(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 11/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዛሬ በፓርላማ ያቀረቧቸው 10 ሚኒስትሮች ሹመት ጸድቋል። የነበሩት ሚኒስትሮች በከፊል ሲባረሩ ፣የተወሰኑት ባሉበት ቀጥለዋል። የቀሩትም የሚኒስትር መስሪያ ቤት ቀይረው በሃላፊነት እንዲቀጥሉ ተወስኗል። በኢሕአዴግ የስልጣን ዘመን የሚኒስትሮቹ የትውልድ ቦታ እንጂ ብሔራቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ያልተገለጸበት ካቢኔ ብዙ አዲስ ፊት አልታየበትም ተብሏል። ከስልጣናቸው የተነሱት ሚኒስትሮች የእንስሳትና አሳ ሀባት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ፣የእርሻና የተፈጥሮ ሃብት ሚኒስትር ዶክተር ...
Read More »Author Archives: Central
የጠ/ሚኒስትሩ አዲስ ሹመት ህዝቡን እያነጋገረ ነው
የጠ/ሚኒስትሩ አዲስ ሹመት ህዝቡን እያነጋገረ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 11 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢትዮጵያ የተነሳውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ ወደ ስልጣን የመጡት ዶ/ር አብይ አህመድ አዳዲስ ሚንስትሮችና ምክትል ሚኒስትሮችን የሾሙ ቢሆንም፣ ሹመቱ ህዝቡን እያነጋገረ ነው። ነባሩ አመራር ተመልሶ መምጣቱን የሚያነሱ ወገኖች የመኖራቸውን ያክል ህወሃትን በኦህዴድ የመተካት እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው የሚል ትችት የሚሰነዝሩ ሰዎችም አሉ። አዲሱ ጠ/ሚኒስትር 6 ነባር ሚኒስትሮችን ወደ ...
Read More »በአሰላ ከተማ የኮማንድ ፖስት አባላት ነን ያሉ ሰዎች እናትና ልጅ ገደሉ
በአሰላ ከተማ የኮማንድ ፖስት አባላት ነን ያሉ ሰዎች እናትና ልጅ ገደሉ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 11 ቀን 2010 ዓ/ም) ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ በአሰላ ከተማ የኮማንድ ፖስት አባላት አንድ የ15 አመት ልጅ እና እናቱን መግደላቸውን እንዲሁም 4 ሴቶችን ማቁሰላቸውን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። ወታደሮቹ በቀበሌ 10 ውስጥ ነዋሪ የሆኑትን የአቶ አህመድ በሽሬን ቤት ሰብረው በመግባት የ15 አመቱን እስማኤል አህመድን እና ...
Read More »ለምግብ እጥረት ተጠቂ ለሆኑ የኢትዮጵያ አዛውንቶች ቅድሚያ እንዲሰጥ ሲል ተመድ አሳሰበ
ለምግብ እጥረት ተጠቂ ለሆኑ የኢትዮጵያ አዛውንቶች ቅድሚያ እንዲሰጥ ሲል ተመድ አሳሰበ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 11 ቀን 2010 ዓ/ም) የኢትዮጵያ መንግስትና ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ለጋሾች በአገሪቱ ላሉ የተመጣጠነ የምግብ እጥረት ተጠቂ ለሆኑ አዛውንቶች ቅድሚያ በመስጠት ሕይወታቸውን ሊታደጓቸው ይገባል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ቀውስ ቡድን ማሳሰቢያ ሰጠ። በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የሚገኙ አገራት የስጊ የድርቅ አደጋ አንዣቧል። ከፍተኛውን የርሃብ አደጋ ካንዣበባቸው አገራት ...
Read More »የሲ አይ ኤ ዳይሬክተር ከሰሜን ኮሪያ ፕሬዝዳንት ጋር በሚስጥር መገናኘታቸው ታወቀ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 10/2010) የአሜሪካው የስለላ ድርጅት ሲ አይ ኤ ዳይሬክተር ማይክ ፖምፒዮ ከሰሜን ኮሪያ ፕሬዝዳንት ጋር በሚስጥር መገናኘታቸው ታወቀ። ግንኙነቱ እውነት መሆኑን ያረጋገጡት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መልካም ግንኙነት ተመስርቷል ሲሉ በቲውተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም የ41ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባለቤትና የ43ኛው ፕሬዝዳንት እናት ባርባራ ቡሽ በ92 አመታቸው ከዚህ አለም ተለይተዋል። በቅርቡ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ታጭተው የሴኔቱን ውሳኔ በመጠባበቅ ...
Read More »ድምጻዊ ታምራት ደስታ ከዚህ አለም በሞት ተለየ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 10/2010)ታዋቂው ድምጻዊ ታምራት ደስታ ከዚህ አለም በሞት ተለየ። ድምጻዊ ታምራት በድንገተኛ አደጋ ሕይወቱ ማለፉን የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ታምራት ደስታ በ 90 ዎቹ ወደ ሙዚቃው ዓለም ብቅ ብለው እውቅና ካገኙ ድምጻውያን ውስጥ አንዱ ሲሆን፣“እኛን ነው ማየት”፣ “ሃኪሜ ነሽ”፣ከዛ ሰፈር ካንች አይበልጥምና፣ሊጀማምረኝ ነው በሚሉና ሌሎችም የሙዚቃ ስራዎቹ ይታወቃል። ድምጻዊ ታምራት መኪና እያሽከረከረ ሕመም ሲሰማው ወደ አንድ ክሊኒክ ቢያመራም ...
Read More »ነገ አዲስ አፈ ጉባኤ ሊመረጥ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 10/2010) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ አዲስ አፈ ጉባኤ ሊመርጥ ነው። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በበኩላቸው ነገ አዲስ ካቢኔ አቅርበው በፓርላማ ያጸድቃሉ ተብሏል። በኦሮሚያም የስልጣን ሹም ሽር ተካሂዶ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ ከፌደራል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ተነስተው የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሹመዋል ። ዶ/ር ነገሪን በመተካት አቶ መለስ አለም እንደሚተኳቸው ለአገዛዙ ቅርበት ያላቸው ሚዲያዎች ዘግበዋል። የፓርላማ ...
Read More »በሞያሌ ውጥረት መንገሱ ተሰማ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 10/2010)በሞያሌ በቦምብ ጥቃት 3 ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት መንገሱ ተነገረ። በሞያሌ ዙሪያ ባሉ የኦሮሚያና የሶማሌ ድንበር አዋሳኝ ጫካዎች ሕዝቡ መሳሪያ እየያዘ መግባቱን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች እንቅስቃሴ በመከላከያና በፌደራል ፖሊስ አባላት የመገደብ ስር መጀመሩንም ለማወቅ ተችሏል። በሞያሌ ዙሪያ ባሉ ቀበሌዎች ህዝቡ እየተጠራራ እርስ በርሱ ሲመካከርና ለበቀል መሳሪያ ሲሰበሰብ እንደዋለና ከሞያሌ በ40 እና 65 ኪሎ ሜትር ...
Read More »በጎጂና በጌዲዮ ብሔረሰብ መካከል በቀጠለው ግጭት 11 ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 10/2010) በጎጂና በጊዲዮ ብሔረሰብ መሀል የተፈጠረው ግጭት ቀጥሎ ትላንት 6 ህጻናትን ጨምሮ 11 ሰዎች መገደላቸው ታወቀ። የተሰደዱ ሰዎችም ወደ 100 ሺህ መጠጋቱ እየተነገረ ነው። በበጉጂ ዞን በሚኖሩ የጌዲዮ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እንዲቆም በሰሜን አሜሪካ የጌዲዮ ማህበረሰብ አባላት ጠይቀዋል። አባላቱ ለኢሳት በላኩት መግለጫ ላይ እንደገለጹት ለዘመናት በጋራ ተከባብረው ተዋልደውና ቤተሰብ ሆነው በኖሩ የሁለቱ ብሔረሰቦች መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ...
Read More »በጉጂ እና በጌዲዮ ብሄረሰቦች መካከል የተጀመረው ግጭት ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል
በጉጂ እና በጌዲዮ ብሄረሰቦች መካከል የተጀመረው ግጭት ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 10 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚገልጹት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ለስደት የዳረገው የሁለቱ ብሄረሰቦቸ ግጭት ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል። በተለይ ባንቆ ጎትቲ 2 የቡና ሳይቶች እንዲሁም በጨልጨል አንድ የቡና ሳይት ሙሉ በሙሉ የወደሙ ሲሆን፣ በቃርጫ ደግሞ ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ ከተሰደዱ ህጻናት መካከል ደግሞ የተወሰኑ ህጻናት መሞታቸው ታውቋል። ቆስለው ...
Read More »