(ኢሳት ዲሲ–ጥር 1/2010) የኦሮሚያ ክልል የፍትህ ቢሮ በቄሮዎች ላይ ምርመራ ማካሄድ ህገወጥ ነው አለ። ቢሮው ይህን ያስታወቀው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት በቄሮዎች ላይ ምርመራ እያደረኩ ነው ማለቱን ተከትሎ ነው። የቢሮው የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ ለጀርመን ድምጽ ሬዲዮ እንደተናገሩት የፌደራል ፖሊስ እያደረኩ ነው ስላለው ምርመራ የኦሮሚያ ክልል መንግስት የሚያውቀው ነገር የለም። የሃላፊው መግለጫ ምርመራው ትኩረት ለማስቀየር የታለመ ነው የሚሉ የፖለቲካ ምሁራንን ...
Read More »Author Archives: Central
በጎረቤት ሀገር ሱዳን ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 30/2010) በዳቦ ዋጋ ላይ የተደረገ ጭማሪ በጎረቤት ሀገር ሱዳን ከፍተኛ ተቃውሞ ቀሰቀሰ። በአራት ከተሞች ህዝብ አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞውን የገለጸ ሲሆን በዚህም ተቃውሞ አንድ ሰው ሲገደል 6 ቆስለዋል። አመጹን አስነስተዋል በሚል ሶስት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ሲታሰሩ 6 ጋዜጦች ተዘግተዋል። በምዕራብ ዳርፉር ግዛት የተጀመረው ተቃውሞ ርዕሰ መዲናዋ ካርቱም መድረሱም ታውቋል። አልጀዚራ እንደዘገበው ትላንት እሁድ በምዕራብ ዳርፉር ግዛት መዲና ጌኒና የተጀመረው ...
Read More »ዶክተር ፍቅሩ ማሩ የሞቱት ታካሚዎች ቁጥር 20 ደርሷል አሉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 30/2010) በከፍተኛ ጥበቃ ስር ሆኜ የልብ ሕሙማንን እንዳክም ጠይቄ ስላልተፈቀደልኝ የሞቱት ታካሚዎች ቁጥር 20 ደርሷል ሲሉ በእስር ላይ የሚገኙት ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ለፍርድ ቤት ገለጹ። ከእስር ቤት ወደ ፍርድ ቤት በአቃቢ ሕግ ምስክር አለማቅረብ ምክንያት መመላለስ እንደመረራቸውም ታዋቂው የልብ ሃኪም ዶክተር ፍቅሩ ማሩ በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በእስር ቤት እየደረሰባቸው ያለውን እንግልት ተናግረዋል። አቃቢ ሕግ ...
Read More »የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ሊያካሂድ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 30/2010) የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ከጥር 12/2010 ጀምሮ ለ8 ቀናት በባህርዳር ከተማ እንደሚካሄድ የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በስብሰባው ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ከአራት ጊዜ በላይ በጉባኤው ተመርጠው የሰሩ የብአዴን አባላት ይገኛሉ ተብሏል። ሕወሃትም ከጉባኤው በፊት ባልተለመደ ሁኔታ ከፍተኛ አመራሮች የሚገኙበት ድርጅታዊ ጉባኤ ከጥር 3/2010 ጀምሮ ለ8 ቀናት በመቀሌ እንደሚያካሂድ ታውቋል። ኢሳት ከምንጮች ያገኘው ሰነድ እንደሚያመለክተው የብአዴን ...
Read More »ሁለት የስውዲን ፓርላማ አባላት ለመንግስታቸው ጥሪ አቀረቡ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 30/2010) ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸመ ያለውን ግድያና የሰብአዊ መብት ጥሰት ችላ ከማንልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል ሲሉ ሁለት የስውዲን ፓርላማ አባላት ለመንግስታቸው ጥሪ አቀረቡ። አንድሬስ አስተርበርግና ማሪያ አንደርሰን የተባሉ የስዊዲን ፓርላማ አባላት በኢትዮጵያ የሚፈጸመውን ጭፍጨፋ በቸልታ የምናየው ከሆነ አጠቃላይ የእርስ በርስ ጦርነት ሊከሰት ይችላል ሲሉ አስተጠንቅቀዋል። የስውዲን መንግስትም አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ በሚል ጥያቄ ያቀረቡት አባላቱ ከዚህ በኋላ ከኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ...
Read More »በአማራ ክልል ከ20 በላይ ሰዎች ተገድለዋል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 30/2010) በአማራ ክልል ተደጋጋሚና ድንገተኛ ጥቃት ባለፈው ወር ብቻ በአገዛዙና በመንግስት ተቋማት የስራ ሃላፊዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች መሞታቸውን በብሔራዊ የጸጥታና ደህንነት ምክር ቤት ላይ የቀረበ ሪፖርት አመለከተ። ከሟቾቹ መካከል የቀበሌና የወረዳ አስተዳደር ባልደረቦች እንደሚገኙበት ከአማራ ክልል ለምክር ቤቱ የቀረበው ሪፖርት ያስረዳል። የብሔራዊ፣ የጸጥታና ደህንነት ምክር ቤት ከዚህ በፊት የወጣውን እቅድ እንደገና በመከለስ አዲስ የጋራ ዘመቻ ...
Read More »በቄሮዎች ላይ ምርመራ ተጀመረ ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 30/2010) የኦሮሞ ወጣቶች እያደረጉ ያሉት ትግል ያሳሰበው የሕወሃት አገዛዝ በቄሮዎች ላይ ምርመራ ጀመርኩ አለ። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ኦፌኮ ምርመራውን ከንቱ ድካም ሲል አጣጥሎታል። የፌደራል ፖሊስ ቄሮ ተብሎ በሚጠራው ቡድን ላይ ምርመራ ጀመርኩ ባለበት መግለጫ በአንዳንድ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የመንግስት መዋቅር ሙሉ በሙሉ መፍረሱን ያመነበት መሆኑ ታውቋል። የአቶ ለማ መገርሳ ቡድን ከእጃችን አልወጣም የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ የታሰበ መግለጫ ነው ...
Read More »ለኦሮሞና ለአማራ ተወላጆች የጄኔራልነት ማዕረግ ሊሰጥ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 30/2010) የመከላከያ ሰራዊቱን በተመለከተ የሚነሱ ተቃውሞዎችን ተከትሎ ለኦሮሞና ለአማራ ተወላጆች የጄኔራልነት ማዕረግ ለመስጠት መወሰኑን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። ማዕረጉ ይሰጣቸዋል የተባሉት መኮንኖች ለተሃድሶ ስልጠና መግባታቸው ተመልክቷል። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በመከላከያ ሰራዊቱ አመራር ውስጥ ያለውን ውጥረት በመቃወም የሚደረጉ ግፊቶችን ተከትሎ የአመራር ቦታዎቹን ከማስተካከል ይልቅ አዳዲስ ግለሰቦችን ከሌላ ብሔረሰብ ለመሾም ዝግጅት መጠናቀቁን መረዳት ተችሏል። ከ30 የማያንሱ ሰዎች ይሾሙበታል በተባለው በዚህ ፕሮግራም ...
Read More »ኡጋንዳ እጩዎች ላይ የጣለችውን የዕድሜ ገደብ አነሳች
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 27/2010) ኡጋንዳ ለፕሬዝዳንትነት በሚወዳደሩ እጩዎች ላይ የጣለችውን የዕድሜ ገደብ አነሳች። ርምጃው ፕሬዝዳንት ዮዎሬ ሞሶቬኒ እድሜያቸው ለተጨማሪ ፕሬዝዳንታዊ ውድድር አለመፍቀዱን ተከትሎ የተነሳ እንደሆነም ታውቋል። የኡጋንዳ ፓርላማ በኡጋንዳ ሕገመንግስት ላይ የተቀመጠውን የዕድሜ ጣሪያ ያነሳው 317 ለ97 በሆነ የድምጽ ብልጫ እንደሆነም አልጀዚራ በዘገባው ላይ አስፍሯል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1995 የታወጀው የኡጋንዳ ሕገመንግስት ዕድሜው 35 አመት ያልደረሰና ከ75 አመት ያለፈው የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ...
Read More »ወጣቱ በፍርድ ቤት ጉዳቱን እንዳያሳይ ተከለከ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 14/2010) በማዕከላዊ የማሰቃያ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ የደረሰበት ወጣት በፍርድ ቤት ጉዳቱን እንዳያሳይ ተከለከ። ወጣት ፈዲሳ ጉታ በማዕከላዊ እስር ቤት ከፍተኛ ሰቆቃ የተፈጸመበት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ማዕከላዊን በተመለከተ አነጋጋሪ የሆነ መግለጫ በሰጡበት በዚሁ ሳሞን ነው። ዳኞች ፈዲሳን ጉዳቱን እንዳያሳይ ከከለከሉት በኋላ የደበደቡህን ክሰሳቸው ማለታቸው ተገልጿል። ወጣት ፈዲሳ ጉታ የታሰረው ከወለጋ ነው።የተከሰሰው በኦነግ ስም ሲሆን የሽብር ተግባር ለመፈጸም በማቀድና ...
Read More »