Author Archives: Central

ማይክል ፍሌን ጥፋተኛ ነኝ አሉ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 22/2010)   የፕሬዝዳንት ትራምፕ የቀድሞ የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ ማይክል ፍሌን ዛሬ በፍርድ ቤት ጥፋተኝነታቸውን አመኑ። ማይክል ፍሌን በፍርድ ቤት ቀርበው የሀገሪቱ የፌደራል ምርመራ ቢሮ/ኤፍ ቢ አይ/ ጉዳዩን በተመለከተ ባደረገላቸው ምርመራ መዋሸታቸውን አምነዋል።        የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀድሞ የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ ማይክል ፍሌን ሩሲያ ባለፈው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጣልቃ ገብታለች በሚል የፌደራል ምርመራ ቢሮ/FBI/ ምርመራ ሲያደርግላቸው በወቅቱ የሰጡት ቃል ከእውነት ...

Read More »

ጋዜጠኛ ሳሙኤል ፈረንጅ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 22/2010)  በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን በጋዜጠኝነትና በስራ አስኪያጅነት ለረጅም አመታት ያገለገለው ጋዜጠኛ ሳሙኤል ፈረንጅ ከዚህ አለም በሞት ተለየ። ሳሙኤል ፈረንጅ ከጋዜጠኝነቱ ሌላ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ ማገልገሉ ታውቋል። አቶ ሳሙኤል ፈረንጅ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በጋዜጠኝነትና በስራ አስኪያጅነት ለረጅም አመታት አገልግሏል።በሌሎች የመንግስት ተቋማትም በከፍተኛ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ አገልግለዋል። ከአባቱ ከቀኝ አዛማች ፈረንጅና ከእናቱ አበበች ገመዳ በ1929 ...

Read More »

የ104 ዓመቷ አዛውንት በድብደባ ተገደሉ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 22/2010) የ104 ዓመት አዛውንት ሴት በእስር ቤት በድብደባ ተገደሉ። በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ በሚገኝ እስር ቤት ባለፈው ረቡዕ የታሰሩት ወ/ሮ አምባሮ ሺክህ ዳይብ በደረሰባቸው ድብደባ ህይወታቸው አልፎ ዛሬ አስከሬናቸው ለቤተሰብ መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል። የእሳቸው ልጅ የ83 ዓመቱ አዛውንት አሊ አብዱላሂ ፊሂዬም በእስር ቤት የሚገኙ ሲሆን ህይወታቸው አደጋ ላይ በመውደቁ ህዝቡ እንዲከታተል ጥሪ ቀርቧል። መነሻው የፖለቲካ አቋም ነው። የአዛውንቷ የልጅ ...

Read More »

በቱርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አታሼ ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ትዕዛዝ ተላለፈ

(ኢሳት ዜና– ሕዳር 22/2010) የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቱርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አታሼ ሰክረው በፈጠሩት ችግር ምክንያት ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ትዕዛዝ አስተላለፈ። ዲፕሎማቱ ተስፋኪሮስ ሃይሉ ገብረማርያም ባለፈው ቅዳሜ በስካር መንፈስ መኪና ሲያሽከረክሩ ካደረሱት ተደራራቢ የትራፊክ አደጋ ጋር በተያያዘ ፖሊስ ሲያስቆማቸው ለህጉ ከመገዛት ይልቅ በኢትዮጵያና በቱርክ መሃል ጦርነት እጭራለሁ ሲሉ ማስፈራራታቸውን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል። የቱርክ መገናኛ ብዙሃንም ዲፕሎማቱ ያሳዩትን ያልተገባ ባህሪ ...

Read More »

የቦስኒያ ክሮሺያ ጄኔራል በችሎቱ ፊት መርዝ ጠጥተው ሕይወታቸውን አጠፉ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 21/2010)በሔግ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደታቸውን ሲከታተሉ የነበሩት የቦስኒያ ክሮሺያ ጄኔራል በችሎቱ ፊት መርዝ ጠጥተው ሕይወታቸውን አጠፉ። በቦስኒያ ሙስሊሞች ላይ በተፈጸመ የጦር ወንጀል ከዚህ በፊት የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባቸውና በ20 አመት እስራት እንዲቀጡ የተፈረደባቸው ጄኔራል አሟሟት ጉዳይ በመጠራት ላይ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ አንድ የቀድሞ የቻይና ጄኔራል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ እየተደረገባቸው ባለበት ወቅት ሕይወታቸውን ማጥፋታቸው ታውቋል። አንድ የቀድሞው ...

Read More »

የጋምቤላ ክልል ለመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ መክፈል አልቻለም ተባለ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 21/2010)በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኢኮኖሚ ቀውስ እየተባባሰ መቀጠሉ በሚነገርበት በአሁኑ ወቅት የጋምቤላ ክልል ለመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ መክፈል አለመቻሉን ገለጸ። በዚህም በክልሉ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች በሙሉ የጥቅምት ወር ደሞዛቸው እስከ ህዳር አጋማሽ እንዳልተከፈላቸው ታውቋል። የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ ክልሉ ገንዘብ ለመክፈል ጊዜያዊ ችግር እንዳጋጠመው አረጋግጠዋል። የጋምቤላ ክልል በስሩ የሚያስተዳድራቸው የመንግስት ሰራተኞች በአጠቃላይ 1550 ያህል እንደሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ። ታዲያ እነዚህ ሁሉ ሰራተኞች ...

Read More »

በአማራ ክልል ቻግኒ ከተማ ማንነታቸው ያልታወቀ ሰዎች በፖሊስና በአካባቢው የሚሊሻ ታጣቂዎች ላይ ጥቃት ሰነዘሩ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 21/2010)ይህ በእንዲህ እንዳለ በአማራ ክልል ቻግኒ ከተማ ማንነታቸው ያልታወቀ ሰዎች በፖሊስና በአካባቢው የሚሊሻ ታጣቂዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል። በደቡብ ጎንደር ደጎማም ዛሬ ክፍተኛ የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል። በሀዋሳና በአዲስ አበባ አንዳንድ ቦታዎች የትግል ጥሪ ወረቀቶች መበተናቸው ታውቋል። በአዊ ዞን ቻግኒ ከተማ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች በፖሊስና በአካባቢው ሚሊሻ ታጣቂዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ነው የታወቀው። ...

Read More »

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞ ተካሄደ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 21/2010)በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞ ተካሄደ። በምስራቅ ሀረርጌ ሰሞኑን የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም የቀጠለ ሲሆን የህወሃት መንግስት ከስልጣን ይውረድ የሚለው ደግሞ ጥያቄያቸው ነው ። በወለጋ የተለያዩ ከተሞች ህዝባዊ ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው። በሌላ በኩል በአርባምንጭ ከተማ የሚገኘውን አየር ማረፊያ ሲጠብቁ የነበሩ ወታደሮች መጥፋታቸው ታወቋል። ባህርዳር የሚገኘው የምዕራብ እዝ አየር ምድብ አባላትም ለሁለት ቀናት አድማ አድርገዋል። ዳግም የተቀሰቀሰውንና ለበርካታ ሰዎች መገደል ...

Read More »

ከስልጣን የተወገደው የህወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ራሱን ወደ ጥገኛ ገዢ መደብ የማሸጋገር አዝማሚያ ተጠናውቶት ነበር ተባለ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 21/2010)በአባይ ወልዱ ሲመራ የነበረው የህወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ራሱን ወደ ጥገኛ ገዢ መደብ የማሸጋገር አዝማሚያ ተጠናውቶት እንደነበር የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ በአቋም መግለጫው አስታወቀ። ስራ አስፈጻሚው የውሸት ሪፖርት ሲያወጣ እንደነበርም ተመልክቷል። በትግራይ ማህበረሰብ ዘንድ የአድዋ ተወላጆች ስልጣኑን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጠሩት የሚል አስተያየት በሰፊው በመደመጥ ላይ ነው። ለተራዘሙ ቀናት በመቀሌ ግምገማ ተቀምጦ የነበረው የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ህዳር 21/2010 ድርጅታዊ የአቋም ...

Read More »

የመውሊድ በአል ተከበረ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር /2010)የነብዩ መሀመድ 1 ሺ 492ኛው የልደት በአል በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ተከብሮ ዋለ። በአሉ በተለይም በኢትዮጵያ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ በድምቀት ተከብሯል። በበአሉ ላይ የእምነቱ ተከታዮች በአሉን ሲያከብሩ የሰላም፣የፍቅርና የመቻቻል አስተምህሮቶችን በመጠበቅ ሊሆን እንደሚገባ ተገልጿል። የነቢዩ መሀመድን አስተምህሮ ህዝበ ሙስሊሙ እርስ በእርሱ በመዋድድና በመረዳዳት ሊተገብረው እንደሚገባ በበአሉ አከባበር ላይ ተገልጿል፡፡ በአሉ በዚህ በአሜሪካም በተለያዩ አካባቢዎች በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ተከብሮ ውሏል።

Read More »