳ፣ ኬኒያ፣ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ 12 ሚሊዮን ዜጎች ለከፋ ድርቅ ተጋልጠዋል። በተባበሩት ...
Read More »ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ዝምባብዌ የእርሻ ማሳ ውስጥ ተደብቀው ተገኙ
ታኅሣሥ ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዝንባቢዌ ማሮንዴራ ግዛት ውስጥ ቁጥራቸው 34 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በእርሻ ማሳ ውስጥ ተደብቀው ተይዘዋል። ስደተኞቹ የአገሪቷን ሕግ ተላልፈው በሕገወጥ መንገድ መግባታቸውን ተከትሎ ክስ ተመስርቶባቸዋል። ስደተኞች በሙሉ ወንዶች ሲሆኑ ከመሃከላቸው እድሜያቸው ከ11 እስከ 12 የሚገመቱ አራት ታዳጊዎችም ይገኙበታል። ስደተኞች ከአንዱ በስተቀር ሌሎቹ የቋንቋ ችግር ያለባቸው ሲሆን በኢንባሲያቸው በኩል አስተርጓሚ እስኪቀርብላቸው ድረስ በእስር ...
Read More »የዘንድሮውን የገና በዓል አከባባርን አስመልክቶ የሃይማኖት አባቶች መልዕክት አስተላለፉ
ኢሳት (ታህሳስ 28 ፥ 2009) ነገ ቅዳሜ በመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረውን የገና በዓል አከባባር አስመልክቶ የሃይማኖት አባቶች መልዕክት አስተላለፉ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ህብረትና የኢትዮጵያ መካነ-እየሱስ ቤተክርስቲያን መሪዎች የእምነቱ ተከታዮች በአሉን ችግረኞችን በመደገፍ እንዲሁም በመከባበርና የታመሙ ሰዎችን በመጠየቅ አክብረው እንዲውሉ በመልዕክታቸው ጠይቀዋል። የበአሉ አከባበር በተለይ በመዲናዋ አዲስ አበባ ከዋዜማው ጀመሮ በደማቅ ሃይማኖታዊ ...
Read More »የመሰረታዊ የሸቀጣሸቀጦች እጥረት በበአሉ አከባበር ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን ነዋሪዎች ገለጹ
ኢሳት (ታህሳስ 28 ፥ 2009) ሰሞኑን በመዲናይቱ አዲስ አበባ ከተማ ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች የተፈጠረው የመሰረታዊ የሸቀጣሸቀጦች እጥረት በበአሉ አከባበር ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን ነዋሪዎች አስታወቁ። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በዘይት ዱቄትና ስኳር ምርቶች ላይ የታየው አቅርቦት እጥረት በበአሉ ወቅት ሊቀርፍ አለመቻሉን ተጠቃሚዎች የገለጹ ሲሆን፣ የከተማዋ የንግድ ቢሮ በበኩሉ እጥረቱ ከስርጭት ጋር በተገናኘ የተፈጠረ ነው ሲል ምላሽን ሰጥቷል። ይሁንና አስመጪ ነጋዴዎች በሃገሪቱ ያለው ...
Read More »በባህርዳር የደረሰውን የቦምብ ፍንዳታ ተከትሎ የብሪታኒያ መንግስት ዜጎቹ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ
ኢሳት (ታህሳስ 28 ፥ 2009) በባህርዳር ከተማ በሚገኘው የግራንድ ሆቴል አቅራቢያ የደረሰውን የቦምብ ፍንዳታ ተከትሎ የብሪታኒያ መንግስት ዜጎቹ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ። የቦንብ ፍንዳታ መድረሱን ያወሳው የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በባህር ዳር ከተማ ሊኖሩ የሚችሉ የብሪታኒያን የአካባቢው ባለስልጣናት የሚሰጧቸውን ምክር እንዲከተሉ ጠይቋል። የብሪታኒያ መንግስት በባህር ዳር ከተማ የደረሰውን የቦንብ ፍንዳታ አስመልክቶ ለዜጎቹ ማሳሰቢያን ቢያሰራጭም በጥቃቱ የሞተ ሰው እንደሌለ ከመግለጽ ውጪ ዝርዝር ...
Read More »በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በታጣቂዎችና በመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል የተካሄደውን ውጊያ ተከትሎ 12 ሰዎች ታሰሩ
ኢሳት (ታህሳስ 28 ፥ 2009) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰሞኑን በአካባቢው ተቃዋሚ ታጣቂዎችና በመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል የተካሄደውን ውጊያ ተከትሎ በአሶሳ 12 ሰዎች መታሰራቸው ተነገረ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች አቶ ሃሊድ ናስር ለኢሳት እንደገለጹት የታሰሩት ሰዎች ሰላማዊ የአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው። በቤኒሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ /ቤህነን/ እና በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት መከላከያ ሃሙስና አርብ በተካሄደ ውጊያ 8 የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸው ተነግሯል። ከንቅናቄው በኩልም ...
Read More »