ኢፈርት ለመቀሌ ከነማና ለወልዋሎ አዲግራት ስፖርት ክለቦች 30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 14/2009)የትግራይ መልሶ ማቋቋም ድርጅት/ኢፈርት/ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ አዜብ መስፍን ለመቀሌ ከተማና ለወልዋሎ አዲግራት ስፖርት ክለቦች 30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ።

ኢፈርት  ለሁለት ክለቦች ማጠናከሪያም ለእያንዳንዳቸው ተጨማሪ 10 ሚሊየን ብር መሰጠቱ ተነግሯል።

ድርጅቱ ሁለት ዘመናዊ አውቶቡሶችን ለሁለቱም ክለቦች መስጠቱንም ወይዘሮ አዜብ መስፍን ገልጸዋል።

ለክለቡ ተጫዋቾችም ለእያንዳንዳቸው የ25 ሺ ብር ሽልማት አበርክተዋል።

ወይዘሮ አዜብ መስፍን እንዳሉት በአጠቃላይ ለተጫዋቾችና ለአሰልጣኞቹ 2 ሚሊየን 7 መቶ ሺ ብር ሽልማት አበርክተዋል።

ኢፈርት በቀጣይም ለሁለቱም ክለቦች ሆነ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ለሚያድጉ ክለቦች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ወይዘሮ አዜብ መስፍን አረጋግጠዋል።

የመቀሌ ከነማና ወልዋሎ አዲግራት የስፖርት ክለቦች በፍጹም ቅጣት ምት ብዛትና በዳኛ ተጽእኖ ወደ ፕሪሚየር ሊግ እንዲያልፉ ምቹ ሁኔታ በፌዴሬሽኑ እንደተፈጠረላቸው የስፖርት ተንታኞችና ተችዎች ይናገራሉ