ሐምሌ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “የወልቃይት የአማራ ማንነት ይከበር” በሚል መነሻ የተጀመረው ህዝባዊ እንቅስቀሴ ወደ አጠቃላይ የመብት እና የእኩልነት ጥያቄዎች ተሸጋግሮ፣ በሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ በምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እንዲሁም በአዊ ዞን ከፍተኛ ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴዎች መደረጋቸው የሚታወስ ሲሆን፣ አመጹ የተጀመረበትን ቀን ለመዘከር የተለያዩ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ ናቸው። ይህ ህዝባዊ አመጽ የስርዓቱን ህልውና አደጋ ላይ መጣሉን ...
Read More »Author Archives: Central
በኦነግ ስም በተከከሱ 22 ሰዎች ላይ ምስክሮች በዝግ እንዲሰሙለት አቃቢ ህግ ጥያቄ አቀረበ
ሐምሌ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ የተካሄደውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ ከኦነግ ጋር በተያያዘ በሽብር ወንጀል ተከሰው በታሰሩ 22 ተከሳሾች ላይ አቃቢ ህግ ምስክሮቹ በዝግ ችሎት እንዲታዩለት ጥያቄ አቅርቧል። ከተከሳሾች መካከል በአንደኛ ቁጥር ላይ የሚገኘው ደረጀ አለሙ ከእስር ቤት በማምለጡ ጉዳዩ በሌለበት በመታየት ላይ ነው። አቃቢ ህግ ሀምሌ 3 ቀን 2009 ዓም ለከፍተኛው ፍርድ ...
Read More »ታጋይ አበበ ካሴ ጨለማ ቤት መክረሙ ታወቀ
ሐምሌ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአርበኞች ግንቦት7 በሽብር ወንጀል ተከሶ በእስር ላይ የሚገኘው ታጋይ አበበ ካሴ ፣ በእስር ቤት የተሰፋለትን ዩኒፎርም አልለብስም በማለቱ ጨለማ ቤት ውስጥ ታስሮ መክረሙ ታውቋል። አበበ ዩኒፎረም እንዲለብስ ሲጠየቅ “ ጥሩ ጊዜ ላይ ነው ያሰፋችሁት እናንተው ትለብሱታላችሁ፣ እኔ አልለብስም” በማለቱ የተበሳጩት ፖሊሶች፡ ለወራት በጨለማ ቤት ውስጥ አስገብተው ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ...
Read More »የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ወለድ አርሶ አደሩን እያሰደደ ነው፡፡
ሐምሌ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ አርሶአደሮች ማዳበሪያና ምርጥ ዘር የራሱ ድርጅት ከሆነው ከአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም በምህጻረ ቃል አብቁተ በግድ ተበድረው እንዲወስዱ በማድረጉ፣ አርሶአደሮች በወለድ አመላለስ እና በምርታመነት ችግር ምክንያት መሬታቸው እና ከብቶቻቸው እየተወረሱባቸው እንደሚገኙ እየተናገሩ ነው። በምዕራብ አማራ በሚገኙ 73 ወረዳዎች አምና 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን አርሶ አደሮች በግዳጅ በወሰዱት ብድር ምክንያት ...
Read More »የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ማህበር በጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ ላይ የወሰደውን እርምጃ አወገዘ።
ሐምሌ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ሬዲዮ ጣቢያ ውስጥ ስፖርት አዘጋጅ በመሆን የሚሰራውን ጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒን የመስራት ነጻነት በሚጋፋ መልኩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ማህበር የጻፈውን ደብዳቤ ተከትሎ ማህበሩ በአባላቱ ሥም የተቃውሞ መልስ ጽፏል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ማህበር ሰኔ 16 ቀን 2009 ዓ.ም በብስራት ሬዲዮ ጣቢያ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴውን የሚኮንኑ እና ሚዛናዊነት ...
Read More »አዲሱ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለአራት አገራት 639 ሚሊዮን ዶላር የሰብዓዊ ዕርዳታ ለመስጠት ወሳኔ አሳለፈ:: ልገሳው ኢትዮጵያን አያካትትም።
ሐምሌ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአሜሪካ መንግስት ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል የ639 ሚሊዮን ዶላር በጀት አጽድቋል። ይህም አፋጣኝ ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው አራት አገራት እንደሚውል የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ (USAID) አስታውቋል። ከአራቱ አገራት አገራት ውስጥ በዘንድሮው ዓመት ኢትዮጵያ አልተካተተችም። ናይጀሪያ121 ሚሊዮን፣ ደቡብ ሱዳን 199፣ ሶማሊያ 126 ሚሊዮን እና የመን 191 ሚሊዮን ዶላር እያንዳንዳቸው እንደሚያገኙ ...
Read More »የአውሮፓ ህብረት 39 የፓርላማ አባላት በኢትዮጵያ የሚፈጸመው የሰባዊ መብት ጥሰት እንዲጣራ ጥሪ አቀረቡ
ኢሳት ዜና ( ሃምሌ 4, 2009 ) የአውሮፓ ህብረት 39 የፓርላማ አባላት በኢትዮጵያ የሚፈጸመው የሰባዊ መብት ጥሰት እንዲጣራ ጥሪ አቀረቡ ። የፓርላማ አባላቱ የፈረሙት ደብዳቤ ላይ እንደተገለጸው በኢትዮጵያ ያለው የሰባዊ መብት ረገጣ ሙሉ በሙሉ መጣራት ይኖርበታል ።በአገዛዙ የተቋቋመው የኢትዮጵያ የሰባዊ መብት ኮሚሽን ተካሄደ የተባለው የምርመራ ሪፖርት የገለልተኛነት ጥያቄ እንዳለበትም የፓርላማ አባላቱ ገልጸዋል ። የአውሮፓ ህብረት የ39ኙ የፓርላማ አባላት ፊርማ ያለበት ...
Read More »ለአበባ እርሻ የመሬት እጦት መኖሩን ጠ/ሚ ሃይለማሪያም ገለጹ
ኢሳት ዜና (ሀምሌ 4 ,2009 )በኢትዮጵያ የአበባ ኢንቨስትመንት በመሬት አቅርቦት እጥረት መገታቱን ጠ/ሚ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ለፓርላማ ገለጹ ። በኢህአዴግ ፓርላማ የ2010 በጀትን ለማጽደቅ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪኣም ደሳለኝ የሃገሪቱ የውጪ ንግድ እያሽቆለቆለ መሆኑን ተናግረዋል ። ችግሩን እንዲጎላ ካደረጉት ጉዳዮች መካከል በአበባ ኢንቨስትመንት ማስፋፋት ምክንያት የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ፌደራል መንግስት ያረገው ጥረት የክልል መስተዳደሮች መሬት አናቀርብም በማለታቸው ተስተጓጉሏል ሲሉ ስሞታ አቅርበዋል ...
Read More »በአዲስ አበባ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ተደረገ
ኢሳት ዜና (ሃምሌ 4 ,2009 ) የአዲስ አበባ አስተዳደር በመካከለኛ ገቢ ለሚኖሩ ሰዎች በገነባቸው የኮንደሚኒየም ቤቶች ላይ ያደገው የዋጋ ጭማሪ ተመዝጋቢዎችን ማስቆጣቱ ተነገረ ። አስተዳደሩ የ972 ቤቶችን እጣ ከማውጣቱ ሁለት ቀናት ቀደም ብሎ መካከለኛ ገቢ ላላቸው የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዋጋን በፊት ከታቀደው 56 በመቶ ጭማሪ አድርጓል ። ለቤቶቹ 11 ሺህ 88 ተመዝጋቢዎች የነበሩ ሲሆን ሁሉም ሙሉ በሙሉ የሚጠበቅባቸውን ክፍያ ...
Read More »በእስራኤል ኢትዮጵያውያን ከቀያቸው ተፈናቀሉ
(ኢሳት ዜና – ሐምሌ 4/2009) በእስራኤል ማቫሰርት ጺዮን አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ናቸው ከቀያችን አላግባብ ተፈናቅለናል ሲሉ በዋና ከተማዋ ቴልአቪቭ በመውጣት ድምጻቸውን ያስሙት መኖሪያቸውን እንዲለቁ የተሰጣቸው ከሁለት ወራት ያነሰ የጊዜ ገደብም ቢሆን አግባብነት የሌለው ነው ሲሉ ተናግረዋል። ለተፈናቃዮቹ ጥብቅና የቆመው አካልም የተወሰደው እርምጃ ትክክል አይደለም ሲል ጉዳዩን ለፍርድ ቤት አቅርቧል። እንደተቆርቋሪው አካል አገላልጽ ከሆነም ለተፈናቃዮቹ መዘጋጃ የሚሆን ተጨማሪ የሶስት አመት የጊዜ ...
Read More »