ሰኔ ፯ (ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጉራጌ ዞን ዋና ከተማ ወልቂጤ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት ላይ አንድ የቀቤና ብሄረሰብ ተወላጅ የሆኑ ሴት መገደላቸውን ተከትሎ አቶ መስፍን አዳነ የተባሉ የአማራ ብሄር ተወላጅ በጥርጣሬ ከተያዙ በሁዋላ በቡድን የተደራጁ ሰዎች ወደ እስር ቤት ገብተው ግለሰቡን የገደሉት ሲሆን፣ ፖሊሶች ቆመው እያዩም መኖሪያ ቤቱ እንዲቃጠል ተደርጓል። የአካባቢው ፖሊሶች እጃቸው እንዳለበት የሚያመለክቱ መረጃዎች ...
Read More »Author Archives: Central
የህወሃት የግንባታ ኩባንያዎች የሚሰሩዋቸው ግንባታዎች በጥራት ችግርና በሙስና እየተወነጀሉ ነው
ሰኔ ፯ (ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃት የግንባታ ድርጅቶች በአማራ ክልል የሚሰሩዋቸው የግንባታ ስራዎች የጥራት ችግር ያለባቸው እንዲሁም ከተያዘላቸው የማጠናቀቂያ ጊዜ በላይ በማዘግየት በህብረተሰቡ ላይ ችግር እየፈጠሩ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ። በክልሉ የህንጻ ግንባታና መንገድ ስራዎችን በስፋት የተቆጣጠሩት የህወሃት ድርጅቶች ስራቸውን ለምን እንዳላጠናቀቁ በአካባቢው ነዋሪዎችና አመራሮች ሲጠየቁ፣ በማዕከላዊ ደረጃ የሚገኙ የህውሃት አመራሮችን እንደመከታ በመጥራት በቂ መልስ እንደማይሰጡ ...
Read More »የእንግሊዝ መንግስት ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ዜጎችን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ
ሰኔ ፯ (ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ዜጎች የደህንነት ዋስትናቸውን በተመለከተ ልዩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል። ምንም እንኳ ከ10 ቀናት በሁዋላ ተቋርጦ የነበረው የኢንትርኔት አገልግሎት መልሶ ቢመጣም፣ አገልግሎቱ ያለምንም ማስጠንቀቂያ በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ እንደሚችል በማስጠንቀቅ፣ ዜጎቹ ሌሎች የስልክ የመገናኛ አማራጮችን እንዲጠቀሙ አስጠንቅቋል። የእንግሊዝ ኢምባሲ በኢንተርኔት መቆራረጥ የተነሳ በቂ አገልግሎት ...
Read More »የአሜሪካ መንግስት ዜጎቹ ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዙ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አዲስ ማሳሰቢያ አወጣ
ኢሳት (ሰኔ 6 ፥ 2009) የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎቹ ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዙ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አዲስ ማሳሰቢያ አወጣ። ሚኒስቴሩ ማክሰኞ ባወጣው ማሳሰቢያ እንዳለው አስቸኳይ ጊዜ ከታወጀበት ከመስከረም 2009 በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ በተከሰተው ህዝባዊ ተቃውሞ ብዛት ያላቸው ሰዎች ለእስርና ለእንግልት መዳረጋቸውን ገልጿል። ሚኒስትሩ በድጋሚ በድረገጹ ያወጣው የጉዞ ጥንቃቄ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቀጣይ ከተደረገበት እኤአ ከ ማርች 2017 ጀምሮ በአማራ ክልል ...
Read More »በትግራይ አድዋ ከተማ የሚኖሩ ሙስሊሞች ጫና እየተደረገባቸው ነው ተባለ
ኢሳት (ሰኔ 6 ፥ 2009) በትግራይ ክልል አድዋ ከተማ የሚኖሩ ሙስሊሞች መስጊድ ገብተን ለመጸለይ እንዲሁም ሌሎች ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን እንዳይወጡ ጫና እየተደረገባቸው መሆኑን ገለጹ። የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን የመብት ጥያቄ ደግፈውታል በሚል ወከባ እየደረሰባቸው ያሉ ሙስሊሞች በቁጥር ከ150 እንደሚበልጡም ተመልክቷል። ሰለባዎቹ ለኢሳት እንደተናገሩት ይቅርታ ካልጠየቃችሁ ወደ መስጊድ አትገቡም ከሚለው ተፅዕኖ ባሻገር የሙስሊሞችን የመብት ጥያቄ ደግፋችኋል በሚል ፍ/ቤት ቀርበው ገንዘም ተቀጥተዋል። በረመዳን ወቅት መስጊድ ...
Read More »አቶ አብርሃ ደስታ ህይወቱን ያተረፉትን የመቀሌ ወጣቶችን አመሰገነ
ኢሳት (ሰኔ 6 ፥ 2009) ባለፈው ቅዳሜ በመቀሌ ከተማ ድብደባ የተፈጸመበት አቶ አብርሃ ደስታ ህይወቱን ያተረፉት የመቀሌ ወጣቶች መሆናቸውን ገለጸ። የአረና ፓርቲ ሊቀመንበር የሆነው አቶ አብርሃ ደስታ ቅዳሜ ሰኔ 3 ቀን 2009 አም ምሽት በመቀሌ ከተማ ባልታወቁ ሃይሎች በተፈጸመበት ጥቃት ከፍተኛ ጥቃት እንደደረሰበትም ተመልክቷል። አቶ አብርሃ ደስታ ቅዳሜ ምሽት ከምሽቱ 1 ሰዓት ተኩል ላይ በመቀሌ ከተማ አብርሃ ካስል በተባለው አካባቢ ...
Read More »የባህርዳርና የኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች ለብአዴኑ ጥረት ድርጅት ተላለፉ
ኢሳት (ሰኔ 6 ፥ 2009) የባህርዳርና የኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች ለብአዴኑ ጥረት ድርጅት መተላለፋቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። የባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ በጣሊያን ወረራ ምክንያት ለደረሰ ጉዳት በደም ካሳነት ለህዝብ ሲባል የተሰራ እንደነበር ይገለጻል። በቅርቡ 5 መቶ ሚሊዮን ወጪ ተደርጎ ማስፋፊያ የተሰራለትን የባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ እና የኮምቦልቻውን ጨምሮ ጥረት መጠኑ ባልታወቀ ርካሽ ዋጋ እንደተረከበው ለማወቅ ተችሏል። በአማራ ክልል ከዳሸን ቢራ ፋብሪካ ውጪ የረባ ...
Read More »ህወሃት አርበኞች ግንቦት 7 እና ኦብነግ የደረሱትን ስምምነት ተከትሎ የቴሌቪዥን ፕሮፓጋንዳ እያዘጋጀ መሆናቸው ተነገረ
ኢሳት (ሰኔ 6 ፥ 2009) የአርበኞች ግንቦት ሰባት የኢትዮጵያን ሃገራዊ አንድነትን ለማፈራረስ ከኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጪ ግንባር ጋር የጀመረው ሴራ በሚል የኢትዮጵያው አገዛዝ የፕሮፓጋንዳና የስለላ ተቋማት ዘጋቢ የቴሌቪዥን ፕሮግራም እያዘጋጁ መሆኑን ለኢሳት የደረስ መረጃ አመለከተ። ዘጋቢ የቴሌቪዥን ፕሮግራሙ አርበኞች ግንቦት 7 በዚሁ ምክንያት እየፈረራሰና አባላቱም እጅ እየሰጡ ናቸው የሚሉ ቃለ-ምልልሶችና ፊልሞች እየተቀናበሩለት መሆናቸውን የኢሳት የትምህርት ብልጭታ አዘጋጅ ዶ/ር ታደሰ ብሩ ...
Read More »የነጻነት ታጋዮች ቤተሰቦች እየታደኑ በመታሰር ላይ ናቸው
ሰኔ ፮ (ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጭልጋና መተማ ወረዳዎች የሚገኙ የነጻነት ታጋዮች ቤተሰቦች እየታደኑ በመታሰር ላይ መሆናቸውን ከአካባቢው የሚደርሱን መርጃዎች አመልክተዋል።የወልቃይት ጠገዴን የአማራ ማንነት ጥያቄን ተከትሎ በጎንደር የተነሳውን ህዝባዊ እንቅስቃሴ ለመጨፈለቅ የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ የወሰደው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ በርካታ አርሶአደሮች ቤተሰቦቻቸውን እየተዉ ጫካ ገብተው እየታገሉ ናቸው። እነዚህ ታጋዮች በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጽሙዋቸውን ጥቃቶች ተከትሎ አገዛዙ የታጋዮችን እንቅስቃሴ ለማቆም ...
Read More »አሜሪካ ዜጎቿ በድጋሜ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ አስጠነቀቀች
ሰኔ ፮ (ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ በጥቅምት ወር ላይ የተጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ፣ አሁንም በማንኛውም ጊዜ ህዝባዊ አመጽ ሊከሰት ስለሚችል ዜጓቿ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ ፣ ከተጓዙም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል። የኢትዮጵያ መንግስት መጋቢት ወር ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማራዘሙን የገለጸው የአሜሪካ መንግስት፣ አሁንም ድረስ አለመረጋጋት መኖሩን በተለይም በባህርዳርና ...
Read More »