ለአባይ ግድብ ማሰሪያ የታቀደወ የሩጫ ፕሮግራም ባልተጠበቀ መንገድ ተከናወነ

ግንቦት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ዝግጅቱ በከፍተኛ ምስጥር ተይዞ ስለነበር እስከ ቅዳሜ ምሽተ ድረስ ማወቅ የተቻለው ዝግጅቱን የአ/አ ከተማ አስተዳደር እንዳዘጋጀው ነበር፡፡  በፕሮግራሙ ላይ ግን በአቶ አየለ ጫሚሶ የሚመራው ቅንጅት የተባለው ፓርቲ ከአስተዳደሩና ከአትሌቲክስ ፌዴሬሸን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው መሆኑ በይፋ ተነግሯል፡፡ዓላማውም በህዳሴ ግድብ ዙሪያ መነቃቃትን ለመፍጠር፣ድጋፍን ለማጠናከር ነው ተብሏል፡፡በዝግጅቱ ላይ ከየክለቡ የተውጣጡ አትሌቶች፣የህዳሴ ግድብ የአ/አ ም/ቤት አባላት ፣የፓርቲው አመራሮች እና በግል ጥሪ የደረሳቸው እጅግ አነሰተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች የተካፈሉ ሲሆን የጸጥታ ጥበቃው ከወትሮ በተለየ ከበድ ብሎ ታይቷል፡፡  የጸጥታ ችግር ያጋጥማል በሚል የአ/አ ነዋሪ ሕዝብ እንዳይሰማ መደረጉን የኢሳት ምንጮች ገልጠዋል፤  በአቶ ሙሼ ሰሙ የሚመራው ኢዴፓን ጨምሮ ከኢህአዴግ ዓመታዊ የፋይናንስ ድጎማ የሚሰጣቸው ኢራፓ፣ኢሶዴፓ፣መኢብን፣ኢፍዴሃግ  የሚባሉ ፓርቲዎች  የህዳሴ ግድብ የአ/አ እና የፌዴራሉ ም/ቤት አባላት ቢሆኑም በዛሬው ፕሮግራም ላይ ባልታወቀ  ምክንያት አልተሳተፉም::

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide