መጋቢት ፳፰ (ሃይ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በዱባይ በአሰሪዋ ተገድላ ግቢ ውስጥ ተቀብራለች የተባለችው ወጣት እጣ ፋንታ አልታወቀም ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት የኢትዮጵያው ዲፕሎማት መረጃ አልሰጥም ብለዋል።
በዱባይ በአሰሪዋ ተገድላ ጓሮ ውስጥ ስለተቀበረችው ወጣት ኢትዮጵያ ኢምባሲ በቂ ክትትል እንዳላደረገ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት በዱባይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ገልጠዋል። በተለይም አረጋሽ እየተባለች የምትጠራዋ ኢትዮጵያዊት ድርጊቱን ይፋ ካደረገች በሁዋላ አሁንም ድረስ በኢትዮጵያ ኢምባሲ ውሰጥ ተጠልላ እንደምትገኝ፣ ትናንት ወደ ስፍራው በመሄድ ለማረጋገጥ መቻሉዋን አንድ ስሟ እንዳይጠቀስ የፈለገች ኢትዮጵያዊት ገልጣለች
ልጅቷን በሀላፊነት ተረክቧታል የተባለውን የኢምባሲ ሰራተኛ ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም ግለሰቡ ግን ለመናገር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል
________________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide