የአድዋ ድል 116ኛው ዓመት መታሰቢያ በዓል ተከበረ

የካቲት 23 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-መላው ኢትዮጵያዊ በነቂስ ወጥቶ የጣሊያንን ወራሪ ሀይል ድል ያደረገበት ቀን በአዲስ አበባ ጀግኖች አርበኞች በተገኙበት ተከብሮአል።

የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች መላው አፍሪካን ለመቀራመት በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ1884 እስከ 1885 በፖርቱጋል አስታዋሽነት እና በጀርመን አዘጋጅነት የበርሊን ጉባኤ እየተባለ የሚጠራውን ስምምነት ፈርመዋል።

ስምምነቱ አውሮፓውያን አፍሪካን ለመቀራመት በሚያደርጉት ሩጫ እርስበርሳቸው እንዳይገጩ ዋስትና የሚሰጥ ብቻ ሳይሆን፣ የአፍሪካን ህልውናም በነጮች እጅ የሚያስገባ ነው።

በጊዜው በአውሮፓ ውስጥ በጥንካሬ ደረጃ የሁለተኝነት ስፍራ የነበራት ጣሊያን ፣ በአፍሪካ ውስጥ ቅኝ ግዛት በመያዝ ጥንካሬዋን ከፍ የማድረግ ምኞት ነበራት። ኢጣሊያ ከራሱ የቀደመ ስልጣኔ እና ታሪክ ያላትን ኢትዮጵያን ለመቆጣጠርው ያለመችው ህልም  የካቲት 23 ፣ ቀን 1888ዓም በጀግኖች የኢትዮጵያ ልጆች ህልም ሆኖ እንዲቀር ተደርጓል።

በአጼ ሚኒሊክና እና በእቴጌ ጣሀይቱ የተመራው የአድዋ ጦርነት ድል ፣ የኢትዮጵያውያንን ጀግንነት ለመላው አለም ያሳየበት ብቻ ሳይሆን፣ አፍሪካዊያን በራሳቸው እንዲኮሩ ያደረገ እና በሁዋላ ላይ ለታዩት የነጻነት ትግሎች በር የከፈተ ነበር።

ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን አፍሪካውያንን እና ለሰው ልጆች ነጻነት የሚታገሉትን ሁሉ ያኮራው ድል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ የሆነ ፈተና እየገጠመው መሆኑ ይታወቃል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስልጣን ላይ ያለው የመለስ መንግስት፣ የአድዋን ታሪክ በመበረዝ እና ጦርነቱን የመሩትን አጼ ሚኒሊክን በማንቋሸሽ ስራ ላይ መጠመዱን መዘገባችን ይታወሳል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide