በኢትዮ ሶማሊ ለሚካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ ህዝቡ ድጋፉን እንዲሰጥ ተጠየቀ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 18 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ተወላጆች እንደገለጹት በክልሉ የሚካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ እየቀጠለ በመሆኑ ከክልሉ ተወላጆች ውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ጠይቀዋል። ህዝባዊ እንቅስቃሴው ከተጀመረ በሁዋላ በርካታ የክልሉ ተወላጆች ተይዘው ታስረዋል። የአብዲ ኢሌን ጭካኔ የተሞላበት አገዛዝ ለመቃወም በውጭ አገር የተቋቋመው ዱል ሚዲድ አባላት ናቸው የተባሉ ወላጆች እና ቤተሰቦች እየተያዙ ...
Read More »Author Archives: Central
የአምቦ ተማሪዎች ባነሱት ተቃውሞ ተማሪዎች ወደ ሆስፒታል ተወሰዱ
የአምቦ ተማሪዎች ባነሱት ተቃውሞ ተማሪዎች ወደ ሆስፒታል ተወሰዱ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 18 ቀን 2010 ዓ/ም)ተማሪዎቹ በእስር ላይ የሚገኙ ጓደኞቻቸው እንዲፈቱ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ ወታደሮች አስለቃሽ ጥይት በመተኮስ በትነዋቸዋል። በተኩሱ አንድ የጎንደር እና ሁለት የአምቦ ተወላጆች ተጎድተዋል። አንደኛው ተማሪ ከሆስፒታል የወጣ ሲሆን፣ ሁለቱ ግን አሁንም በህክምና ላይ ናቸው። ተማሪዎች ጥያቄያቸው ካልተመሰለ በስተቀር ተቃውሞአቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። አምቦ በኢትዮጵያ ለሚካሄደው የለውጥ እንቅስቃሴ ...
Read More »የዳባት ከተማ ነዋሪዎች የወልቃይት ጉዳይ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ ጭምር ነው አሉ
የዳባት ከተማ ነዋሪዎች የወልቃይት ጉዳይ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ ጭምር ነው አሉ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 18 ቀን 2010 ዓ/ም) “የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት የአማራ ድንበር ተከዜ ነው። የድንበሩ ጉዳይ ፖለቲካዊ ውሳኔ ሊሰጠው ይገባል” ብለዋል። የዳባት ህዝብ ከመንግስት አንዳች ጥቅም አግኝቶ አያውቅም፡፡ለሃያ ሰባት ዓመታት ያለአንዳች እገዛ ህብረተሰቡ እርስ በእርሱ እየተረዳዳና በአካባው ካሉ ህዝቦች ጋር እየተሸማገለ የሚኖር እንጅ በገዥው መንግስት ፍትህ አግኝቶ እንደማያውቅ ነዋሪዎች ...
Read More »በባቡር ፕሮጀክት ሥም የመስኖ መሬታቸውን ካለተመጣጣኝ ክፍያ መነጠቃቸውን የተሁለደሬ ወረዳ የጎበያ 012 ቀበሌ አርሶ አደሮች ተቃወሙ
በባቡር ፕሮጀክት ሥም የመስኖ መሬታቸውን ካለተመጣጣኝ ክፍያ መነጠቃቸውን የተሁለደሬ ወረዳ የጎበያ 012 ቀበሌ አርሶ አደሮች ተቃወሙ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 18 ቀን 2010 ዓ/ም) ነዋሪነታቸው በደቡብ ወሎ ዞን በተውለደሬ ወረዳ 012 ቀበሌ ልዩ ቦታው ጎበያ ገ/ማኅበር በመባል በሚጠራው ነዋሪ የሆኑ አርሶ አደሮች በመስኖ የሚለማ መሬታቸውን በባቡር መንገድ ዝርጋታ ምክንያት በርካሽ ዋጋ እንዲለቁ መደረጋቸውን 34 አርሶ አደሮችና ቤተሰቦቻቸው ተቃውሞ አሰምተዋል። አርሶ አደሮቹ ...
Read More »ሰራተኞች ደቡብ ሱዳን ውስጥ የደረሱበት ጠፋ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 18/2010) በሰብአዊ እርዳታ ላይ የተሰማሩ 10 ሰራተኞች ደቡብ ሱዳን ውስጥ የደረሱበት ጠፋ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዳስታወቀው እነዚህ በሰብአዊ አድራጎት ስራ ላይ የተሰማሩት ግለሰቦች የተሰወሩት ትላንት ረቡዕ መሆኑ ታውቋል። ሁሉም የደቡብ ሱዳን ዜጎች መሆናቸውም ተመልክቷል። በተባበሩት መንግስታት የደቡብ ሱዳን የሰብአዊ እርዳታ ጉዳዮች አስተባባሪ አለይን ኖውዴሁ ለመገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት የተባበሩት መንግስታትና ሌሎች የእርዳታ ድርጅት ሰራተኞችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ዪ ከተባለው ...
Read More »የጎበያ አርሶ አደሮች በሃይቅ ከተማ ከፍተኛ ተቃውሞ አሰሙ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 18/2010) በደቡብ ወሎ ዞን በተሁለደሬ ወረዳ የጎበያ አርሶ አደሮች በሃይቅ ከተማ ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰማታቸው ተነገረ። አርሶደሮቹ ተቃውሞውን ያደረጉት የእርሻ ቦታቸው፣ ለባቡር ፕሮጀክት በሚል እጅግ ዝቅተኛ በሆነ የካሳ ዋጋ የተወሰደባቸው ናቸው። በደቡብ ወሎ የጎበያ አካባቢ በወረዳው ከፍተኛ ምርት የሚሠጥ ለም መሬትና ሀይቁን ተከትሎም ምርታማ የመስኖ ግብርና የሚከናወንበት አካባቢ ነው፡፡ በዚሁ አካባቢ የሚገኙ አርሶ አደሮች ታዲያ የእርሻ ቦታቸው ለባቡር ፕሮጀክት ...
Read More »ሽንሌ ዞን የተጀመረው ተቃውሞ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተዛመተ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 18/2010) በሶማሌ ክልል ሽንሌ ዞን የተጀመረው ተቃውሞ ወደ ቀብሪ በያህ፣ ደገሀቡር፣ቀብሪዳሃርና ወደሌሎች አካባቢዎች ተዛምቶ በመካሄድ ላይ መሆኑ ታወቀ። በጅጅጋ ዙሪያ ባሉ መንደሮችም ተቃውሞው ቀጥሏል። በአብዲ ዒሌ የሚታዘዘው የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል አዛውንቶችን ጨምሮ በርካታ ወጣቶችን እያፈነ በመውሰድ ላይ መሆኑንም የኢሳት የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል። የሽንሌ ዞን አስተዳደር የተዘጋ ሲሆን በዞኑ የሚገኙ የአራት ወረዳ መንግስታዊ መዋቅሮችም መወገዳቸው ታውቋል። በአንድ ዞን ...
Read More »የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 18/2010)የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸው ተሰማ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣስ ዛሬ ሃሙስ የተቃውሞ ሰልፍ ያካሄዱት የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በእስር ላይ የሚገኙ ጓደኞቻቸው እንዲለቀቁ ጠይቀዋል። ተማሪዎቹ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በፍጥነት እንዲነሳም ባሰሟቸው መፈክሮች አስተጋብተዋል:: በአምቦ ዩኒቨርስቲ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሰው በመውጣት ለተቃውሞ አደባባይ ባወጡ ተማሪዎች ላይ ፖሊስ አስለቃሽ ጋሽ መበተኑን የአካባቢው ምንጮች ተናግረዋል። ከተቃዋሚ ተማሪዎች መረዳት እንደተቻለው አዋጁ ...
Read More »የሕወሃት አገዛዝ የሰብአዊ መብትን በማክበር ለዜጎች ተስፋ እንዲሰጥ ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 18/2010) የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ዛይድ ራድ አል ሁሴን የኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ መብትን በማክበር ለዜጎች ተስፋ እንዲሰጥ ጠየቁ። ኮሚሽነሩ በኢትዮጵያ ያካሄዱትን ጉብኝት ካጠናቀቁ በኋላ በሰጡት መግለጫ አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አመራር ለሕዝቡ የሰጠውን ተስፋ በመተግበር የሰብአዊ መብቶች ሊጠበቁ ይገባል ብለዋል። በጉብኝታቸውም የፖለቲካ እስረኞች የነበሩ ሰዎችን፣ የሃይማኖት አባቶችንና ባህላዊ መሪዎችን አነጋግረው ሕዝቡ በአዲሱ አስተዳደር የተገቡ ተስፋዎች መክነው ...
Read More »የዚምባቡዌ ፖሊስ አዲስ ሃይል ሊያቋቁም ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 17/2010)የዚምባቡዌ ፖሊስ አዲስ ሃይል ሊያቋቁም መሆኑን አስታወቀ። አዲስ የሚቋቋመው ሃይል ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲም ሆነ ግለሰብ ጾታና ከለርን ሳይለይ ፈጣንና ሙያዊ በሆነ መልኩ ምላሽ የሚሰጥ ሃይል ነው። ይሄ ሃይል ቀደም ሲል የዜጎችን የሰብአዊ መብት በመጣስና የገዢዎችን እድሜ ለማራዘም አላግባብ የሆኑ ድርጊቶችን ይፈጽማል በሚል ሲወገዝበት የቆየውን ስሙን ይቀይረዋል ተብሏል። በዚምባቡዌ ከዚህ ቀደም ከፖሊስ ሃይሉ ጋር በተያያዘ ይነሱ የነበሩ የሰብአዊ መብት ...
Read More »