በኮሬና ጉጂ ብሄረሰቦች መካከል እየተካሄደ ባለው ግጭት የሰዎች ህይወት እየጠፋ ነው።

በኮሬና ጉጂ ብሄረሰቦች መካከል እየተካሄደ ባለው ግጭት የሰዎች ህይወት እየጠፋ ነው። (ኢሳት ዜና ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) መቋጫ ያልተገኘለት በአማሮ ወረዳ በሚኖሩ የኮሬና አዋሳኝ አካባቢዎች የሚኖሩ ጉጂዎች መካከል ከድንበር ማካለል ጋር በተያያዘ ከ11 ወራት በላይ የወሰደው ደም አፈሳጭ ግጭት ሰሞኑን አገርሽ 6 የኮሬ ብሄረሰብ አባላት ሲገደሉ ከ10 በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። እስካሁን ባለው ግጭት በከሮ በኩል ከ50 ያላነሱ ሰዎች ሲገደሉ ከ100 በላይ ደግሞ ቆስለዋል።
በጉጂ በኩል የሞቱትን ሰዎች ቁጥር ለማወቅ አልተቻለም። በአካባቢው የተሰማሩት የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ አዛዦች ግጭቱን ለማስቆምና የሰዎችን ህይወት ለመታደግ ምንም አይነት እርምጃ ባለመውሰዳቸው የአካባቢው ማህበረሰብ ተስፋ አስቆርጧል። የአገሪቱ መንግስትም ሆነ ሚዲያዎቹ ስለ ግጭቱ አለመዘገባቸው የአካባቢው ማህበረሰብን እያበሳጨ ነው። ከ2 ሺ በላይ ዜጎች እርዳታ አጥተው ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።