(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 14/2010) የአማራ ክልል የሕዝብ ቁጥር እድገት እጅግ አዝጋሚ መሆኑን በኢትዮጵያው አገዛዝና በአለም አቀፍ ለጋሾች የቀረበ አንድ ሰነድ አመለከተ። በዚህ ሰነድ መሰረት በመጪው የሕዝብ ቆጠራ ከዚህ ቀደም ከነበረው በተጨማሪ 3 ሚሊየን የአማራ ህዝብ ሊጠፋ እንደሚችል ተገምቷል። በሰነዱ እንደተመለከተው ለምግብ እጥረት የተጋለጡትን ለመለየት በተካሄደ የሕዝብ ቁጥር ትንበያ ጥናት የአማራ ክልል ነዋሪዎች 20 ነጥብ 5 ሚሊየን ብቻ ናቸው። የኦሮሚያ ክልል ሕዝብ ...
Read More »Author Archives: Central
የስደተኞች ቁጥር ባለፈው ዓመት ብቻ ከ5ሺህ በላይ ነበር ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 13/2010)ወደ አውሮፓ ሳይሻገሩ ባህር ላይ የሰመጡ ስደተኞች ቁጥር ባለፈው ዓመት ብቻ ከ5ሺህ በላይ እንደነበር ተዘገበ። ከወራት በፊት አንድ የጀርመን ጋዜጣ ባውጣው ዘገባ ከ33ሺህ የሚበልጡ ሟቾችን ዝርዝር ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። ዴር ታግ ኢስፒግል የተባለው የጀርመን ጋዜጣ በቅርቡ ይፋ እንዳደረገው መረጃ ከሆነ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1993 ወዲህ ባለው ጊዜ ብቻ 33ሺ 293 ስደተኞች ወደ አውሮፓ ሊሻገሩ ሲሉ ባህር ውስጥ ሰምጠው ...
Read More »የሕወሃት አገዛዝ የ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር እርዳታ ጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 13/2010) በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ ለእለት የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ የ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር እርዳታ መጠየቁ ተነገረ። እርዳታው የተጠየቀው 8 ሚሊየን ለሚጠጉ የድርቅ ተጎጂዎች ድጋፍ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት አስታውቋል። በግጭትና በድርቅ ከተጎዱ ኢትዮጵያውያን መካከል 2 ነጥብ 4 ሚሊየን የሚሆኑት አርብቶ አደሮች ናቸው ተብሏል። በኢትዮጵያ ባለፉት 3 አመታት ከተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስ ባሻገር በድርቅ ሳቢያ የተጠቁት 8 ሚሊየን ያህል ናቸው። ፖለቲካዊ ...
Read More »ከፍተኛ የመድሃኒት እጥረት ተከሰተ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 13/2010)በኢትዮጵያ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያ ከፍተኛ የመድሃኒት እጥረት በመከሰቱ ሕሙማን ሕይወታቸው በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ። አቅራቢዎችም ሆነ የጤና ተቋማት በመድሃኒት እጥረት ምክንያት አገልግሎት ለመስጠት መቸገራቸውን አስታውቀዋል። በተለይም የስኳርና የልብ ሕሙማን ሕይወታቸው አደገኛ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል። በኢትዮጵያ ከ330 በላይ መድሃኒት አስመጪዎች ቢገኙም በውጭ ምንዛሪ መታጣት ምክንያት ስራቸውን በአግባቡ እየሰሩ አይደሉም። በዚሁም ሳቢያ የመንግስትም ሆነ የግል መድሃኒት ቤቶች ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋረጠ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 13/2010)በኦሮሚያ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን የክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘገበ። የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ በዩኒቨርስቲዎች እንዲሁም በራሱ በኦሮሚያ ክልል መገናኛ ብዙሃን ላይ ተጽእኖ ማድረጉም ተመልክቷል። ኢንተርኔት ፍለጋ ከአዳማ አዲስ አበባ የሚመላለሱ ግለሰቦችም ቅሬታቸውን ገልጸዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ ከፍተኛ የሰራዊት ሃይል የተሰማራበት የኦሮሚያ ክልል ከሌሎች ክልሎች በተለየ የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠበት ምክንያት አልታወቀም። የኦሮሚያ ክልል ቴሌቪዥን ጣቢያ ኦ ቢ ኤን እንደዘገበውም ...
Read More »የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን የተቃወሙ የኦህዴድ ተመራጮች ከፓርላማ እንዲባረሩ ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 13 /2010) የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴን ስብሰባ ተከትሎ ማክሰኞ በተጀመረው የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን የተቃወሙ የኦህዴድ ተመራጮች ከአባልነት እንዲሁም ከፓርላማ እንዲባረሩ ህወሓት ጠየቀ። በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ከተወሰነው ውጭ የቀረበው ይህ አጀንዳ ተቃውሞ ገጥሞታል። የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አመራር አባላት በተጨማሪም በአቶ ለማ መገርሳ እና በዶ/ር አብይ አህመድ ላይ የተለያዩ ክሶች ማቅረባቸውም ተሰምቷል። እነርሱም ጠንካራ ምላሽ ...
Read More »በሶማሌ ክልል ከሚገኙ 16 የጉምሩክ ጣቢያዎች 38 ሃላፊዎች ስራ እንዲያቆሙ ታዘዙ 34 ቱ የትግራይ ብሄር ተወላጅና የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው ናቸው።
በሶማሌ ክልል ከሚገኙ 16 የጉምሩክ ጣቢያዎች 38 ሃላፊዎች ስራ እንዲያቆሙ ታዘዙ 34 ቱ የትግራይ ብሄር ተወላጅና የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው ናቸው። (ኢሳት ዜና ማጋቢት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) ምንጮች እንደገለጹት እነዚህ የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው አዛዦች ከመከላከያ በጡረታ ከተገለሉ በሁዋላ ያለ ትምህርት ደረጃቸው በትዕዛዝ ብቻ በመላ አገሪቱ ባሉ የጉሙሩክ መስሪያ ቤቶች ተቀጥረው ላለፉት 8 ዓመታት ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ሲመዘብሩ ቆይተዋል። ዛሬ የትምህርት ...
Read More »በሰሜን ወሎ ሮቢት ከተማ ላይ አንድ አውቶቡስ በድንጋይ ተመታ
በሰሜን ወሎ ሮቢት ከተማ ላይ አንድ አውቶቡስ በድንጋይ ተመታ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ዛሬ ጠዋት ከአዲስ አበባ የተነሳ ስካይ ባስ በሚል የሚጠራ የመንገደኞች ማመላለሻ አውቶቢስ ሮቢት ከተማ ላይ በድንጋይ ተመትቶ የሚከናው መስታውት መሰባባሩን ገልጸዋል። ወጣቶቹ ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ በተሳፋሪዎች ላይ ጉዳት ይድረስ አይድረስ የታወቀ ነገር የለም። ጥቃቱ እንደተሰነዘረ ከቆቦ የተነሱ ወታደሮች ወዲያውኑ አካባቢውን ...
Read More »ወጣት አወቀ አባተ ለቀናት በገመድ ተንጠልጥሎ ሲገረፍ መቆየቱን ተናገረ
ወጣት አወቀ አባተ ለቀናት በገመድ ተንጠልጥሎ ሲገረፍ መቆየቱን ተናገረ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) የመኢአድ የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው ወጣት አወቀ አባተ፣ በጎንደር ሲካሄድ የነበረውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ትመራለህ ተብሎ በ2008 ዓም ከተያዘ በሁዋላ፣ ያልሰጠውን ቃል እንደሰጠ ተደርጎ እንዲፈርም ለማስገደድ ለ4 ቀናት ያክል እጆቹና እግሮቹ ታስረው ሲደበደብ መቆየቱን ተናግሯል። በድብደባው ብዛት በጥፍሮቹ ደም ይፈሰው እንደነበር ...
Read More »ተመድ 10 ሺ ለሚሆኑ ከሞያሌ ከተማ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ
ተመድ 10 ሺ ለሚሆኑ ከሞያሌ ከተማ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 12 ቀን 2010 ዓ/ም) ራሱን ኮማንድ ፖስት በሚል የሚጠራው ወታደራዊ እዝ በበኩሉ ተፈናቃዮች እየተመለሱ ነው ብሎአል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽነር ከኬንያ ባወጣው መረጃ ከኢትዮጵያዋ የሞያሌ ከተማ ለተፈናቀሉ 10 ሺ ለሚሆኑ ዜጎች ዛሬ የቤትና የምግብ ማብሰያ እቃዎችን ሲያድል መዋሉን ገልጿል። ወታደራዊ እዙ ባወጣው መግለጫ ደግሞ ...
Read More »