Author Archives: Central

አንድነት ግንቦት 12 ቀን የሚያዘጋጀው መድረክ በአራት እውቅ አርቲስቶች እንደሚመራ አስታወቀ

ግንቦት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲው፦”ኪነ-ጥበብ በማህበረሰቡ ውስጥ ያላት ሚና” በሚል መሪ ሀሳብ በሚቀጥለው እሁድ በብሄራዊ ቴአትር በሚያካሂደው ዝግጅት የአገሪቱ እውቅ አርቲስቶች ተገኝተው ከተሳታፊው ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ገልጿል። ይሁንና መድረኩን የሚመሩት ዕውቅ አርቲስቶች እነማን እንደሆኑ ፓርቲው ለጊዜው ስማቸውን ከመግለጽ ተቆጥቧል። በፓናል ውይይቱ ስለሚሳተፉት አራት ፓናሊስቶች ማንነት ፓርቲው ለጊዜው ከመግለጽ ቢቂጠብም፤ ከመካከላቸው ሰዓሊ፣ ደራሲና ጸሐፊ ተውኔት እንደሚገኙበት የፓርቲው የህዝብ ...

Read More »

የግንቦት7 7ኛ አመት ታስቦ ዋለ

ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ግንቦት 7 ፣ 1997 ዓም በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ልየ  ስፍራ የሚይዝ ቀን ነው። መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚባል ሁኔታ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ አካሂዷል። ምንም እንኳ የመጨረሻ ውጤቱ ፣ እንደሂደቱ ያማራ ባይሆንም፣ ግንቦት7 አሁንም ዲሞክራሲያዊ ስርእት ተገንበቶ ማየት በሚሹ በብዙ ኢትዮጵያውያን አእምሮ ውስጥ እንደ አዲስ በእየአመቱ ይታወሳል። ቀኑን በማስመልከት ግንቦት 7ትን ለ7ኛ ...

Read More »

ከ400 በላይ የፖለቲካ እስረኞች ፍትህ አጥተው በመንገላታት ላይ ናቸው

ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከቃልቲና እና ከቂልንጦ ማረሚያ ቤቶች ለኢሳት በተላከው ስም ዝርዝር ላይ ለመመልከት እንደሚቻለው ፣ በሁለቱ እስር ቤቶች ብቻ በመለስ መንግስት የሀሰት ክስ ተከሰው ፍትህ አጥተው የሚሰቃዩ 401 ሰዎች አሉ። አብዛኞቹ የታሰሩት ከግንቦት7 እና ከኦነግ ጋር በተያያዘ ነው። በብሄር ተዋጽኦም አብዛኞቹ አስረኞች የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች ናቸው። በአቶ አንዱአለም መዝገብ 24፣ በአቶ በቀለ ገርባ 9፣ በጄ/ል ...

Read More »

በህትመት ሚዲያዎች ላይ ያለው ጫና እየጨመረ ነው

ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅርቡ የሕትመት ሰታንዳርድ ውል ፈርሙ በሚል በአሳታሚዎች ላይ ጫና እያሳደረ ያለው  የብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት በአሳታሚዎች ላይ ተዘዋዋሪ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው። ማተሚያ ቤቱ ባለፉት ሶስት ቀናት ሲ.ቲ.ፒ የተባለ ማሸን ( computer to plate)ተበላሸቷል፣ፊልም የለኝም በማለት ጋዜጦችን በማጉላላት ላይ ከመገኘቱም በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት መታተም የነበረበት “ፍኖተ ነጻነት ” የተባለው የአንድነት ፓርቲ ጋዜጣ እንዳይታተም ምክንያት ...

Read More »

በሙስሊሞች ላይ መንግስት ጠጣር የሀይል እርምጃ ይወስዳል የሚል ስጋት እንዳለ ተነገረ

ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መቀመጫውን በለንደን  ያደረገው ዓለማቀፉ “ኮንትሮል ሪስክ” ድርጅት ፤የ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች በተቃውሟቸው እየጠነከሩ ከመጡ መንግስት ጠጣር የሀይል እርምጃ ይወስዳል የሚል ስጋት እንዳለው ገለጸ። የድርጅቱ የውዝግቦች ጉዳይ ተንታኝ ሚስተር ፓትሪክ ሜየርን ከዶቸ ቨለ የ አማርኛው ክፍል ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ባደረጉት ቃለ-ምልልስ፤ኢትዮጵያ ፤ በአፍሪቃ ቀንድ አክራሪ እስልምናን በመቋቋም ረገድ፣ የምዕራቡ ዓለም ተጓዳኝ መሆኗን እና ይህን በማከናወን ...

Read More »

ኢህአግ፤ ወታደራዊ ድል ተቀዳጀሁ አለ

ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ሚያዝያ 28 ቀን 2004 ዓመተ ምህረት  በሰሜን ጎንደር ዞን በሰሮቃ ልዩ ስሙ እምቡጉዳድ በሚባል ስፍራ ከወያኔው ልዩ ሀይል ጋር ባካሄደው አውደ ውጊያ ዘጠኝ ወያኔ ገድሎ ሶስት ማቁሰሉን ገለጸ። ግንባሩ  ጥቃቱን ከመፈፀምም ባሻገር  እንቅስቃሴውን በአካባቢው በማስፋፋት ህዝቡን የሚቀሰቅሱ በራሪ ወረቀቶችን ማሰራጨቱንም አስታውቋል። በግንባሩ የተበተኑት ወረቀቶች ከያዙት መልእክቶች ውስጥ፦በዋልድባ ገዳምና በተለያዩ ...

Read More »

በበለደ ወይን የኢትዮጵያ ወታደሮች ተገደሉ

ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሶማሊያ በበለደወይን አካባቢ በመንገድ ላይ የተጠመደ ፈንጂ ፈንድቶ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ጉዳት ማድረሱን መረጃዎች አመልክተዋል። ፍንዳታው የተከሰተው የኢትዮጵያ ወታደራዊ ተሽከርካሪ፣ ወደ ምስራቅ የአገሪቱ ክፍል ለማምራት ጉዞ ሲጀምር ነው። ምንም እንኳ የሟቾች ቁጥር ባይገለጠም፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች በወሰዱት የአጸፋ እርምጃ ሁለት ሲቪሎችን መግደላቸው ታውቋል። እስካሁን ድረስ ጥቃቱን ማን እንዳደረሰው አልታወቀም። የኢትዮጵያ ወታደሮች አካባቢውን አጥረው ፍተሻ ...

Read More »

በርካታ ኢትዮጵያውያን፦መለስ ሥልጣን በቃኝ ማለታቸውን ”የተለመደ ቧልትና ፌዝ”ሲሉ አጣጣሉት

ግንቦት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መለስ  እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2015 ማለትም የዛሬ ሦስት ዓመት ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ እና ከዚያ በሁዋላ በማናቸውም የመንግስት የሥልጣን ቦታ ላይ እንደማይቀመጡ መናገራቸውን በርካታ ኢትዮጵያውያን፦”የተለመደ ቧልትና ፌዝ”ሲሉ አጣጣሉት። መለስ ይህን ያሉት ፤  ሰሞኑን ከሲሲቲቪ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ቀደም ካሉት ዓመታት ጀምሮ ለቢቢሲ እና ለሌሎች ዓለማቀፍ ሚዲያዎች ጭምር ፦”የሚቀጥለው ተርም የመጨረሻዬ ነው” እያሉ ...

Read More »

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት ፕሬዝዳንት መንግሥት ለደህንነታቸው ከለላ ሰጣቸው

ግንቦት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት (መጅሊስ) ፕሬዝዳንት ሸህ አህመዲን ሸህ አብድላሂ ጩሌ የኢህአዴግ መንግሥት ለደህንነታቸው ሲል ባመቻቸላቸው ቤት ውስጥ መኖር መጀመራቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮች አስታወቁ፡፡ የአዲስ አበባ እና አካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ በአወሊያና ሌሎች መስኪዶች የመጅሊስ ይፍረስና የኢህአዴግ መንግሥት በላያችን ላይ በሥልጠና በግድ የሚጭነውን የአሕባሽ አስተምህሮ  ያንሳልን ሲሉ የተጠናከረ ጥያቄ ማንሳት ከጀመሩ ካለፉት አራት ወራት ...

Read More »

ለአባይ ግድብ ማሰሪያ የታቀደወ የሩጫ ፕሮግራም ባልተጠበቀ መንገድ ተከናወነ

ግንቦት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዝግጅቱ በከፍተኛ ምስጥር ተይዞ ስለነበር እስከ ቅዳሜ ምሽተ ድረስ ማወቅ የተቻለው ዝግጅቱን የአ/አ ከተማ አስተዳደር እንዳዘጋጀው ነበር፡፡  በፕሮግራሙ ላይ ግን በአቶ አየለ ጫሚሶ የሚመራው ቅንጅት የተባለው ፓርቲ ከአስተዳደሩና ከአትሌቲክስ ፌዴሬሸን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው መሆኑ በይፋ ተነግሯል፡፡ዓላማውም በህዳሴ ግድብ ዙሪያ መነቃቃትን ለመፍጠር፣ድጋፍን ለማጠናከር ነው ተብሏል፡፡በዝግጅቱ ላይ ከየክለቡ የተውጣጡ አትሌቶች፣የህዳሴ ግድብ የአ/አ ም/ቤት አባላት ፣የፓርቲው ...

Read More »