ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ማህበሩ ሚያዚያ 23 በአልያንስ ፍራንሴስ ባካሄደው የሽልማት ስነስርአት ላይ የብሉምበርጉ ጋዜጠኛ ዊሊያም ዳቪድ ሰን የኢትዮጵያ ሚዲያ ብዙ ጊዜ የሚተች ቢሆንም፣ የሚቀርቡ አንዳንድ ዘገባዎች፣ መዝናኛዎችና መረጃዎች ፣ ተስፋ የሚሰጡ ናቸው ሲሉ በስነስርአቱ ላይ ተናግረዋል።
በእንግሊዝኛ የፎርቹኗ ማህሌት መስፍን አሸናፊ ስትሆን ማህሌት በሰሜን ወሎ የተገኘን ማእድን ተከትሎ የተፈጠረውን ውዝግብ ሚዛናዊ በሆነ መንገድ አቅርባለች። ”
ሁለተኛው ሽልማት ለካፒታሉ ኪሩቤል ታደሰ ሲሰጥ ኩሩቤል “ፕሬስ በስደት፣ የኢትዮጵያ እውነታ” በሚል ባቀረበው ጽሁፍ ነው ተሸላሚ የሆነው። በአማርኛ ጽሁፍ አሸናፊ የሆነው የሪፖርተሩ የማነ ነጋሽ ሲሆን፣ የማነ በጽሁፉ ህወሀት በረሀ ላይ በነበረበት ጊዜ መግበው ያሳደጉትን አካባቢዎች እንዴት ስልጣን ከያዘ በሁዋላ እንደረሳቸው የሚያሳይ ነው። በፎቶ ግራፍ ጋዜጠኝነት ደግሞ የካፒታሉ ሙሉጌታ አየለ አንደኛ የሪፖርተሩ ናሆም ተስፋየ ደግሞ ሁለተኛ ሆኖ ተመርጧል።
የመንግስት የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መስሪያ ቤት በምርጫው ላይ እንዲሳተፍ ቢጠየቅም ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። በሽልማት ስነስርአቱ ላይ ግን የመንግስት ተወካይ ተገኝቷል። መንግስት ሽልማቱ በስደት ያሉትን ጋዜጠኞችን ማካተት አለበት የሚለውን ሀሳብ በመቃወም ነው በምርጫው ላይ ያልተሳተፈው።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide