Author Archives: Central

በጥቁር አንበሳ የህክምና ዶክተሮች ባለባቸዉ መሰረታዊ የኑሮ ጫና ምክንያት የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ አስጠነቀቁ : ጥያቄያቸዉ እስከ ጥቅምት 15/2004 መልስ እንዲሰጠዉ የጊዜ ገደብ ሰጥተዋል

ኢሳት ዜና:- ከ400 በላይ የሚሆኑት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በማስተማርና የህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የህክምና ዶክተሮች በአገሪቱ ያለዉ የኑሮ ዉድነትና የመኖሪያ ቤት ችግር በህይወታቸዉ ላይ ከፍተኛ ድቀት እያደረሰባቸዉ በመሆኑ መንግስት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸዉ ጠይቀዋል። አዲስ ነገር የመረጃ መረብ አዲስ አድማስ ጋዜጣን በመጥቀስ እንደገለፀዉ የህክምና ባለሙያዎቹ በጥቁር አንበሳ ግቢ ውስጥ ባደረጉት ስብሳባ ጥያቄያቸዉ የፖለቲካ ወይም የዐመፅ ሳይሆን ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ በመሄድ ላይ ...

Read More »

በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች የሰፈነው የመልካም አስተዳደር እጦት በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመጽን ሊቀሰቅስ እንደሚችል የፌዴራል ጉዳዮች ሚንስትር መሥሪያ ቤት ያስጠናው አንድ ጥናት አመለከተ።

ኢሳት ዜና:- ጥናቱ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የሚታየው የመልካም አስተዳደር እጦት ህብረተሰቡን ወደ አመጽ መንገድ እየመራው መሆኑን አመልክቷል። የሙያተኞች ግብረ ኃይል የሕዝብ አደረጃጀትና የደህንነት ጉዳይ በሚል ርእስ ባጠናው ጥናት ሁልቆ መሳፍርት ችግሮችን ዘርዝሯል። በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በምክትል ከንቲባዎች የሚመሩ ከህብረተሰቡ የተውጣጡ የአማካሪዎች ምክር ቤት እንዲቋቋም እና የግምገማና የክትትል ሥራ እንዲሰራ የሚል የመፍትሄ ሀሳብ በጥናቱ ውስጥ ቀርቧል። ከመፍትሄዎች አንዱ ከነዋሪዎች፣ ከምሑራን፣ ነጋዴዎች፣ የሀገር ...

Read More »

ኢሳት የአጭር ሞገድ ሬዲዮ በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ መጀመሩን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ፣

መስከረም 26 2004 ዓ.ም የኢሳት ማኔጅመንት እና መላው የኢሳት ቤተሰቦች የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃ እና ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት አለው በሚል እምነት ከተነሳን አንድ ዓመት ተሻገርን፤ ይህንንም  ከግብ ለማድረስ ማናቸውንም መሰናክል ሰብረን ለማለፍ ባልተቋረጠ ትግል ውስጥ ቀጥለናል። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንዳሳወቅነው የኢትዮጵያ ህዝብ ትክክለኛና ሚዛናዊ መረጃ ማግኘት ተፈጥሮዓዊና  ሰብዓዊ መብቱ ነው። ስልጣን ላይ ያለው የአቶ መለስ መንግስት ይህንን መብት ገፎ የፈለገውንና ...

Read More »

የኢሳትን ወደ ፕሮግራም ሥርጭት መመልስ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ፣

ሰኔ 3፣ 2003 ዓም ከሁለት ወር በላይ በደረሰበት ከፍተኛ የዓየር ሞገድ የፕሮግራሙን ሥርጭቅ አቁሞ የነበረው ኢሳት በሰኔ 2፣ 2003 ዓም ወደ መደበኛ ሥርጭቱ መመለሱን ለህዝብ ይፋ ሲያደርግ በታላቅ ደስታ ነው። መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ማንም ሊከለክልህና ሊገድብብህ ሥልጣን የሌለውን እውነተኛ መረጃ የማግኘት ተፈጥሯዊ መብትህን ለማፈን እና እነርሱ የፈለገውን የውሸት ትርኪ ምርኪ ካልሆነ በቀር፣ ሌላ ምንም ዓይነት መረጃ እንዳታገኝ፣ በሥልጣን ላይ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን (ኢሳት) ከጥር እስከ ሚያዚያ 2003 ዓ/ም የአደረገው የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ዘመቻ አስመልክቶ የወጣ መግለጫ

ሐምሌ 6 ቀን 2003 ዓ/ም የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን (ኢሳት) ከጥር እስከ ሚያዚያ 2003 ዓ/ም የአደረገው የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ዘመቻ አስመልክቶ የወጣ መግለጫ በሃገራች በሥልጣን ላይ ያለው የፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ የኢትዮጵያን ህዝብ በመረጃ ጨለማ ውስጥ ለመግዛት ያሰፈነውን የአፈና ቀንበር ለመስበርና፣ ፍትህና ዴሞክራሲን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን የህዝብ አይንና ጆሮ በመሆን የበኩሉን አስተዋጾ ሲያደርግ መቆየቱን ይታወሳል። እንደሚታወቀው ኢሳት በእቅድ ...

Read More »

ለኢሳት የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ ለ10 ቀናት ተራዘመ ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) የተሰጠ መግለጫ፣

መጋቢት 11 ቀን 2003 ዓ/ም የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ሥራ ከጀመረ ካለፈው የሚያዚያ ወር 2002 ዓም ጀምሮ በተለያዩ ደረጃዎች ያጋጠሙትን ችግር እየተቋቋመ በርካታ ፕሮግራሞችን በቀጥታ ወደ ሀገር ቤት በማስተላለፍ ከፍተኛ የህዝብ ቀልብ ለመሳብ በቅቷል፣ ይህን ሥራውን ዛሬም ቀጥሏል። ኢሳት አሁን ባለበት ደረጃ ወደ ሀገር ቤት የሚሰጠውን አግልግሎት እንዲቀጥልና በውጭ ሀገርም የቴሌቪዥን አገልግሎት ስርጭት ለመጀመር ያለውን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ፣ ከዚህ በፊት ...

Read More »

ኢሳት አፈና ተቋቁሞ በአየር ተመለሰ ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት የተሰጠ መግለጫ

ኢሳት አፈና ተቋቁሞ በአየር ተመለሰ ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት የተሰጠ መግለጫ የካቲት 3፣ 2003ዓም ውድ ኢትዮጵያውያን፣ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ከህዳር 23 2003 ዓም ጀምሮ ላለፉት ሁለት ወራት ስርጭቱን በታይኮም 5 ሲያስተላለፍ መቆየቱ ይታወሳል። በስልጣን ላይ ያለው ገዢ ፓርቲ ይህን የቴሌቪዥን ጣቢያ ለማፈን ያለፉትን ሁለት ወራት ላይ ታች በማለት አሳልፎአል። ገዢው ፓርቲ በተለይ በአሁኑ ጊዜ ወደ ሦስት ሚሊዮን ህዝብ ለከፍተኛ ...

Read More »

ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ፣

የካቲት 2፣ 2003 ዓም በዛሬው ዕለት የካቲት 2፣ 2003 ዓም በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 5:45 ላይ ኢሳት ወደ ኢትዮጵያና አካባቢ ሀገራት የሚያስተላልፈው የቀጥታ ፕሮግራም ስርጭት ተቋርጧል። የኢሳት ስራ አመራር እና ቴክኒካል ቡድን ከታይኮም ኩባንያ ባለስልጣናት ጋር በመሆን ፕሮግራሙ የተቋረጠበትን ምክንያት ለማወቅ በመነጋገር ላይ ይገኛል። ይህም በመሆኑ፦ ሀ) ከሳተላይት ኩባንያው ጋር ተነጋግረን የምናገኘውን ውጤት በአስቸኳይ ለህዝብ ይፋ እናደረጋለን። ለ) የኢሳት ፕሮግራም ...

Read More »