ህይወታችን ሲኦል ሆኖል ይላሉ የሰሜን ወሎ ነዋሪዎች

የካቲት 24 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የጤፍ ዋጋ ባልተጠበቀ ሁኔታ ጭማሪ ማሳያቱ ህይወታችንን  ሲኦል አድርጎታል ሲሉ  የሰሜን ወሎ ነዋሪዎች ተናገሩ

ነዋሪዎቹ ለኢሳት እንደተናገሩት ከሳምንት በፊት አንድ ጣሳ ጤፍ 10 ብር ሲሸጥ የነበረ ቢሆንም፣ በሳምንት ውስጥ የ8 ብር ጭማሪ በማሳየት 18 ብር በመሸጥ ላይ ነው።

የጤፍ ዋጋ መጨመርን ተከትሎም በርካታ እቃዎች እየጨመሩ ነው። አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ሰው እንደተናገሩት በእህልና በሌሎች እቃዎች ጭማሪ ህዝቡ ግራ ተጋብቷል።

የፓርላማ አባሉ አቶ ግርማ ሰይፉ የኢትዮጵያ ህዝብ በተአምር የሚኖር ህዝብ ነው ያሉት  ትክክለኛ አባባል መሆኑን አሁን የሚታየውን የኑሮ ዋጋ እና የህዝቡን አኗኗር አይቶ መናገር እንደሚቻል እኝሁ አስተያየት ሰጪ አክለዋል

በአዲስ አበባም ከሶስት ቀናት በፊት 1250 ብር ሲሸጥ የነበረው ጤፍ በዛሬ እለት 1400 ብር ሲሸጥ መዋሉን ዘጋቢያችን ገልጧል።በድሬዳዋና በባህርዳርም እንዲሁ ባለፉት ሁለት ቀናት ከነበረው ዋጋ የ50 ብር ጭማሪ አሳይቷል።

የካቲት ወር በተለምዶ የእህል ዋጋ የሚቀንስበት ቢሆንም ዘንድሮ ግን ባልተጠበቀ ሁኔታ በተለይ ጤፍ ከፍተኛ ጭማሬ ማሳየቱ ህዝቡ ነገስ ምን ይሆን በሚል እንዲጨነቅ እያደረገው ነው።

የኑሮ ውድነቱ ቢጨምርም የሰዎች ገቢ ግን ለውጥ ሊያሳይ አለመቻሉ ችግሩን ውስብስብ አድርጎታል። የመንግስት ሰራተኞች ኑሮውን ለመቋቋም ባለመቻላቸው ጉቦን እንደዋነኛ የገቢ ምንጭ ማድረግ መጀመራቸውም እየተነገረ ነው።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide