(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 21/2010) ባለፈው እሁድ እንደገና ተይዘው ከታሰሩት ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ውስጥ አንዱ የሆነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታሞ ሆስፒታል መግባቱ ታወቀ። የአሜሪካው የጸሃፊያን ተቋም ፔን አሜሪካም እስራቱን በማውገዝ እነ እስክንድር ነጋ ይፈቱ ሲል ጥሪውን አቅርቧል። እስክንድር ነጋን በመጥቀስ ፔን አሜሪካ እንደገለጸው 5 ሜትር በ8 ሜትር ስፋት ባለው እስር ቤት ውስጥ 200 ሰዎች ታጭቀው በአስከፊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። ባለፈው እሁድ መጋቢት 16/2010 ...
Read More »Author Archives: Central
ዶክተር አብይ አህመድ የተመረጡት በመራራና እልህ አስጨራሽ ትግል ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 21/2010)ዶክተር አብይ አህመድ የኢሕአዴግ ሊቀመንበርነትን ያገኙት በመራራና እልህ አስጨራሽ ትግል ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ ገለጹ። አቶ ለማ ኦ ቢ ኤን ከተባለው የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አዲሱ የኢሕአዴግ አመራር ዝም ብሎ የተገኘ ሳይሆን በጠንካራና ሰፊ ትግል ነው ብለዋል። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ኦህዴድ የፌደራል ስርአቱን የመምራት ዕድል በማግኘቱ ድርብ ሃላፊነት ተሰጥቶታል ...
Read More »አርበኞች ግንቦት ሰባትና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሀይል ንቅናቄ በከፍተኛ ሁኔታ በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸው ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 21/2010) አርበኞች ግንቦት ሰባትና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሀይል ንቅናቄ በአማራ ክልል ወጣቶችን በማደራጀትና በማሰልጠን በከፍተኛ ሁኔታ በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን አንድ የኮማንድ ፖስት ሰነድ አመለከተ። ለኢሳት የደረሰውና በጎንደር የኮማንድ ፖስት የተዘጋጀው ሰነድ ላይ አርበኞች ግንቦት ሰባትና አዴሀን ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለማፍረስ እየተረባረቡ መሆናቸው ተገልጿል። በጎንደር ከተማ በስድስቱ ክፍለከተሞችና በጎንደር ዩኒቨርስቲ በተዘጋጀው የኮማንድ ፖስቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መድረክ ላይ የቀረበው ሰነድ ...
Read More »በሞያሌ ከተማ ስለተገደሉት ዜጎች የሚያጣራው ቡድን የማጣራት ተልዕኮውን እንዲያቋርጥ ታዘዘ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 21/2010)በመከላከያ ሰራዊት አባላት በሞያሌ ከተማ ስለተገደሉት ዜጎች እንዲያጣራ የተሰየመውና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈጻጸም የሚከታተለው መርማሪ ቡድን የማጣራት ተልዕኮውን እንዲያቋርጥ ታዘዘ። በኢትዮጵያ ፓርላማ የተቋቋመው የስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቡድን ከመጋቢት 16 እስከ መጋቢት 24 ድረስ ወደ ሞያሌ ተጉዞ ምርመራ የማካሄድ እቅድ ነበረው። ዋዜማ የቡድኑን አባል ጠቅሶ እንደዘገበው መርማሪ ቦርድ “ከበላይ የመጣ ትዕዛዝ” ነው በሚል ተልዕኳቸውን አቋርጠው እንዲመለሱ ተደርጓል። አስራሁለት ...
Read More »የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተጠራ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 20/2010) እነእስክንድር ነጋ እንዲፈቱ ግፊት ለማድረግ የታሰበ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ለነገ ተጠራ። በሀገር ቤትና በውጭ የሚገኙ አክቲቪስቶች ያዘጋጁት የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ባለፈው ዕሁድ የታሰሩት ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪዎችን በተመለከተ ትኩረት እንዲያገኙና በአገዛዙ ላይ ጫና በመፍጠር እንዲፈቱ ለማድረግ እንደሆነ ተገልጿል። ኮከብ የሌለበትን ሰንደቅ ዓላማ ይዛችኋል በሚል በፖሊስ የታሰሩት እነእስክንድር ነጋ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ በኮማንድ ፖስቱ የሚፈለጉ እንደሆነም መረጃዎች ...
Read More »የኢትዮጵያ ፓርላማ የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሰይም ነው
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት20 /2010)የኢትዮጵያ ፓርላማ በመጭው ሰኞ በሚያካሂደው ስብሰባ የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሰይም ታወቀ። በዚሁም መሰረት ኢህአዴግ የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ የሰየማቸው ዶክተር አብይ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ይሾማሉ። የዶክተር አብይ አህመድ የጠቅላይ ሚኒስትርነት የፓርላማ ሹመት በመጭው ቅዳሜ ይካሄዳል ተብሎ የሕወሃት ንብረት በሆነው ፋና ሚዲያ ከተገለጸ በኋላ እንደገና ለሰኞ መቀየሩ ተገልጿል። ፓርላማው በመጭው ሰኞ በሚያካሂደው ስብሰባ ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ስልጣናቸውን ...
Read More »የግብጹ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ በድጋሚ የማሸነፍ እድላቸውን አረጋገጡ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 29/2010) የግብጹ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ በሃገሪቱ የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በድጋሚ የማሸነፍ እድላቸውን ማረጋገጣቸው ታወቀ። ጠንካራ የሚባሉት ተቃዋሚዎች እራሳቸውን ከምርጫ ማግለላቸውን ተከትሎም በተቃዋሚዎች ዘንድ መራጮች ድምጽ እንዳይሰጡ ጥሪ መደረጉን ቢቢሲ በዘገባው ላይ አስፍሯል። ለ 3 ቀናት በተካሄደው በዚህ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተመዝግበው ድምጽ ያልሰጡ መራጮች ከ 500 – 28 ፖውንድ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተብሏል። የሀገሪቱ ህግ ለምርጫ የደረሰ ማንኛውንም ...
Read More »ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን አማካሪ ቦርድ አባል ሆነው ተሾሙ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 20/2010) ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣አቶ አብዱ አሊ ሂጅራን ጨምሮ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን አማካሪ ቦርድ አባል ሆነው ተሾሙ። ግለሰቦቹ የተመረጡበት መንገድ አነጋጋሪ ሆኗል። ለአዲስ አበባና ለኦሮሚያ የተዘጋጀው የተቀናጀ ማስተር ፕላን በሕዝባዊ እምቢተኝነት የተሰረዘ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ይህንንም ተከትሎ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ከፍተኛ እልህ የተጋቡና ጥቅማችን ሊቀርብን ይችላል ያሉት የሕወሃት ነባር ባለስልጣናት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በተናጠል እንዲታወጅ ...
Read More »ዶክተር አብይ ደፋር የለውጥ ርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ ቀረበ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 20/2010) “ደፋር የለውጥ ርምጃዎችን ውሰድ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ከጎንህ ነው” የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት ሚስተር ኽርማን ኮኽን ዶክተር አብይ ደፋር የለውጥ ርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ አቀረቡ። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከጎናቸው እንደሆነም አረጋግጠዋል። የአፍሪካ ሕብረት የወቅቱ ሊቀመንበር እና የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜም በአፍሪካ ሕብረት እና በአፍሪካ መሪዎች ስም የደስታ መግለጫ አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያም በአፍሪካ አህጉር ታሪካዊ እና ...
Read More »የዶ/ር አብይ የኢህአዴግ ሊ/መንበር ሆኖ በመመረጡ ደስታቸውን የገለጹ የጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተደበደቡ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) የኦህዴዱ ሊ/መንበር ዶ/ር አብይ አህመድ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ይፋ እንደሆነ ደስታቸውን በመግለጽ ላይ የነበሩ የጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ በአጋዚ ወታደሮች ከፉኛ መደብደባቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ትናንት ፣ ረቡዕ፣ በኢንጂነሪንግ ትምህርት ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች፣በድስታ ሲጨፍሩ ኮማንድ ፖስት ሳታስፈቅዱ ለምን ጨፈራችሁ በሚል ...
Read More »