Author Archives: Central

ሁለት ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ አንገታቸው ተቀልቶ ተገደሉ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 17/2009)ባራሂ መንገሻና ተወልደ ገብረስላሴ በሪያድ ከተማ ፓኪስታናዊውን የታክሲ ሹፌሩ ራቅ ወዳለ ስፍራ በመወሰድና በጩቤ በማስፈራራት አንገቱን በገመድ አንቀው ከገደሉት በኋላ ከመኪናው ወንበር ጋር አስረውት መሄዳቸውን ነው የሳውዲአረቢያ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ያስታወቀው። ኢትዮጵያውያኑ የታክሲ ሹፌሩን ከገደሉት በኋላ ገንዘቡን ዘርፈው እኩል መከፋፈላቸውን የሀገሪቱን ባላስልጣናትን ጠቅሶ ሪያድ ዴይሊ ዘግቧል። ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ወንጀሉን መፈጸማቸውን በማመናቸውና በማስረጃ በመረጋገጡ አንገታቸው ተቀልቶ በሞት እንዲቀጡ መደረጉን ...

Read More »

ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የተጓዘ አንድ ስፔናዊ በዝሆን ተመቶ ህይወቱ አለፈ  

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 17/2009)በስፔን የሚታተመው እለታዊ ጋዜጣ ላቫንጋርዲያ ሐምሌ 16/2009 ባወጣው እትሙ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የተጓዘ አንድ ስፔናዊ በዝሆን ተመቶ ህይወቱ ማልፉን አስነብቧል። ስሙ ያልተጠቀሰው ጎብኚ ጨበራ ጩርጨራ በተባለውና ደቡብ ኢትዮጵያ በሚገኘው የእንስሳት መጠበቂያ ስፍራ ከባለቤቱ ጋር ለጉብኝት የወጡት ከሳምንት በፊት ነበር። ጎብኚው ለአደጋ የተጋለጠው ከመኪናው ወርዶ በቅርብ ርቀት ዝሆኑን ፎቶ ለማንሳት በሞከረበት ወቅትም እንደሆነ ከዘገባው መረዳት ተችሏል። ጋዜጣው የአይን እማኞችን ...

Read More »

በአማራ ክልል በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ችግር ልማቱ ወደ ኋላ መቅረቱ ተሰማ

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 17/2009)በኤሌክትሪክ ሃይል ማጣት ስራ መጀመር ያልቻሉት የአማራ ክልል 197 ፕሮጀክቶች ከ6 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ የወጣባቸው ናቸው። ፕሮጀክቶቹ ስራ ቢጀምሩ ደግሞ ከ18 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥሩ እንደነበር የአማራ ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገልጿል። የኮሚሽኑ የፕሮሞሽንና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ይሄነው አለም ለሪፖርተር እንደገለጹት በክልሉ ያለው የሃይል አቅርቦት የክልሉን ልማት ወደ ኋላ እያስቀረው ነው። ዳይሬክተሩ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ በእኛ ስራ ምን አገባችሁ ሲሉ የመንግስት ባለስልጣናትን ተቃወሙ

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 17/2009)በሳምንቱ መጨረሻ አርብ ሐምሌ 14/2009 የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ ካሳ ተክለብርሃንና ሌሎች ባለስልጣናት ከአባቶቹ ጋር ያደረጉትን ውይይት በተመለከተ ዝርዝር መረጃን ይዞ የወጣው በቤተክርስቲያኒቱ ጉዳይ ላይ የሚያተኩረው ሃራ ተዋህዶ የተባለው ድረ ገጽ ነው። በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ አሉ የሚባሉ ችግሮችን መነሻ ባደረገው ውይይት ላይ የመንግስት ባለስልጣናት መገኘታቸውን አንዳንድ አባቶች ቢደግፉም፣ፓትሪያርኩን ጨምሮ ሌሎች አባቶች ግን ተቃውሞ ማሰማታቸውን ዘገባው አመልክቷል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ...

Read More »

ከቀን ገቢ ግብር ጋር ተያይዞ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ቀጥሏል

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 17/2009))መርካቶ ዛሬ በአብዛኛው ክፍል አድማ ተመቷል።ከጣና የገበያ አዳራሽ አንስቶ በምናለሽ ተራ፣ሶማሌ ተራ፣ሲዳሞ ተራ፣ጎጃም በረንዳ ምእራብ ሆቴል አካባቢ ዛሬ አድማውን ተቀላቅለዋል። የጣና ገበያ አዳራሽ ሱቆች ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል።ከግብር መስሪያ ቤት የደረሳቸው ተመን ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ስራቸውን ለማቆም እንደተገደዱ ዘጋቢያችን ያነጋገራችው ነጋዴዎች ገልጸዋል። ዘግይተው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በአንዳንድ አድማ በመቱ የመርካቶ ስፍራዎች የመንግስት ደህንነቶችና ታጣቂዎች እየተዘዋወሩ በማስፈራራት ላይ ናቸው። በዱባይ ...

Read More »

በአዲስ አበባ እና በሌሎችም ከተሞች የነጋዴዎች አድማ ተጠናክሮ ቀጥሎአል

ሐምሌ ፲፯ ( አሥራ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለሳምንታት የዘለቀው የነጋዴዎች አድማ ዛሬ ሰኞ፣ ሃምሌ 17 ቀን 2009 ዓም ተጠናክሮ ቀጥሎአል። በሳሪስ፣ ኮሌፌ አጠና በሌሎችም የአዲስ አበባ የንግድ ቦታዎች የተካሄደው አድማ በታላቁ ገበያ መርካቶም ተደግሟል። የአገሪቱ የንግድ ማእከል በሆነው መርካቶ አድማው የተጀመረው ከጠዋቱ ሲሆን፣ በርካታ መደብሮች በመሶብ ተራ፣ ሸራ ተራ ፣ ብርድ ልብስ ተራ፣ ሳህን ተራ፣ ...

Read More »

13 የመንግስት ወታደሮች ለአርበኞች ግንቦት7 እጃቸውን ሰጡ

ሐምሌ ፲፯ ( አሥራ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወታደሮቹ እጃቸውን የሰጡት ለንቅናቄው የሰሜን እዝ ሲሆን፣ 1 ብሬን መትረየስ፣ 2 ስናይፐር፣ 10 ክላሽ፣ 1600 ጥይቶችንና 2 የመገናኛ ሬዲዮና የተለያዩ የእጅ ቦንቦችን ይዘው ገብተዋል። ወታደሮቹ በመከላከያ ውስጥ ያለው ዘረኝነት አንገፍግፏቸው እጃቸውን ለመስጠትና የህወሃትን አገዛዝ ለመዋጋት መወሰናቸው ተናግረዋል። የኢሳት ወኪል ወታደሮችን በስልክ አነጋግሯቸዋል። እጃቸውን ስለሰጡ ወታደሮች ገዢው ፓርቲ እስካሁን ...

Read More »

ሲያወዛግብ የነበረው የባህር ዳሩ ታሪካዊ የሃጂ ኣድጎአይ ዳቦ ቤት ፈረሰ

ሐምሌ ፲፯ ( አሥራ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለ51 ዓመት ለባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ሲያገለግል የነበረው አንጋፋ ዳቦ ቤት አቶ ዳንኤል ለተባሉ የህውሃት ቀኝ እጅ ለካሬ ሜትር በብር 3600 ሂሳብ ተላልፎ መሰጠቱና በዚህም ምክንያት በህዝቡና በአመራሩ መካከል ከፍተኛ ውዝግብ ሲያስነሳ ቆይቷል። የሃጂ ኣድጎአይ ዳቦ ቤት ላይ በህይወት በሌሉት የከተማዋ ባለውለታ ስም ልጆቻቸው ግንባታ ለማከናወን ለካሬ ሜትር ...

Read More »

 ከግብር ጫና ጋር ተያይዞ የተነሳው ሕዝባዊ አመጽ መላ የኢትዮጵያ አካባቢዎችን እያዳረሰ ነው

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 14/2009)በሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የሚመራው/ሕወሃት/ የሚመራው መንግስት ለ2010 በጀት ከ320 ቢሊየን ብር በላይ በፓርላማ ሲያጸድቅ የበጀት ጉድለቱ ከ1 መቶ ቢሊየን ብር በላይ ማለትም የበጀቱ አንድ ሶስተኛ መሆኑን አሳውቆ ነበር። ይህንን ተከትሎም የአዲስ አበባ አስተዳደርና ሌሎች ከልሎችም በጀታቸውን ሲያጸድቁ የበጀት ጉድለታቸው የብዙዎቹ ከፍተኛ መሆኑም ነበር የተገለጸው። ከዚሁ ጋር ተያይዞም በነዋሪዎችና በተለይም በዝቅተኛ ህብረተሰብ ላይ ከፍተኛ የግብር ጫና መጣሉ ብዙዎችን ...

Read More »

ኢፈርት ለመቀሌ ከነማና ለወልዋሎ አዲግራት ስፖርት ክለቦች 30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 14/2009)የትግራይ መልሶ ማቋቋም ድርጅት/ኢፈርት/ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ አዜብ መስፍን ለመቀሌ ከተማና ለወልዋሎ አዲግራት ስፖርት ክለቦች 30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ። ኢፈርት  ለሁለት ክለቦች ማጠናከሪያም ለእያንዳንዳቸው ተጨማሪ 10 ሚሊየን ብር መሰጠቱ ተነግሯል። ድርጅቱ ሁለት ዘመናዊ አውቶቡሶችን ለሁለቱም ክለቦች መስጠቱንም ወይዘሮ አዜብ መስፍን ገልጸዋል። ለክለቡ ተጫዋቾችም ለእያንዳንዳቸው የ25 ሺ ብር ሽልማት አበርክተዋል። ወይዘሮ አዜብ መስፍን እንዳሉት በአጠቃላይ ለተጫዋቾችና ...

Read More »