Author Archives: Central

የእንግሊዙ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደስታቸውን ገለጹ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 22/2010) አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር በመለቀቃቸው የእንግሊዙ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደስታቸውን ገለጹ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሪስ ጆንሰን እንዳሉት የአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ለእንግሊዝ መንግስት ቀዳሚ ጉዳይ ሆኖ ከእስር ለማስፈታት ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። እናም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከረጅም እስር በኋላ ተለቆ ከቤተሰቡ ጋር መገናኘቱ ለእንግሊዝ መንግስት ትልቅ ደስታ ነው ብለዋል። በአንዳርጋቸው ጽጌ መለቀቅ በርካታ ሰዎች ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። አቶ አንዳርጋቸው ...

Read More »

“ፍርዱን ተፈጻሚ አድርጉትና ሰው እየሳቀ እንደሚሞት ላሳያችሁ እያልኩ ደህንነቱን ጠይቄያቸዋለሁ” ሲሉ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ተናገሩ

“ፍርዱን ተፈጻሚ አድርጉትና ሰው እየሳቀ እንደሚሞት ላሳያችሁ እያልኩ ደህንነቱን ጠይቄያቸዋለሁ” ሲሉ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ተናገሩ (ኢሳት ዜና ግንቦት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) ዛሬ ከእስር ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው እና ከደጋፊዎቻቸው ጋር የተገናኙት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፣ ደህንነቶች ምርምራ ቢያመደርጉበት ወቅት፣ በእንዲህ አይነት አገር ከምኖር ፍርድ ቤት የወሰነውን የሞት ፍርድ ቤት ፈርዳችሁ እንድትገድሉኝ፣ ዛሬም እዚህ ቁጭ ብዬ የምናገረው ፍርድ ቤት የወሰነውን ውሳኔ በአስቸኳይ ...

Read More »

ከቤንሻንጉል ለተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች እርዳታ ማሰባሰቢያ የሙዚቃ ኮንሰርት ሊዘጋጅ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት21/2010) ከቤንሻንጉል ለተፈናቀሉና በባህርዳር ለሚገኙ የአማራ ተወላጆች እርዳታ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ የሙዚቃ ኮንሰርት ለማዘጋጀት ማቀዳቸውን ታዋቂ ድምጻውያን ገለጹ። አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ፥ አርቲስት ፍቅርአዲስ ነቃ ጥበብ እና አርቲስት አምሳል ምትኬ ተፈናቃዮቹ ወደሚገኙበት ባህርዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በማምራት የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል። በአሜሪካ የሚገኘው አርቲስት መሐሪ ደገፋውም 30 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ለተፈናቃዮቹ ልኮ በአርቲስቶቹ በኩል እንዲደርስ ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል። አርቲስቶቹ በቤተክርስቲያኒቱ ለተጠለሉ ...

Read More »

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋና ጃዋር መሀመድ ላይ ተመስርቶ የነበረው ክስ ተቋረጠ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 21/2010) አቃቤ ሕግ በአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋና ጃዋር መሀመድ ላይ መስርቶት የነበረውን ክስ ማቋረጡ ተነገረ። በሁለት መገናኛ ብዙሃን ማለትም በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ (ኢሳት) እና በኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦ ኤም ኤን)፣ ላይ አቅርቦት የነበረውን ክስም አቃቤሕግ ማንሳቱ ታውቋል። ይሕ በእንዲህ እንዳለ ግን በአርበኞች ግንቦት 7 ስም የተከሰሱ በርካታ ተከሳሾች ክስአሁንም አልተቋረጠም። የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ...

Read More »

በተለያዩ አካባቢዎች በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ70 በላይ ሰዎች ሞቱ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 21/2010) በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ70 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ። በደቡብ የኢትዮጵያ ክፍል በሲዳማና ጋሞጎፋ 32 ሰዎች ሲሞቱ፣ በሶማሌ ክልል ደግሞ የ47 ሰዎች ህይወት ማለፉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በአካባቢዎቹ በጣለው የማያቋርጥ ዝናብ ምክንያት በደረሰ የመሬት መደርመስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ተገልጿል። በሶማሌ ክልል ብቻ በጎርፍ አደጋ ወደ 200ሺህ የሚጠጋ ህዝብ መፈናቁሉም ታውቋል። በስልጤ ዞንም 1ሺህ ...

Read More »

ብረት ያነሱ አርበኞች ስርነቀል ለውጥ እስከሚመጣ ትግላችንን እንቀጥላለን አሉ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 21/2010) በኢትዮጵያ ስርነቀል ለውጥ እስከሚመጣ ትግላቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ብረት ያነሱ አርበኞች ገለጹ። በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል በተለያዩ አካባቢዎች የትጥቅ ትግል በማድረግ በአገዛዙ የተለያዩ ወታደራዊና መንግስታዊ ተቋማት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ላይ የሚገኙት አርበኞች ሰሞኑን በአማራ ክልል መገናኛ ብዙሃን እየቀረበ ያለው ዜና ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ አስተባብለዋል። ሁለት የአርበኛ መሪዎች ወደ አገዛዙ የገቡበት ምክንያት ከጤና ጋር የተያያዘ ነው ያሉት አርበኞች ትግሉን ...

Read More »

በአፋር ሰመራ ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 21/2010)በአፋር ክልል ሰመራ ህዝባዊ ተቃውሞ ተደረገ። የሰመራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችም በአፋር ያለው የመልካም አስተዳደር እጦት በመባባሱ ተቃውሞ በማድረግ ላይ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። እስራትና ማፈናቀል በአፋሮች ላይ እየተጠናከረ መሆኑን በመጥቀስም ህዝቡ ተቃውሞውን ሲያሰማ መዋሉን ለማወቅ ተችሏል። ከሁለት ሳምንት በፊት በአፋር ክልል ሰመራና ሌሎች ከተሞች ህዝባዊ የተቃውሞ ጥሪ የሚያደርግ በራሪ ወረቀት መበተኑን ተከትሎ በሌሎችም አካባቢዎች ተመሳሳይ ተቃውሞ ሊኖር እንደሚችል ነው ...

Read More »

ከአራት ዓመታት በፊት የዓለምአቀፍ ሕግን በሚጻረር መልኩ ከየመን ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ ታግተው የተወሰዱት የነፃነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር እንደተፈቱ በስፋት ቢነገርም ከመንግስት፣ከቤተሰቦቻቸውም ሆነ ከእንግሊዝ ኤምባሲ ዘንድ ማረጋገጥ አልተቻለም።

ከአራት ዓመታት በፊት የዓለምአቀፍ ሕግን በሚጻረር መልኩ ከየመን ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ ታግተው የተወሰዱት የነፃነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር እንደተፈቱ በስፋት ቢነገርም ከመንግስት፣ከቤተሰቦቻቸውም ሆነ ከእንግሊዝ ኤምባሲ ዘንድ ማረጋገጥ አልተቻለም። (ኢሳት ዜና ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በህገወጥ መንገድ ከታገቱበት ጊዜ አንስቶ በሀገር ውስጥም ሆነ በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተቃውሞ ሰልፎችና በተለያዩ መድረኮች ተቃውሟቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል። ከዚህም ባሻገር ...

Read More »

የዘንድሮው ግንቦት 20 ካለፉት 27 ዓመታት በተለየ መልኩ ያለ ፉከራና ቀረርቶ ታስቦ ውሏል።

የዘንድሮው ግንቦት 20 ካለፉት 27 ዓመታት በተለየ መልኩ ያለ ፉከራና ቀረርቶ ታስቦ ውሏል። (ኢሳት ዜና ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) አገዛዙ በየዓመቱ ግንቦት 20 በመጣ ቁጥር ህዝብን በተደጋጋሚ አሰልቺ ፕሮፓጋንዳ ሲያደነቁር የቆዬ ሲሆን ፣ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ስላለፈው ስርዓትም ሆነ ስለ ነጻነት ዕለትነቱ ፕሮፓጋንዳ ሳይነዛ እንዲያልፍ ተደርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም በሰጡት መግለጫ “ዕለቱን የእረፍት እናድርገው” ከማለት ውጭ እስከዛሬ በሹመኞች ሲባል ...

Read More »

በኮሬና ጉጂ ብሄረሰቦች መካከል እየተካሄደ ባለው ግጭት የሰዎች ህይወት እየጠፋ ነው።

በኮሬና ጉጂ ብሄረሰቦች መካከል እየተካሄደ ባለው ግጭት የሰዎች ህይወት እየጠፋ ነው። (ኢሳት ዜና ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) መቋጫ ያልተገኘለት በአማሮ ወረዳ በሚኖሩ የኮሬና አዋሳኝ አካባቢዎች የሚኖሩ ጉጂዎች መካከል ከድንበር ማካለል ጋር በተያያዘ ከ11 ወራት በላይ የወሰደው ደም አፈሳጭ ግጭት ሰሞኑን አገርሽ 6 የኮሬ ብሄረሰብ አባላት ሲገደሉ ከ10 በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። እስካሁን ባለው ግጭት በከሮ በኩል ከ50 ያላነሱ ሰዎች ...

Read More »