ህዳር 28 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በታጠቅ ወታደራዊ ማሰልጠኛ በአህባሽ የእስልምና አስተምህሮ ላይ ስልጣና የወሰዱት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን፣ በኢትዮጵያ የሚታየውን የእስልምና አክራሪነት እንዲዋጉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። ስልጠናው በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር በዶ/ር ሺፈራው ተክለማርያም፣ በአዲስ አበባ የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊ በኮማንደር መኮንን አሻግሬ እና የአህባሽን አስተምህሮ በሚከተሉ ሙስሊሞች አማካኝነት መሰጠቱ ታውቋል። ለሰልጣኞቹ የተሰጠው ስልጠና በዋነኝነት ያተኮረው ፣ አህባሽ የተባለው የእስልምና እምነት አገርበቀል በመሆኑ ማንኛውም ...
Read More »Author Archives: Central
የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ አዲስ ማእቀብ ለመጣል መወሰኑን ተከትሎ በሁለቱ አገሮች ውጥረቱ ጨመሯል
ህዳር 28 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ አዲስ ማእቀብ ለመጣል መወሰኑን ተከትሎ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ውጥረት መጨመሩ ታወቀ ደብረብርሀን ብሎግ የጦር መሳሪያና ሰራዊት የጫኑ ተሽከርካሪዎች በሰሜን አዲስ አበባ በኩል ሲጓዙ እንደነበር ዘግቧል። ኢሳት ወደ ሰሜን የአገሪቱ ክፍል በመደወል እንዳረጋገጠው ከሆነ እረቡ በወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የሚመሩ ፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የጫኑ በርካታ አውቶብሶች ወደ ሰሜን ተጉዘዋል። በድንበር ...
Read More »አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ በዋሽንግተን ዲሲ ዝግጅት ያቀርባሉ
ህዳር 28 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ “ለመብት ተማጓቾች ይጻፉ” በሚል ርእስ በዋሽንግተን ዲሲ ናሽናል ፕሬስ ክለብ አንድ ዝግጅት ያቀርባሉ። ዲሰምበር 9፣ 2011 በሚቀርበው ዝግጅት ላይ የቀድሞ የአንድነት ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በክብር እንግድነት ይገኛሉ። ከ6፡30 እስከ 9፡30 በሚቆየው ዝግጅት ኢትዮጵያኖች ተገኝተው በእስር ላይ ለሚገኙት የነጻነት ታጋዮች ደብዳቤ እንዲጽፉ የአንድነት ዲሲ ሜትሮ የድጋፍ ቅርንጫፍ ...
Read More »በ2002 ዓም ከኢትዮጵያ ተዘርፎ ወደ ውጭ አገር ባንኮች የተላከው ገንዘብ ፣ መንግስት በተመሳሳይ አመት መድቦት ከነበረው ገንዘብ ጋር እኩል መሆኑን መረጃዎች አመለከቱ
ህዳር 27 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በ2002 ዓም ከኢትዮጵያ ተዘርፎ ወደ ውጭ አገር ባንኮች የተላከው ገንዘብ ፣ መንግስት በተመሳሳይ አመት መድቦት ከነበረው ገንዘብ ጋር እኩል መሆኑን መረጃዎች አመለከቱ ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ ይፋ ባደረገው ቅድመ ጥናት መሰረት በፈረንጆች አቆጣጠር ከ2002 እስከ 2009 ባሉት 7 አመታት ውስጥ፣ ከ187 ቢሊዮን ብር ወይም 11 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገንዘብ ተዘርፎ በውጭ አገር ባንኮች ተቀምጧል። ...
Read More »ህወሀት፤ የድርጅቱን ታሪክ በአዲስ መልክ ለማፃፍ 43 ሚሊዮን ብር መመደቡ ተጠቆመ
ህዳር 27 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የ “ከአገር በስተጀርባ” መጽሐፍ ደራሲን በመጥቀስ ፍኖተ-ነፃነት እንዳስነበበው፤የህወሀት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑትን ዶክተር ሰሎሞን ዕንቋይን “ጠልመት” እና የ አቶ ሀይላይ ሀድጉ ሥራ የሆነውን “ንንዓት” የተባሉትን መጽሀፍት መሰረት በማድረግ፤ የህወሀትን ታሪክ በአዲስ መልክ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ለማፃፍ 43 ሚሊዮን ብር ተመድቧል። “የሀብት ብዛትና ስልጣን እውነተኛውን ታሪክ ሊቀይሩት አይችሉም” ያሉት የመጽሐፉ ደራሲ፤ “43 ሚሊዮን ብር ቀርቶ 43 ...
Read More »የስዊድን ጋዜጠኖች የመለስ መንግስት ያቀረበውን የሽብርተኝነት ክስ ፈጠራ ነው አሉ
ህዳር 27 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጋዜጠኞቹ ማክሰኛ እለት በዋለው ችሎት እንደገለጡት ፣ ወደ ኦጋዴን ክልል የገቡት የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅትን ለመርዳት ሳይሆን በአካባቢው በነዳጅ ፍለጋ ላይ የተሰማራው ሉንዲን ኦይል የተባለውን የስዊዲሽ የነዳጅ ኩባንያ በሰብአዊ መብት ጥሰት የሚከሰሰውን የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት አባላት በዘበኝነት መቅጠሩን ለማረጋገጥ ነው። ጋዜጠኛ ማርቲን ሺቢዬና ጆሀን ፔርሰን እንዳሉት ከኦብነግ ጋር የነበራቸው ግንኙነት የጋዜጠኝነት ስነምግባርን በተከተለ ...
Read More »በተለያዩ ህገወጥ መንገዶች ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ አገር የወጣው ገንዘብ 11 ቢሊዮን ደረሰ፣ ኢትዮጵያውያን እየደሙ ነው
ህዳር 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በስርቆት፣ በሙስናና በተለያዩ ህገወጥ መንገዶች ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ አገር የወጣው ገንዘብ 11 ቢሊዮን መድረሱን አንድ ታዋቂ አለማቀፍ ተቋም አጋለጠ፣ ኢትዮጵያውያን እየደሙ ነው ሲል የድርጊቱን አስከፊነትም ገልጧል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት መርሀግብር ወይም ዩኤን ዲ ፒ የገንዘብ ድጋፍ ጥናቱን ያካሄደው “ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ” የተባለው አለማቀፍ ተቋም ባወጣው የቅድመ ዳሰሳ ሪፖርት ፣ እጅግ ደሀ ከሆነችው ኢትዮጵያ ...
Read More »በአማራ ክልል በመንግስት እና በመምሀራን መካከል ያለው ውዝግብ ተካሯል
ህዳር 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስማቸውን መግለጥ ያልፈለጉ የክልሉ መምህራን እንደሚሉት፣ መንግስት የክልሉን የመምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት፣ አቶ መንግስቱ አህመዴን፣ ከስልጣን ለማስወገድ የጀመረውን ዘመቻ አጠናክሮ መቀጠሉ ፣ በመምህራን እና በመንግስት መካከል ያለው ፍጥጫ እንዲጨምር አድርጎታል። የመንግስት ባለስልጣናት በተለያዩ የወረዳ ትምህርት ቤቶች ተገኝተው “የማህበሩ ሊቀመንበር የግንቦት7 አባል ነው፤ መምህራን የተቃውሞ ሰልፍ እንዲያደርጉ እና ከመንግስት ጋር እንዲጋጩ እየቀሰቀሰ ነው” በማለት መናገራቸው ታውቋል። ...
Read More »የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ኮሚቴዎች በባህር ዳር ተገናኝተዉ መነጋገራቸዉን ቪዢን ዴይሊ የተሰኘዉ የሱዳን የሚዲያ ማእከል ገለጸ
ህዳር 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኮሚቴዉ በድንበር አካባቢ በድብቅ የሚካሄደዉን የጦር መሳሪያ ዝዉዉር ለመግታት፤ አዘዋዋሪዎቹን ለመያዝና ለማሰር፤ በድንበሩ አካባቢ ያሉ ትናንሽ ከተማዎችና ወረዳዎች በፀጥታ ጥበቃ ረገድ ይበልጥ በሚጠናከሩበት፤ እና መረጃ በሚለዋወጡበት መንገድ ላይ መክሯል። እንዲሁም የቀንድ ከብት በሽታዎችን ለመቆጣጠርና የእንሰሳት የህክምና መስጫ ጣቢዎችን ለማቋቋም ስምምነት ላይ መድረሳቸዉ ተገልጿል። የሱዳን የድንበር ኮሚቴ የተመራዉ ያልተማከለዉ የመንግስት ም/ቤት ዋና ፀሃፊ በሆኑት ፕሮፌሰር ...
Read More »በጋሞጎፋ ዞን በጨንቻ ከተማ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ
ህዳር 25 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአካባቢው የሚኖሩት የጋሞ ተወላጆች ተቃውሞውን ያነሱት፣ የእርሻ ማሳቸውን ወደ ከተማ ለማካለል ሙከራ ማድረጉን ለመቃወም ነው። ከሁለት ቀናት በፊት 5 ሺ የሚጠጉ ነዋሪዎች ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡበት ጊዜ የፌደራል ፖሊስ አባላት በአካባቢው ተገኝተው ሰልፉን የበተኑ ሲሆን፣ መንግስትም በአካባቢው የስልክ ግንኙነት እንዳይኖር አድርጎ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ውጥረቱ አሁንም እንዳለ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች፣ ህዝቡ ሰልፉ ከተበተነ በሁዋላም ...
Read More »