ጥር 5 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የአርባምንጭ ወኪል እንደገለጠው ወጣት ደግነት ጌታቸው ታህሳስ 28 ፣ 2004 ዓም ለገና በአል ዋዜማ ከጓደኞቹ ጋር ሲዝናና በነበረበት ወቅት፣ በፖሊሶች ተገድሏል። ወጣት ደግነት ለጸጥታ አደገኛ ነው በሚል ምክንያት ክትትል ሲደረግበት እንደነበር ዘጋቢያችን ገልጧል። የወጣት ደግነት አባት የሆኑት አቶ ጌታቸው ለኢሳት እንደተናገሩት ልጃቸው የተገደለው ምንም ጥፋት ሳያጠፋ መሆኑን ገልጠው፣ ገዳይ ፖሊሶችን ለፍርድ ለማቅረብ አቅም ...
Read More »Author Archives: Central
በሺ የሚቆጠሩ የስዊድን ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
ጥር 5 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የስዊዲን ጋዜጠኞች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እንዲሁም ከዴንማርክ፣ ፊንላንድ፣ ኖርዌይ፣ ኢትዮጵያ፣ ኢራቅ እና ኢራን የመጡ በስዊድን የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሰልፉ ላይ ተገኝተዋል። ሰልፈኞቹ የስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት ለህዝብ እንዲያሳውቅ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ስልጣን እንዲለቁ፣ የመለስ መንግስት ጋዜጠኞችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ እንዲሁም የስዊድን መንግስት ጋዜጠኞችን በገንዘብ ለማስፈታት የሚያደርገው ...
Read More »በመንግስትና በኦሞ ሸለቆ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መካከል ያለው ውዝግብ እንደቀጠለ ነው
ጥር 5 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት በአካባቢው የሚኖሩ በርካታ ብሄረሰቦችን በማፈናቀል ፣ መሬታቸውን ለእርሻ ልማት ማዋሉ የአካባቢውን ነዋሪዎች ማስቆጣቱን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ አስታውቋል። ንቅናቄው የቦዲ ብሄረሰብ አባላት በጭነት መኪና ቀያቸውን ለቀው ከተጋዙ በኋላ በመሬታቸው ላይ ስላላቸው መብት መንግስት እንክብካቤ እንዲደረግላቸው ቢጠይቁም ምላሽ አላገኙም። ታህሳስ 28፣ 2004ዓም ወ/ሮ ቢኮሉ የተባሉ ሴት ወደ ከብቶቻቸው እየተጓዙ ባለበት ወቅት በከባድ ጭነት መኪና ...
Read More »የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ በአዋጁ ዙሪያ ከነዋሪው ጋር ያደረጉት ውይይት ተቃውሞ ቀረበበት
ጥር 5 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የከተማ ቦታን አስመልክቶ የወጣው አዲስ አዋጅ ፓርላማ በተባለው የኢህአዴግ አባላት ሸንጎ ከፀደቀ በሁዋላ የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ በአዋጁ ዙሪያ ከነዋሪው ጋር ያደረጉት ውይይት ተቃውሞ ቀረበበት። የአቶ ኩማ አስተዳድር ቢሊዝ አዋጁ ላይ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ በተለየ መልኩ የተስተጋባው ተቃውሞ፤ የራሱ የውይይት መድረኩn መዘጋጀቱ ፋይዳነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ነው። ምክንያት፦ የሊዝ አዋጁ ለውይይት ተብሎ ...
Read More »በአወልያ የተጀመረውን ተቃውሞ ተከትሎ በአዲስ አበባ የሚኖሩ ሙስሊሞች ለተማሪዎች እንቅስቃሴ ያላቸውን ድጋፍ ገለጡ
ጥር 4 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአርብ ወይም የጁማን ስገደት ለመስገድ በአወልያ መስጂድ የተገኙት የአዲስ አበባ ነዋሪ ሙስሊሞች፣ ከተማሪዎች ጋር በመሆን የተቃውሞ መፈክሮችን አሰምተዋል። በርካታ ሙስሊሞች በአወልያ መስጂድ ተገኝተው ስግደት መስገዳቸውን፣ ከስግደቱ በሁዋላ በአንድ ተማሪ አማካኝነት የቀረበውን መፈክር አብረው መድገማቸውን ተማሪዎች ለኢሳት ገልጠዋል። ከመፈክሮቹ መካከል ምርጫ በነጻነት ይካሄድ፣ መጂሊሱ ይፍረስ፣ የሀይማኖት ነጻነት ይከበር የሚሉ ይገኝበታል። ለስግደት የሄዱት ሙስሊሞች ተማሪዎችን ሲያበረታቱ ...
Read More »በምእራብ ጎጃም ዜን በአዴት ወረዳ የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ሰዎች ታሰሩ፣ መሳሪያ የቀሙት ወጣቶችን የማደኑ ስራ ቀጥሏል
ጥር 4 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በወረዳው ፈቃድ በህብረተሰቡ የተገነቡ ከ500 መቶ መኖሪያ ቤቶች በላይ በቅርቡ በክልሉ መንግስት ጨረቃ ቤት ተብለው ማክሰኞ እለት በግብረ ኃይል ሊያፈርሱ የተንቀሳቀሱት የወረዳው የጥቃቅን እና እንዱስትሪ ዋና ኃላፊ አቶ ይበሉ ደሴ፣ ምክትል ኃላፊው አቶ እንድሪስ ክንዴ፣ የቤቶች ቁጥጥር ኃላፊው አቶ ገበያው ደምለው እና ፖሊስ ይልማ ተፈራ በታጣቂ ኃይል ይዘውት የመጡትን መሳሪያ ተቀምተው መመታታቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ...
Read More »በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በአሸባሪነት ወንጀል ክስ የመሰረተባቸው ላይ ሊሰጥ የነበረውን የጥፋተኝነት አሊያም ከጥፋት ነፃ የመሆን ብይን በተለዋጭ ቀጠሮ አራዘመ
ጥር 4 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ መንግሥት በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በአሸባሪነት ወንጀል ክስ የመሰረተባቸው 24 የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባላት፣ ጋዜጠኞች እና ነፃ አሳቢ ዜጎች ላይ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ሊሰጥ የነበረውን የጥፋተኝነት አሊያም ከጥፋት ነፃ የመሆን ብይን ለጥር 14 ቀን 2004 ዓ.ም በጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ አራዘመ፡፡ በዳኛ እንደሻው አዳነ፣ ሙሉጌታ ኪዳኔ ...
Read More »የአባይ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ በርካታ ችግሮች እንዳሉበት ተገለፀ
ጥር 4 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዜናዊ “ የኢትዮጵያ ህዝብ ማንኛዉንም መስዋዕትነት ይከፍላል፡ በአንድ ቃል ‘ ግድቡ ይሰራ!’ እንደሚሉ ምንም ጥርጥር የለኝም” በማለት የተናገሩ ቢሆንም ፣ ዜጎች በአብዛኛዉ በግንባታዉ ስራ ደስተኛ እንዳልሆኑ ክርስቲያን ሳይንስ ሞኒተርስ ዘገበ። አገሪቱ በራሷ ተግባራዊ አደርገዋለሁ ብላ የተያያዘችዉና ያደረባት ጉጉት ከሚገባዉ በላይ መጠኑን ያለፈ መሆኑ እና ፕሮጀክቱ ለህዝብ በተገለፀ ከአንድ ወር በሚያንስ ጊዜ ዉስጥ ...
Read More »ኢትዮጵያዊያን ቤተ እስራኤላዊያን በደረሰባቸዉ የዘር መድልዎ ያነሱት ተቃዉሞ እንደሚጣራ ፖሊስ አረጋገጠ
ጥር 4 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእየሩሳሌም ኪሪያት ማላኪ በተባለዉ አካባቢ ነዋሪዎች ቤታቸዉን ለኢትዮጵያዊያን ቤተ እስራኤላዊያን ላለማከራየትና ላለመሸጥ በፊርማ ያደረጉት ስምምነት ያስቆጣቸዉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላቀረቡት አቤቱታና ተቃዉሞ የተሰጣቸዉ መልስ ሌላ ቁጣን አስከትሏል። የቤተ እስራኤላዉያኑን አቤቱታ ለመስማት የተገኙት የእስራኤል የስደተኛ ጉዳዮች ሚኒስትር ወ/ሮ ሶፋ ላንድቨር “ ከኢትዮጵያ የመጡት ፈላሻዎች የእስራኤል መንግሰት ላደረገላቸዉ ዉለታ ምስጋና ሊያቀርቡ ይገባል” በማለት የሰጡት ምላሽ “በዘር ላይ ...
Read More »በም/ጎጃም በአዴት ከተማ በተነሳ የህዝብ ተቃውሞ አንድ ባለስልጣን ሲገደል ሌሎች ሁለት ፖሊሶች እና ሌላ አንድ ባለስልጣን ከፉኛ ቆስለዋል
ጥር 3 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአማራ ክልል በምእራብ ጎጃም ዞን በይልማና ዴንሳ ወረዳ በአዴት ከተማ በተነሳ የህዝብ ተቃውሞ አንድ ባለስልጣን ሲገደል ሌሎች ሁለት ፖሊሶች እና ሌላ አንድ ባለስልጣን ከፉኛ ቆስለዋል። ማምሻውን በደረሰን ዜና ደግሞ በጽኑ ከቆሰሉት መካከል አንደኛው ህይወቱ አልፎአል። በትናንትናው እለት የወረዳው ባለስልጣናት የጨረቃ ቤቶችን ለማፍረስ በተንቀሳቀሱበት ጊዜ፣ ህዝቡ ቤታችንን አታፈርሱም በማለት ከባለስልጣኖች ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብቶ ነበር። ...
Read More »