የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 18/2010)የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸው ተሰማ።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣስ ዛሬ ሃሙስ  የተቃውሞ ሰልፍ ያካሄዱት የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በእስር ላይ የሚገኙ ጓደኞቻቸው እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

ፋይል

ተማሪዎቹ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በፍጥነት እንዲነሳም ባሰሟቸው መፈክሮች አስተጋብተዋል::

በአምቦ ዩኒቨርስቲ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሰው በመውጣት ለተቃውሞ አደባባይ ባወጡ ተማሪዎች ላይ ፖሊስ አስለቃሽ ጋሽ መበተኑን የአካባቢው ምንጮች ተናግረዋል።

ከተቃዋሚ ተማሪዎች መረዳት እንደተቻለው  አዋጁ በፍጥነት እንዲነሳም ጠይቀዋል።

ቀደም ሲል በአስቸኳይ አዋጁ ሰበብ የታሰሩ ተማሪዎች እንዲለቀቁ የጠየቁት ከአምቦ ዩኒቨርስቲ የወጡ ተቃዋሚዎች አደባባይ በመውጣት መፈክር ሲያስተጋቡ ነበር።

በተቃውሞው የአምቦ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተቃውሞውን በመደገፍ እንቅስቃሴ ለማድረግ ሞክረው እንደነበርም የአምቦ ነዋሪዎች መግለጻቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ዘገባዎች እንዳመለከቱት የአምቦ ዩኒቨርስቲ በወታደራዊ እዙ ታጣቂዎች እንደተወረረ ይገኛል።

ተማሪዎቹም ወታደሮች የዩኒቨርስቲውን ግቢ ለቀው እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የአምቦ አካባቢ ዋነኛ የተቃውሞ እንቅስቃሴ መሰረት በመሆኑ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አካባቢውን መጎብኘታቸው ይታወሳል።

በጉብኝታቸውም ለቄሮ እውቅና በመስጠት ለለውጥ ያደረጉትን እንቅስቃሴ ማድነቃቸው አይዘነጋም።