13 የመንግስት ወታደሮች ለአርበኞች ግንቦት7 እጃቸውን ሰጡ

ሐምሌ ፲፯ ( አሥራ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወታደሮቹ እጃቸውን የሰጡት ለንቅናቄው የሰሜን እዝ ሲሆን፣ 1 ብሬን መትረየስ፣ 2 ስናይፐር፣ 10 ክላሽ፣ 1600 ጥይቶችንና 2 የመገናኛ ሬዲዮና የተለያዩ የእጅ ቦንቦችን ይዘው ገብተዋል።
ወታደሮቹ በመከላከያ ውስጥ ያለው ዘረኝነት አንገፍግፏቸው እጃቸውን ለመስጠትና የህወሃትን አገዛዝ ለመዋጋት መወሰናቸው ተናግረዋል። የኢሳት ወኪል ወታደሮችን በስልክ አነጋግሯቸዋል።
እጃቸውን ስለሰጡ ወታደሮች ገዢው ፓርቲ እስካሁን የሰጠመው መግለጫ የለም።