ሐምሌ ፲፫ ( አሥራ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ክልል ምክር ቤት ለሶስት ቀናት ባካሄደው ስብሰባ ላይ የሃብሩ ወረዳ ተወካይ እንደተናገሩት በሁለቱ ክልሎች መካከል የተነሳው ግጭት እየተባባሰ የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ነው ። ህጻናት፣ ሴቶችና አዛውንቶች ችግር ላይ መውደቃቸውንም የምክር ቤት አባሏ ገልጸዋል። የክልሉ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ችግሩ በንግግር መፈታቱን ቢናገሩም፣ የአካባቢው ወኪል ግን የሚቀበሉት አልሆኑም። በሁለቱ ...
Read More »Author Archives: Central
ብርሃን ኢትዮጵያ የባህል ማዕከል በመንገድ ግንባታ ሥም ሊፈርስ ነው
ሐምሌ ፲፫ ( አሥራ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ቅርስና ኪነጥበብን ለማስተዋወቅ ለመጀመሪያ ጊዜ በግል ተነሳሽነት የተቋቋመው ብርሃን ኢትዮጵያ የባህል ማዕከል በመንገድ ግንባታ ሥም የመፍረስ አደጋ ተጋርጦበታል። በአዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገኘውና በአንድ ግቢ ውስጥ የነገስታትን ታሪክ፣ የታሪካዊ ቦታዎችን፣ ባህላዊ እሴቶችን እና ዕደጥበቦችን በምስል አስደግፎ በማስተዋወቅ የቱሪዝም ገቢ ምንጭ በመሆን የአገር ባለውለታ ተቋም ...
Read More »በፕሬዝዳንት ሙላቱ ፊርማ የተፈቱት አቶ ከበደ ተሰራ እንደገና ታሰሩ
(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 12/2006)ወርልድ ባንክ በሚል ቅጽል ስም የሚታወቁት አቶ ከበደ ተሰራ በፕሬዝዳንቱ ይቅርታ ከተደረገላቸው 92 ታሳሪዎች መካከል አንዱ በመሆን ከእስር የወጡት ሰኔ 24 2009 ነበር። ከ13 ቀናት ከእስር ቤት ውጭ ቆይታ በኋላም በድጋሚ በጸጥታ ሃይሎች ታጅበው ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ ተደርጓል። የፕሬዝዳንቱን የይቅርታ ፊርማ በመሰረዝ ወደ ዘብጥያ እንዲመለሱ የተደረገው ከስምንት አመታት በፊት ተከሰው ከተፈረደባቸው የ25 አመታት የእስር ቅጣት ጋር ...
Read More »የአማራ ክልል ቱሪዝም ዘርፍ ገቢ ከግማሽ በላይ ቀነሰ
(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 12/2009)የአማራ ክልል ምክር ቤት 2ኛ አመት 7ኛ መደበኛ ስብሰባ ሰሞኑን በባህር ዳር በተካሄደበት ወቅት የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለምክር ቤቱ አባላት እንደተናገሩት ክልሉ በቱሪዝም ዘርፍ ያገኝ የነበረው ገቢ እየተገባደደ ባለው አመት 53 በመቶ ቀንሷል። በአማራ ክልል ያለው የቱሪዝም ገቢ በ53 በመቶ ሲቀንስ በሀገር አቀፍ ደረጃ በምን ያህል መጠን እንደቀነሰ የታወቀ ነገር የለም። ሆኖም የመንግስት ባለስልጣናት በሃገሪቱ የቀጠለው ...
Read More »የኦፌኮ ሊቀመንበር የኢትዮጵያ መንግስትን ከሰሱ
(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 12/2009)ዶክተር መራራ ጉዲናን ወክሎ ክሱን ለአፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ያቀረበው ማእከል ይህንን አህጉራዊ ተቋም ለምን መረጠ የክሱ ፋይዳስ ምን ሊሆን ይችላል ብዙዎች የሚያነሱት ጥያቄ ነው። የኢትዮጵያ የሰብአዊና የዲሞክራሲያዊ እድገት ማእከል አደራ ጠባቂና ጠበቃ የሆኑት ዶክተር አባድር ኢብራሂም ለኢሳት እንደገለጹት ክሱን ለዚሁ ተቋም የተመረጠው ኮሚሽን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን አያያዝ ጉድለት የሚያሳስበውና በጉዳዩ ላይም ተከታታይ መግለጫዎችን ያወጣ በመሆኑ ...
Read More »በደብረታቦር ኢየሱስ ደብር ገዳም የተነሳው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሏል
(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 12/2009)በደብረታቦር ኢየሱስ ደብር ገዳም ሊተከል በታቀደው የቴሌቪዥን ማማ ምክንያት የተነሳው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሏል ። ህዝቡ ወደ ቤተክርስቲያኒቱ በመሄድ ድምጹን እያሰማ ነው። ከቀናት በፊት የታሰሩት ባህታዊ አባ ብርሃኑ የህዝቡን ቁጣ ተከትሎ መፈታታቸው ታውቋል።
Read More »ከግብር ትመና ጋር በተያያዘ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዜናሐምሌ 12/2009) በግብር ትመና የተነሳ የተቀሰቀስው ህዝባዊ ተቃውሞ ዛሬም እንደቀጠለ መሆኑን ከተለያዩ አካባቢዎች ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች አመለከቱ። ከኦሮሚያ በተጨማሪ በደቡብ የኢትዮጵያ ክፍል በሲዳማ ዞን ሶስት ከተሞች የግብር ጭማሪውን በመቃወም አድማ መመታቱ ታውቋል። በተመሳሳይ በጋሞጎፋ ዞን በሳውላ፣ሰላም በር፣ ኦይዳ ዳራማሎ፣ ባስኬቶ ልዩ ወረዳ ተቃውሞ መነሳቱን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል
Read More »በኢትዮ ኤርትራ ድንበር አካባቢ ተቀስቅሶ የነበረው ግጭት መቆሙ ተገለጸ
(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 12/2009) በኢትዮጵያና በኤርትራ ድንበር ኢሮብ አካባቢ በሁለቱ መንግስታት ሃይሎች መካከል የተከሰተው ግጭት መቆሙን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። መጠነኛ ነበር የተባለው ግጭት የተካሄደው በሳምንቱ መጨረሻ እንደሆነ የተመለከተ ሲሆን ግጭቱን ማን ለምን አላማ እንደጀመረውም አልታወቀም አርብ እና በተለይም ቅዳሜ ዘለግ ብሎ የቀጠለውን ግጭት በተመለከተ በሁለቱም መንግስታት በኩል የተሰጠ መግለጫ የለም። የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ደጋፊ ድረ ገጾች ግጭቱን በተመለከተ ባቀረቡት ዘገባ ...
Read More »ከግብር ጋር በተያያዘ የተጀመረው አድማ ለሶስተኛ ቀን ቀጥሎአል
ሐምሌ ፲፪ ( አሥራ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከግብር ጋር በተያያዘ የተጀመረው አድማ ለሶስተኛ ቀን ቀጥሎ መዋሉን ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱን መረጃዎች አመልክተዋል። አድማው አድማሱን እያሰፋ በመምጣት ላይ ሲሆን፣ የአገዛዙ ካድሬዎች ነጋዴውን ማህበረሰብ ከተቻለ በማግባባት ካልተቻለም በማስፈራራት አድማውን እንዲያቆም ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ነው። አምቦ እንደ ሰሞኑ ሁሉ ዛሬም ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ወታደሮች ተከባ ውላለች። ወታደሮቹ በመኪኖች ላይ ተጭነው ...
Read More »በእነ ወጣት ንግስት ይርጋ ላይ የሚቀርቡት ምስክሮች እንዲታለፉ ብይን ተሰጠ
ሐምሌ ፲፪ ( አሥራ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ፣አቃቤ ህግ በእነ ንግስት ይርጋ ላይ ሊያቀርባቸው የነበሩት ምስክሮች እንዲታለፉ ብይን ሰጥቷል። አቃቤ ህግ 7 ምስክሮችን አቀርባለሁ ብሎ አስመዝግቦ የነበረ ሲሆን 2ቱን እንደማይፈልጋቸው በመግለጽ አሰናብቷቸዋል። ሶስቱን ምስክሮች ለማሰማት ፍርድ ቤቱ አራት ጊዜ ለፖሊስ ቀጠሮ ቢሰጥም፣ ፖሊስ ምስክሮችን ላገኛቸው አልቻልኩም ...
Read More »