ዜና (የካቲት 2 ፥ 2009) በደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ የሚገኙ የአንደኛ አመት የኢንጂነሪንግ ተማሪዎች ሰሞኑን በወሰዱት ፈተና አንድም ተማሪ ሊያልፍ አለመቻሉን ተከትሎ ረቡዕ በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ተቃውሞን አካሄዱ። የዩኒቨርስቲው አስተዳደር በበኩሉ የፈተና ሂደቱ ከፖለቲካ ጋር የተገኛኘ ነው በማለት ተማሪዎቹ የጀመሩትን ተቃውሞ ለማረጋጋት መሞከሩን ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። ረቡዕ ረፋድ ላይ በተቀሰቀሰው በዚሁ ተቃውሞ የመማሪያ ክፍሎች መስኮቶችን መሰባበራቸውና ተማሪዎቹ ቁጣቸውን ሲያሰሙ ማርፈዳቸው ታውቋል። የዩኒቨርስቲው ...
Read More »Author Archives: Central
“ በተለይ ጊዜው ለትግራይ አስተማማኝ አይደለም” ሲል ብአዴን አስታወቀ
የካቲት ፩ ( አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብአዴን ሰሞኑን በክልሉ የተደረጉ ስብሰባዎችን በማስመለክት ባወጣው የማጠቃለያ ሪፖርት ላይ “ የሰላም መናጋት ለገዢው ፓርቲ አመራሮች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ህብረተሰብ የሚተርፍ ነው። በተለይ ለትግራይ ጊዜው አስተማማኝ አይደለም” ሲል ገልጿል። “የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ማበር ካልቻለ በስተቀር፣ ጊዜው አስተማማኝ” አይደለም የሚለው ብአዴን፣ የክልሉ ህዝብ በህወሃት ላይ ያለውን ጥላቻ በሪፖርቱ ላይ ...
Read More »የኦሮምያ ከተማ ልማት ቢሮ ሰራተኞች በጥልቅ ተሃድሶ ስም የቀረበውን ሪፖርት ተቃወሙ
የካቲት ፩ ( አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሁለት ሳምንት በፊት በአዳማ ከተማ ቶኩማ ሆቴል የተሰበሰቡት የኦሮምያ ከተማ ልማት ቢሮ ሰራተኞች፣ በአዲሱ ሃላፊያቸው የቀረበውን ሪፖርት አጣጥለውታል። ሃላፊው ፣” መንግስት ደሞዝ በመጨመር፣ ቤት ሰርቶ በመስጠትና የኑሮ ሁኔታችሁ እንዲሻሻል ቢያደርግም ፣ እናንተ ግን በተቀራኒው የምትሰሩት ስራ መንግስትን የሚያስወቅስ በመሆኑ ይህ እንዳይቀጥል ቃል መግባት አለባችሁ” ብለው ሲናገሩ፣ ሰራተኞቹ በበኩላቸው “ እርስዎ ...
Read More »አወዛጋቢው የትራፊክ ህግ ጸድቆ በስራ ላይ ዋለ
የካቲት ፩ ( አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በየካቲት ወር 2008 ዓ.ም በአዲስአበባ ከተማ ተግባራዊ ሊሆን ሲል በታክሲ አሽከርካሪዎች የሥራ ማቆም አድማ መንግሥት ተገዶ አፈጻጸሙ እንዲራዘም የወሰነው የትራፊክ ደህንነት ደንብ ቁጥር 208/2003 ጥቂት ማሻሻያዎችን በማድረግ ሰሞኑን ጸድቆ በሥራ ላይ ውሎአል፡፡ ደንቡ በተደጋጋሚ ጥፋት የሚገኝባቸው አሽከርካሪዎችን መንጃ ፈቃድ እስከመንጠቅ የሚደርስ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ሲሆን ፣ ባለፈው ዓመት ተግባራዊ ሊሆን ...
Read More »ወደ የመን ከሚሰደዱት ስደተኞች ውስጥ 80 በመቶ ኢትዮጵያውን መሆናቸውን ተመድ አስታወቀ
የካቲት ፩ ( አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለዓመታት በእርስበርስ ጦርነት ወደምትታመሰው የመን የሚሰደዱ ስደተኞች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የሚገልጸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነር /UNHCR/ ፣ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ከገቡት 87 000 ስደተኞች መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት ወይም ከ69 600 በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ናቸው ብሎአል። ቀጥሎ ያለውን ደረጃ የሚይዙት ሶማሊያውያን ስደተኞች ናቸው። በኢትዮጵያ ተከታታይ እድገት ተመዘገበ እየተባለ ...
Read More »በኢትዮጵያ በኩል ሁለት ኪሎግራም ኮኬይን ስታዘዋውር የነበረች የቤንዙዌላ ተወላጅ በቁጥጥር ስር ዋለች
ኢሳት (የካቲት 1 ፥ 2009) የካምቦዲያ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ በኩል ሁለት ኪሎግራም ኮኬይን የተሰኘ አደንዛዥ እፅ ስታዘዋውር የነበረች የቤንዙዌላ ተወላጅ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ረቡዕ አስታወቁ። ኔሊን ኮሮሞቶ የተባለችው ተጠርጣሪ አደንዛዥ እፁን ከብራዚል መዲና ሳኦ ፓሎ ከተማ ከተቀበለች በኋላ በኢትዮጵያ በኩል ወደ ታይላንድ ማሸጋገሯን የሃገሪቱ የኢሚግሬሽን ሃላፊዎች ዋቢ በማድረግ ዘ-ካምቦዲያ ዴይሊ የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። የ27 አመቷ ተጠርጣሪ አደንዛዥ እፁን ታይላንድ ካጓጓዘች ...
Read More »በጋምቤላ ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተገኝቶባቸዋል የተባሉ ዘጠኝ የክልሉ ስራ አስፈጻሚዎች ከሃላፊነት እንዲነሱ ተደረገ
ኢሳት (የካቲት 1 ፥ 2009) የጋምቤላ ክልል ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተገኝቶባቸዋል ያላቸው ዘጠኝ የክልሉ ስራ አስፈጻሚዎች ከሃላፊነት እንዲነሱ መደረጉን ረቡዕ አስታወቀ። የክልሉ የትምህርት ቤት ሃላፊ የነበሩት ቱት ጆክን ጨምሮ የክልሉ መስተዳደር የአስተዳደርና ማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ምክትል ኤዲተር፣ በጤናና በተለያዩ ከፍተኛ ቦታ ላይ የነበሩት ሃላፊዎች ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተገኝቶባቸዋል ተብለው መባረራቸውን የክልሉ መንግስት ለመገኛኛ ብዙሃን ገልጸዋል። ይሁንና ለአመታት ሲያገለግሉ የነበሩት እነዚሁ ...
Read More »የፓርላማ አባላትና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን እንዲያገኙ የሚያስችል አዋጅ ጸደቀ
ኢሳት (የካቲት 1 ፥ 2009) የፓርላማ አባላትን ጨምሮ ከሃላፊነታቸው የሚነሱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የመኖሪያ ቤትን ጨምሮ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን እንዲያገኙ የሚያስችል አዋጅ ጸደቀ። ያለምንም ተቃውሞ በፓርላማ አባላቱ የጸደቀው ይኸው አዲስ አዋጅ ሁለት የምርጫ ዘመን እና ከዚያ በላይ ያገለገሉ የምከር ቤቱ አባላት የመኖሪያ ቤት አገልግሎት እንዲያገኙ መፍቀዱ ታውቋል። እንዲሁም አንድ የምርጫ እና ከግማሽ ያላነሰ አገልግሎት ያበረከቱ፣ በህመም በአካል ጉዳት ወይንም ከአቅም ...
Read More »ኢትዮጵያ በጉለን ንቅናቄ ተቋም የተከፈቱ ትምህርት ቤቶችን ለቱርክ ለመስጠት መወሰኗን የቱርክ ባለስልጣናት ይፋ አደረጉ
ኢሳት (የካቲት 1 ፥ 2009) በቱርክ መንግስት የቀረበን ጥያቄ ተከትሎ ኢትዮጵያ በቱርኩ ጉለን ንቅናቄ ተቋም በአዲስ አበባ የተከፈቱ ትምህርት ቤቶችን ለቱርክ ለመስጠት መወሰኗን የቱርክ ባለስልጣናት ረቡዕ ይፋ አደረጉ። በቅርቡ በኢትዮጵያ ጉብኝትን ያደረጉ የቱርክ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሃገሪቱ መንግስት ሽብርተኛ ተብሎ በተፈረጀው የጉለን ድርጅት በኢትዮጵያ የተቋቋሙ ትምህርት ቤቶች ተላልፎ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል። የቀረበውን ይህንኑ ጥያቄ ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት ትምህርት ቤቶቹ በትምህርት ...
Read More »በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዳይነሳ “ኮማንድ ፖስቱ” አስጠነቀቀ
ጥር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል የሚታየውን የጸጥታ ሁኔታ ለመገምገም ከፌደራል የተላከው የኮማንድ ፖስቱ አጣሪ ቡድን ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቢነሳ ህዝቡ በቀጥታ በመንግስት ላይ ከእስካሁኑ የከፋ ጥቃት ሊሰነዝር ይችላል ሲል አስጠንቅቋል። ኮማንድ ፖስቱ “ የክልሉን ህዝብ ገትቶ የያዘው መሳሪያ ነው” ያለ ሲሆን፣ አዋጁ ቢነሳ ከእስካሁኑ በከፋ ሁኔታ አመፁን ለማስቀጠል ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠናል” ብሎአል፡፡ ለአንድ ወር ...
Read More »