አውንግ ሳን ሱ ኪ ከሥልጣናቸው መልቀቅ አለባቸው ተባለ።
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 24 ቀን 2010 ዓ/ም ) የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኃላፊ የሚያንማር መንግስትን ከጀርባ የሚመሩት አውንግ ሳን ሱ ቺ በአስቸኳይ ከስልጣናቸው መልቀቅ አለባቸው አሉ።
የቀድሞዋ የነፃነት ታጋይ እና የኖቬል ሽልማት አሸናፊዋ ሳን ሱ ቺ ከስልጣናቸው እንዲወርዱ የተጠየቁት፣በአናሳናዎቹ የሮሂንግያ ሙስሊሞች ላይ ባለፈው ዐመት የሀገሪቱ መከላከያ በፈፀመው ጭፍጨፋ ሳቢያ ነው።
የተመዱ የሰብአዊ መብት ኃላፊ ዘይድ ራአድ አል ሁሴይን ለቢቢሲ ሲናገሩ፣ የኖቬል ሽልማት አሸናፊዋ ለሰራዊታቸው ጥፋት ይቅርታ ከሚጠይቁ ወደ ቁም እስራቸው ቢመለሱ ይሻላል ብለዋል።
የመንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት በበኩሉ የሚያንማር መከላከያ የወሰደው እርምጃ የዘር ማጥፋት ወንጀል ስለመሆኑና ስላለመሆኑ ሊመረመር እንደሚገባ አሣስቧል።
የሚያንማር መንግስት ግን ወደ አንድ ወገን ያደላ ነው በማለት ሪፖርቲን እንደማይቀበለው አስታውቋል።
በቀድሞው የሚያንማር መንግስት ለ16 አመታት በቁም እስር ላይ የነበሩት የ73 ዓመቷ ሳን ሱ ኪ ፣ አሁን ባላቸው ስልጣን ወታደሩን ማዘዝ እንደማይችሉ በመግለፅ ለማስተባበል ቢሞክሩም፣የሚደረግባቸው ዓለማቀፍ ግፊት ቀጥሏል።
የቀድሞዋ የነፃነት ታጋይ እየተፈፀመ ያለውን ወታደራዊ ጥቃት ማስቆም አልቻሉም ሲል ተመድም ወቅሷቸዋል።
ትነሰንት ረቡዕም የኖቬል ሽልማት ኮሚቴው ተሰብስቦ ሳን ሱ ቺ እ አ አ በ1991 የወሰዱትን ሽልማት እንዲመልሱ ውሳኔ አሳልፏል።