ወላይታ ካለፉት 3 ወራት ጀምሮ ውሀና መብራት አላገኘችም

የካቲት 21 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ነዋሪዎቹ ለኢሳት እንደገለጡት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከ3 ወራት በፊት የጠፋው መብራት እስካሁን አልተመለሰም።

የመብራት መጥፋቱን ተከትሎም የቧንቧ ውሀ አቅርቦት ተቋርጧል። ነዋሪው በውሀ ወለድ በሽታ እየተጠቃ እንደሚገኝ አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ነዋሪ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባም አንዳንድ አካባቢዎች ውሀ መቋረጡን ተከትሎ ህዝቡ በጀሪካን ውሀ ከወንዝ መቅዳት መጀመሩን ዘጋቢያችን ገልጧል።

በሌላ ዜና ደግሞ በበመላ አገሪቱ  ከፍተኛ የሆነ የቢንዚል እጥረት መፈጠሩ ታውቋል። ችግሩ በደቡብ እና በኦሮሚያ ክልሎች ጎልቶ እየታየ ነው። በአርባ ምንጭ ወረዳ በቤንዚን እጥረት ሰበብ በተፈጠረው የትራንስፖርት እጥረት ህዝቡ ምሬቱን በከፍተኛ ሁኔታ እየገለጠ ነው።

መንግስት የቤንዚን እጥረት የለም በማለት ችግሩን የፈጠሩት ስግብግብ ነጋዴዎች ናቸው የላል። የማደያ ባለቤቶች ግን እጥረቱ በግልጥ እየታየ ነው፣ አቅርቦት የለም በማለት እንደሚናገሩ ለማወቅ ተችሎአል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide