(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 29/2010)በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ኢኮኖሚውን እንደሚያቆመው የብሔራዊ ባንክ ገዥ አስታወቁ። ኢትዮ-ቴሌኮም በበኩሉ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ስራ መስራትም ሆነ ብድር መክፈል አልቻልኩም ሲል አስታውቋል። የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ለፓርላማው የፋይናንስና በጀት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዳስታወቁት ከወጭ ንግድ እየተገኘ ያለው የውጭ ምንዛሪ ዝቅተኛ መሆን ሀገሪቱን አጣብቂኝ ውስጥ ከቷታል። በዚህ መልኩ ከቀጠለና የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሪ ማቅረብ ...
Read More »Author Archives: Central
ሰሜን ኮሪያ እያደረገች ባለችው የኒዩክለው ሙከራ ህጻናትና የአካባቢው ነዋሪዎች እየተጎዱ ነው ተባለ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 28/2010)ሰሜን ኮሪያ እያደረገች ባለችው የኒዩክለው ሙከራ ሳቢያ በሚፈጠረው አደገኛ መርዝ ያልተስተካከለ ሰውነት ያላቸው ሕጻናት እንደሚወለዱና በሕይወት መቆየትም እንደማይችሉ አንድ የምርምር ተቋም ይፋ አደረገ። ከሰሜን ኮሪያ ከድተው ወደ ደቡብ ኮሪያ የሄዱ ሰዎች ለምርምር ተቋሙ እንደገለጹት ወደ ስድስት ከሚደርሱና የኒዩክለር የሙከራ ፍንዳታ ከሚደረግባቸው አካባቢዎች ከሚመነጭ ወንዝ የሚመጣውን ውሃ ነዋሪዎች ይጠቀሙታል። ይህ ደግሞ ለህጻናቱ የአካል አለመስተካከልም ሆነ የሟቾች ቁጥርን ለመጨመር ምክንያት ...
Read More »ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም “እንዘጭ እምቦጭ የኢትዮጵያ ጉዞ” የሚል መጽሀፍ ለሕትመት አበቁ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 28/2010)ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም “እንዘጭ እምቦጭ የኢትዮጵያ ጉዞ” የሚል መጽሀፍ ለሕትመት አበቁ። መጽሀፉ በኢትዮጵያ ሕዝብ አኗኗርና ህጸጾች ላይ እንዲሁም ባለፉትና በአሁኑ የአገዛዝ ችግሮች ላይ ያተኮረ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ አገዛዝን ማስወገድና መንቀል ብቻ ሳይሆን ሕጋዊ ስርአት መተካት ካልቻለና የግፍ አዙሪቱ እንደሚቀጥል ፕሮፌሰር መስፍን በመጽሀፋቸው ጠቁመዋል። ፕሮፌሰር መስፍን አዲሱን መጽሀፋቸውን በተመለከተ ከኢሳት ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል። “እንዘጭ እምቦጭ የኢትዮጵያ ጉዞ” የተባለው ...
Read More »በደሴ ከተማ ዛሬ የስራ ማቆም አድማ ተደረገ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 28/2010) በደሴ ከተማ ዛሬ የስራ ማቆም መደረጉ ተገለጸ። በነጋዴዎች የተመታው የስራ ማቆም አድማ ባለፈው ዓመት ከተጣለው ዓመታዊ የቀን ግብር ጋር የተያያዘ ነው። በሌላ በኩል ዝዋይ በሚገኘው የካስትል ቢራ ፋብሪካ የሚሰሩ በሺህ የሚቆጠሩ ሰራተኞች የስራ ማቆም ከመቱ 10 ቀናት እንደሆናቸው ተገልጿል። በሀዋሳ የኢንዱስትሪ መንደር የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞችም ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የስራ ማቆም አድማ መምታታቸው ታውቋል። በደሴ ከተማ ከአቅም ...
Read More »ሼህ መሀመድ አላሙዲንን ጨምሮ ሌሎቹ የሳውዲ ባለሃብቶችና ባለስልጣናት በአንድ ቦታ መታሰራቸው ታወቀ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 28/2010)ሼህ መሀመድ አላሙዲንን ጨምሮ በቁጥጥር ስር የዋሉት የሳውዲ ባለሃብቶችና ባለስልጣናት የታሰሩበት ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል መሆኑ ቢረጋገጥም በሆቴሉ ወለል ፍራሽ ታድሏቸው በአንድ ቦታ መታሰራቸውን በምስል የተደገፉ ሪፖርቶች አመለከቱ። የሼህ መሀመድ አላሙዲን በሙስና ተጠርጥሮ መታሰር በኢትዮጵያ ባላቸው ኢንቨስትመንት ላይ የሚኖረው አንድምታ አነጋጋሪ ሆኗል። የሼህ መሀመድ አላሙዲን ከሳውዲ ልኡላንና ነጋዴዎች ጋር መታሰር በአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በስፋት መዘገቡ ቢቀጥልም በኢትዮጵያ ...
Read More »በአሜሪካ ቴክሳስ በአንድ ቤተክርስቲያን ላይ በተፈጸመ ጥቃት 26 ሰዎች ሞቱ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 27/2010) በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት በአንድ ቤተክርስቲያን ላይ በተፈጸመ ጥቃት 26 ሰዎች ሲሞቱ 20 ደግሞ ቆሰሉ። የሟቾቹ እድሜ ከ18 ወር ሕጻን እስከ 77 ባለው ክልል ውስጥ ነው በተባለው በዚህ ጥቃት 8 የአንድ ቤተሰብ አባላትም መገደላቸው ታውቋል። ጥቃቱን የፈጸመውም የ26 አመት እድሜ ያለውና የአእምሮ ታማሚ ሳይሆን አይቀርም የተባለው ዴቪን ኬሊ የተባለ የቀድሞ አየር ሃይል ባልደረባ መሆኑ ታውቋል። በአሜሪካ ቴክሳስ ሳውዘርላንድ ...
Read More »132 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በኬንያ ታሰሩ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 27/2010)132 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በኬንያ ናይሮቢ በፖሊስ መታሰራቸው ተነገረ። ኢትዮጵያውያኑ በሚኖሩበት መንደር ተከበው የታሰሩት በሕገወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ገብታችኋል በሚል ነው። በዚሁ አይነት ተመሳሳይ ዘመቻ ሌሎች ተጨማሪ 67 ሰዎች በሌላ አካባቢ ናይሮቢ ውስጥ በጅምላ መታሰራቸው ታውቋል። ኢትዮጵያውያን ስደተኞቹ በኬንያ ናይሮቢ በአንድ ክፍል ውስጥ ታጭቀው ወደ ታንዛኒያና ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር የተዘጋጁ እንደነበሩ ዥንዋ በዘገባው አመልክቷል። ስደተኞቹም በሞያሌ በኩል ወደ ኬንያ ...
Read More »ኡስታዝ አብዱልመጂድ ሁሴን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 27/2010) ታዋቂው የእስልምና እምነት መምህር ኡስታዝ አብዱልመጂድ ሁሴን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። በቴሌቪዥን በሚያቀርቡት የእልምና ትምህርቶች የሚታወቁት እኚህ መምህርና ሰባኪ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትላንት ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል። ዛሬ በአዲስ አበባ ኮልፌ የሙስሊሞች መካነ መቃብር በሺዎች የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት የቀብር ስነስርዓታቸው ተፈጽሟል። ይህ በእንዲህ እንዳለም አንጋፋው ጋዜጠኛ ግርማዬነህ ማሞ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። የቀብር ስነስርአቱም ...
Read More »የቅማንት አስተዳደር ጉዳይ ላይ የተጠራውን ስብሰባ ነዋሪው ረግጦ መውጣቱ ታወቀ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 27/2010)በሰሜን ጎንደር ዞን በጭልጋ በህወሀት መንግስት አማካኝነት ለማካለል በታቀደው የቅማንት አስተዳደር ጉዳይ ላይ የተጠራውን ስብሰባ ነዋሪው ረግጦ መውጣቱ ተገለጸ። ያለህዝበ ውሳኔና ፍቃድ በህወሀት መንግስት የተካለሉትን 42 ቀበሌዎች የሚያቅፈው የቅማንት ልዩ ዞን በሚል ለሚዋቀረው አዲሱ አስተዳደር በዋና ከተማነት በተመረጠችው አይከል ከተማ በህዝብና በመንግስት ባለስልጣናት መካከል ከፍተኛ ውዝግብ መፈጠሩን ለማወቅ ተችሏል። የቅማንት ማህበረሰብ በብዛት ይገኝበታል በተባለው የአይከል ከተማ ይህ ተቃውሞ ...
Read More »የቢን ላደንን ልጅ የቅርብ ጊዜ መልክ የሚያሳዩ የቪዲዮ ምስሎችን ይፋ ሆኑ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 24/2010)የአሜሪካው የስለላ ተቋም ሲ አይ ኤ እስካሁን ይፋ ያልሆኑና የቢን ላደንን ልጅ የቅርብ ጊዜ መልክ የሚያሳዩ የቪዲዮ ምስሎችን ይፋ አደረገ። ሲ ኤን ኤን የሲ አይ ኤን ቪዲዮ አባሪ አድርጎ ይፋ ባደረገ መረጃ የቢን ላደን ተመራጭና ተወዳጅ የሆነው ወንድ ልጁ ሀምዛ ቢን ላደን በሕጻንነቱ ከሚታወቀው ፎቶ ግራፉ ውጪ እስካሁን ምን ገጽታ እንዳለው በይፋ አይታወቅም ነበር። የአሜሪካው የስለላ ተቋም ሲ ...
Read More »