Author Archives: Central

እነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ከወህኒ ተለቀቁ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 15/2010) እነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ በዛሬው እለት ከወህኒ ተለቀቁ።ከሚያዚያ 2001 ጀምሮ ላለፉት 9 አመታት በቃሊቲና በዝዋይ ወህኒ ቤት በእስር ላይ የቆዩት እነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ዛሬ ከዝዋይ ወህኒ ቤት መውጣታቸው ተረጋግጧል። ከብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ እና ብ/ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ጋር ዛሬ ከወህኒ የወጡት መኮንኖች እና ሌሎች እስረኞች ኢንጂነር መንግስቱ አበበ፣ኮሎኔል አበረ አሰፋ፣ኮሎኔል ሰለሞን አሻግሬ፣ሻለቃ መኮንን ወርቁ፣ሻለቃ ...

Read More »

የሕወሃት ጨዋታ አበቃለት ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 15/2010) “የሕወሃት ጨዋታ አበቃለት”ሲሉ የአሜሪካው ኮንግረስማን ዳና ሮራ ባከር ገለጹ። የካሊፎርኒያው የሕዝብ ተወካይ ዳና ሮራ ባከር በቲውተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት አገዛዙ በመጨረሻ የሞት አፋፍ ላይ ያለና ያበቃለት ስርአት ነው። ኮንግረስ ማኑ ከዚህ ቀደም በአሜሪካ ምክርቤት በተካሄዱ ውይይቶች ሕወሃት ኢትዮጵያን የማይወክልና በሀገሪቱ ለተፈጸሙ ግድያዎች እንዲሁም የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ተጠያቂ ነው ማለታቸውም ይታወሳል። በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ ከሕዝቡ በደረሰበት ተቃውሞና ግፊት ...

Read More »

ዶክተር አብይ አሕመድ የኦሕዴድ ሊቀመንበር ሆኑ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 15/2010) የኦሕዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዶክተር አብይ አሕመድን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ። አቶ ለማ መገርሳን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ ከፓርቲ ሃላፊነታቸው ዝቅ አድርጓቸዋል። የዶክተር አብይ አህመድ በኦሕዴድ ሊቀመንበርነት መመረጥ ምናልባትም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በእጩነት እንዲቀርቡ ያስችላቸዋል። ዶክተር አብይ አህመድ የፓርላማ አባል በመሆናቸው ኦሕዴድ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ የመረጠው ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እጩ አድርጎ ለማቅረብ እንደሆነ የፖለቲካ ምሁራን ይናገራሉ።በአሁኑ የኦሕዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ...

Read More »

በደቡብ አፍሪካ 5 ፖሊሶች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 14 /2010) መሳሪያ ያነገቡና የተደራጁ ታጣቂዎች ዛሬ ማለዳ የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ጣቢያን በመውረር መኮንኖችን ጨምሮ 5 ፖሊሶችን መግደላቸው ታወቀ።   የደቡብ አፍሪካ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው በምሥራቃዊ ኬፕ ግዛት በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ዛሬ በደረሰው በዚህ ጥቃት ሦስቱ ፖሊሶች ወዲያውኑ መሞታቸው ታውቋል። ሁለቱ ፖሊሶች ደግሞ ታግተው ከተወሠዱ በኃላ 4 ማይል ርቀት ላይ አስከሬናቸው ተገኝቷል፡፡ አላማቸውና ማንነታቸው ያልታወቀው ታጣቂዎች ከፖሊስ ጣቢያው 10 ጠመንጃዎችን እንደሁም ...

Read More »

ኢትዮጵያ ከቱሪዝም ዘርፍ አግኝቻለሁ ያለችው ገቢ ውሸት ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 14 /2010) የዓለም የኢኮኖሚክስ ፎርም የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ባለፉት ስድስት ወራት ከቱሪዝም ዘርፍ ከ1.8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አግኝቻለሁ በማለት ያወጣውን የውሸት ሪፖርት ውድቅ አደርገው። ፎርሙ ከዘርፉ የተገኘው 440 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው ብሏል። በሌላ በኩል ወደተለያዩ አካባቢዎች የተጓዙ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ጉዟቸው መስተጓጎሉንና በመከላከያ ሰራዊት አጃቢነት ወደ ሐዋሳና አርባምንጭ ተወስደው ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውንና ሌሎችም ጉዟቸውን እየሰረዙ መሆናቸውም ...

Read More »

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠየቁ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 14/2010) በኢትዮጵያ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተመለከተ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ያሰሙትን ተቃውሞ በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጡ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጠየቀ። በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሚስተር ማይክ ሬነር ከትላንት በስቲያ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተጠርተው ማብራሪያ መጠየቃቸውን የውስጥ ምንጮችን በመጥቀስ የወጣው ሪፖርት አመልክቷል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መታወጁን ተከትሎ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሬይነር ወዲያውኑ ባወጡት መግለጫ የአዋጁን መውጣት ...

Read More »

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈጽም መመሪያ ወጣ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 14/2010) ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያስፈጽም መመሪያ መውጣቱን የመንግስትና የፓርቲ መገናኛ ብዙሃን ገለጹ። የአውሮፓ ህብረት፣ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ፣የብሪታኒያና የጀርመን መንግስታት የተቃወሙትን ይህንን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተመለከተ የወጣው ዝርዝር መመሪያ የአደባባይ ሰልፍና የአዳራሽ ስብሰባን ጭምር ከልክሏል። ማናቸውም ወገን ባለስልጣናት ጭምር በጸጥታ ጉዳይ ላይ መግለጫ ለመስጠት ኮማንድ ፖስቱን ማስፈቀድ እንዳለባቸውም አሳስቧል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈጽመው መመሪያ ላይ ...

Read More »

በጉራጌ ዞን የተጀመረው አድማ ለጊዜው መቋረጡ ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 14/2010) በጉራጌ ዞን የተጀመረው አድማ እንዲቆም ማድረጉን ዘርማ አስታወቀ። በዞኑ የሚካሄደውን ትግል የሚያስተባብረው የጉራጌ ወጣቶች ስብስብ ዘርማ ለአንድ ሳምንት ሲካሄድ የቆየውን የስራ ማቆም አድማ ዛሬ እንዲቆም ያደረገው ለቀጣዩ ትግል ተጠናክሮ ለመውጣት ነው ብሏል። በሁሉም የጉራጌ ወረዳዎች የሚደረግ አድማና ተቃውሞ ለማዘጋጀት በማቀድ ላይ መሆኑንም ለኢሳት በደረሰው መረጃ ላይ ተመልክቷል። ከዛሬ ጀምሮ ስራ ያቆሙ የንግድ ቦታዎችና ተሽከርካሪዎች ወደ እንቅስቃሴ እንዲገቡ ...

Read More »

በአማራ ክልል የተጠራው አድማ እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 14/2010) በአማራ ክልል የተጠራው የስራ ማቆምና በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ዛሬም መካሄዱ ተገለጸ። በተለይ በጎንደር አድማው ቀጥሎ የዋለ ሲሆን በባህርዳርም በአብዛኛው የከተማው ክፍል ሱቆችና መደብሮች ተዘግተው መዋላቸው ታውቋል። አስቸኳይ አዋጁን በመጣስ የተጠራውና ለሶስት ቀናት እየተካሄደ ያለው በቤት ውስጥ የመቀመጥና የስራ ማቆም አድማ በተለይ በጎንደርና በባህርዳር በስፋት ተካሄዶ በተቀመጠው ግዜ ሰሌዳ ዛሬ ማምሻውን ተጠናቋል። በጎንደር እንደባለፉት ሁለት ቀናት ሱቆች ...

Read More »

በጎንደር የስራ ማቆም አድማው ለ3ኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ

በጎንደር የስራ ማቆም አድማው ለ3ኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ (ኢሳት ዜና የካቲት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) በአማራ ክልል የተጠራውን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ የጎንደር ከተማ ህዝብ አድማውን ለ3ኛ ቀን ሲያካሂድ ውሎአል። ከፍተና ቁጥር ያላቸው ወታደሮች በከተማዋ እየተንቀሳቀሱ የስነ ልቦና ጫና ለመፍጠር ሙከራ ቢያደርጉም፣ ነጋዴዎች በአቋማቸው በመጽናት የመጨረሻውን ቀን የአድማ ጥሪ ተግባራዊ አድርገዋል። አድማውን አስተባብረዋል የተባሉ አንዳንድ ወጣቶች መታሰራቸው ታውቋል። በባህርዳር ከተማ ...

Read More »