ከግብር ትመና ጋር በተያያዘ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዜናሐምሌ 12/2009) በግብር ትመና የተነሳ የተቀሰቀስው ህዝባዊ ተቃውሞ ዛሬም እንደቀጠለ መሆኑን ከተለያዩ አካባቢዎች ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች አመለከቱ።

ከኦሮሚያ በተጨማሪ በደቡብ የኢትዮጵያ ክፍል በሲዳማ ዞን ሶስት ከተሞች የግብር ጭማሪውን በመቃወም አድማ መመታቱ ታውቋል።

በተመሳሳይ በጋሞጎፋ ዞን በሳውላ፣ሰላም በር፣ ኦይዳ ዳራማሎ፣ ባስኬቶ ልዩ ወረዳ ተቃውሞ መነሳቱን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል