(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 20/2009)ባለፈው ማክሰኞ በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተገለጸው 34ቱ ግለሰቦች ዛሬ ሀሙስ ፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል።–የቀረበባቸውም ክስ ተነቦላቸዋል። ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የቀድሞውን የባለስልጣኑን ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፍቃዱ ሃይሌን ጨምሮ ሶስት ኢንጂነሮች የታሰሩ ሲሆን ሚስተር ሚናሽ ሌቪ የተባሉ የኮንስትራክሽን ድርጅት ባለቤትም አብረው ታስረዋል። ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ሃላፊነታቸው ያልተገለጸ 7 ሰዎች ታስረው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።ሆኖም ግን ...
Read More »Author Archives: Central
በግብር ጭማሪው ላይ የተነሳው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሏል
(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 19/2009)አዲስ አበባ በከፍተኛ የሃይል ርምጃና የደህንነቶች ወከባ ውስጥ ሆናም አድማውን አላቋረጠችም። በማስፈራራት፣በማሸግና በማዋከብ የታጀበው የመንግስት ርምጃ በአንዳንድ ቦታዎች ውጤት እንዳላመጣ መረጃዎች ይጠቁማሉ።በመርካቶ ዛሬም ያልተከፈቱ ሱቆችና መደብሮች መኖራቸውን የኢሳት ወኪል ካደረሰን መረጃ ማወቅ ተችሏል። ዛሬ አየር ጤና በተባለው የአዲስ አበባ ክፍል ነጋዴዎች መደብሮቻቸውን በመዝጋት አድማውን ተቀላቅለዋል። የመንግስት ታጣቂዎች አካባቢውን በመውረር በሃይል ሊያስከፍቱ ሞክረው እንደነበር የጠቀሰው ወኪላችን በነጋዴው የተባበረ አቋም ...
Read More »ዶክተር አቡነ ኤውስጣጢዎስወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ሲኖዶሱ ማሳሰቢያ ሰጠ
(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 19/2009)በሀገር ቤት የሚገኘውና በብጹእ አቡነ ማቲያስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ አቡነ ጳውሎስ ከነበሩበት ግቢ ከጥቅምት 30 2004 ጀምሮ ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ 5 ደብዳቤዎችን መጻፉንና በስልክም ተደጋጋሚ ጥረት ማድረጉን አስታውቋል። ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ በአቡነ ጳውሎስ ሲጠየቁ በስነ መለኮት የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪ የነበሩት አቡነ ኤውስጣጢዎስ ትምህርቴን ጨርሼ እመለሳለሁ በማለታቸው ትምህርታቸውን አቋርጠው እንዲመለሱ በሚደረግባቸው ግፊት አለመግባባት መፈጠሩን የቤተክህነት ምንጮች ይገልጻሉ። ...
Read More »በአማራ ክልል የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ መስፋፋቱ ተገለጸ
(ኢሳት ዜና– ሐምሌ 19/2009)በአማራ ክልል በአምስት ዞኖችና 35 ወረዳዎች የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ ተስፋፍቷል ሲሉ ነው የኢሳት ምንጮች በመረጃቸው ያመለከቱት። በአሁኑ ወቅትም በአንዳሳ፣ወንቅሸት፣አቡነሃራና ወረብ ከሚባሉ አካባቢዎች በበሽታው ተጠቅተው የመጡ 17 ሰዎች በሆስፒታሉ ተኝተው እየታከሙ መሆናቸው ተገልጿል። በባህር ዳር ከተማ ወደ አዲስ አለም ሆስፒታል ከመጡ ታካሚዎችም 15 ሰዎች በወረርሽኙ መያዛቸው መረጋገጡን ለማወቅ ተችሏል። በአማራ ክልል ጤና ቢሮ አንድ የስራ ሃላፊ ለመገናኛ ...
Read More »ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በሙስና አለመታሰራቸው ታወቀ
(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 19/2009)በሀገር ቤት የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት በሙስና ተጠርጥረው ታስረዋል ከተባሉት 34 ባለስልጣናት፣ነጋዴዎችና ደላሎች መካከል የተንዳሆና መተሃራ ስኳር ፋብሪካ የቀድሞ ሃላፊዎች ተጠቃሽ ሆነዋል። ሰንደቅ ከአዲስ አበባ እንደዘገበው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የቀድሞ ሃላፊዎች ስራ አስኪያጁ አቶ አበበ ተስፋዬ፣የፋይናንስ ዘርፍ ስራ አስኪያጁ አቶ ተስፋዬ ድምጹ፣እንዲሁም የንብረት አስተዳደር ዳይሬክተሩ አቶ በሃይሉ ገበየሁ፣የፋብሪካው የቀድሞ የግዢና ንብረት አስተዳደር ሃላፊው አቶ ኤፍሬም አለማየሁ ከታሳሪዎቹ መካከል ...
Read More »የነጋዴዎች አድማ በአዲስ አበባ አየር ጤና አካባቢና በደጀን ቀጥሎ ውሎአል
ሐምሌ ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላ አገሪቱ ላለፉት 2 ሳምንታት የተካሄደው የንግዱ ማህበረሰብ አድማ ዛሬም ቀጥሎአል። በአዲስ አበባ በአየር ጤና አካባቢ የሚገኙ ነጋዴዎች የንግድ መደብሮችን በመዝጋት ተቃውሞ እያደረጉ ሲሆን፣ አካባቢው በፖሊሶች ተወሯል። በደጀን ከተማም እንዲሁ ትናንት የተጠራውን አድማ ነጋዴዎች ድርጅቶቻቸውን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ዛሬ ተግባራዊ አድርገውታል። ከተማዋ ሙሉ በሙሉ ጭር ብላ የዋለች ሲሆን፣ ...
Read More »በጉጂ ዞን ያለው ግጭት ተባብሶ ቀጥሎአል
ሐምሌ ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሃምሌ 16 ቀን 2009 ዓም ከቀንድ ከብቶች መዘረፍ ጋር በተያያዘ በጉጂ ኦሮሞዎችና በኮሬ ብሄረሰብ መካከል የተጀመረው ግጭት ተባብሶ ቀጥሎአል። ካለፉት 4 ቀናት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ባለው ግጭት እስካሁን ከሁለቱም ወገን ከ13 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ መሆኑን እና ከ300 በላይ ቤቶች መቃጠላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተለይ ገልማ መታሪ በሚባለው ...
Read More »አገሩ ባለቤት አልባ ሆኗል ሲሉ የኢህአዴግ የታች አመራር አባላት ተናገሩ
ሐምሌ ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ የወረዳ አመራሮች እንደሚሉት ባለፉት 26 ዓመታት አገሪቱ ባለቤት አልባ በመሆኗ ዝርፊያው ተጧጡፏል ። “ይችን አገር ከእንግዲህ ምን ልናደርጋት ነው?” ሲሉም ይጠይቃሉ። አቶ መላኩ አምሳሉ ላለፉት 24 አመታት በተለያዩ የአመራር ቦታዎች ላይ ሰርተዋል። በእነዚህ አመታት ሁሉ የተረዱት ነገር ቢኖር አገሪቱ ባለቤት አልባ መሆኗን ነው። ሙስናው እና ቢሮክራሲው አለ፣ ...
Read More »አቃቢ ህግ የአቶ በቀለ ገርባን የዋስትና መብት ተቃወመ
ሐምሌ ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኦፌኮ ም/ል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ የቀረበባቸው የሽብር ወንጀል ክስ ተቀይሮና በወ/ህ ቁጥር 257/ሀ መሰረት እንዲከላከሉ ፍርድ ቤት የወሰነላቸው መሆኑን ተከትሎ፣ አንቀጹ የዋስትና መብት የማያስከለክል በመሆኑ የዋስ መብታቸው እንዲከበርላቸው ቢያመለክቱም፣ አቃቢ ህግ ተቃውሞ አቅርቧል። አቃቢ ህግ “ ይህ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ማየት ሲጀምር በህግ አግባብ ተከሳሹን የዋስትና ...
Read More »በሳኡዲ አረቢያ ህጋዊ የመኖሪያ ወረቀት ከሌላቸው 400 ሺህ ከሚሆኑ ኢትዮጵያውያን እስካሁን ወደ ሀገራቸው የተመለሱት 60 ሺህ ያህሉ ብቻ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘገበ።
ሐምሌ ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሪያድ ባለፈው መጋቢት ወር ህጋዊ ወረቀት የሌላቸው ስደተኞች በ90 ቀናት ውስጥ ሀገሯን እንዲለቅቁ የሰጠችው ማስጠንቀቂያና የጊዜ ገደብ የተጠናቀቀው ትናንትና ነው። በተጠቀሰው ጊዜ የበርካታ ሀገራት ዜጎች ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ቢሆንም አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለስ ባለመፈለጋቸው ዛሬ በሳኡዲ አረቢያ መንግስት ተጨማሪ የአንድ ወር የምህረት ጊዜ ተሰጥቷቸዋል። ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያውያኑ ...
Read More »