በከምሴ የሚገኙ ሙስሊሞች ዛሬም ከፌደራል ፖሊሶች ጋር ተፋጠው ሶላትን አሳለፉ

ግንቦት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ሙስሊሞቹ በከተማው የገቢዎች ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት በደዌይ መስመር አካባቢ በሚገኘው መስጊድ እንደተሰባሰቡ የፌደራል ፖሊስ አባላትም አብረው በመግባት ሙስሊሞቹ ሶላታቸውን እንደጨረሱ እንዲበተኑ አድርገዋል።  ፖሊሶች ከሶላት በፊት ሌላ ነገር ማድረግ አትችሉም ተብለው እንዲበተኑ ቢደረገም፣ ፍጥጫው እንዳለ መሆኑን ምንጮች ገልጠዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ሙስሊሞችን ለማግባባት ጥረት ሲያደርጉ፣ የተወሰኑ ወጣቶችንም ለማስፈራራት ሙከራ ሲያደርጉ ውለዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ጥያቄዎችን ሲጠይቁ ለነበሩ ሙስሊሞች፣ “እኛ  ከበላይ ታዘን ነው፣ እባካችሁ ይህን ጊዜ በትእግስት አሳልፉት” በማለት ሲማጸኑ ተሰምተዋል።

በሌላ ዜና ደግሞ በኖርዌይ የሚኖሩ መስሊም ኢትዮጵያውያን ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።

በኦስሎ የሙስሊሙ ማህበረሰብ አስተባባሪ ግብረ ሀይል ውስጥ አስተባባሪ የሆኑት አቶ አያሌው ኡመር ለኢሳት እንደተናገሩት የተቃውሞዋቸው  ዋና አላማ መንግስት በእስልምና ሀይማኖት ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት ለመቃወም ነው።

በትናንትናው እለት በተለያዩ የአለም ክፍሎች ተቃውሞዎች መደረጋቸው ይታወሳል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide