(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 14/2010) ለስፖርታዊ ውድድር አውስትራሊያ የገቡ 200 የተለያዩ ሀገራት አትሌቶች ጥገኝነት ጠየቁ ።
ለኮመን ዌልዝ ውድድር ባለፈው ሚያዚያ አውስትራሊያ የገቡት ከ200 የሚበልጡት አትሌቶች ጥገኝነት የጠየቁት ወደ ሃገራቸው ቢመለሱ ስቃይ እንደሚደርስባቸው በማመናቸው ነው።
ብሪታኒያ እና በብሪታንያ ቅኝ የተገዙ ሃገራት በሚያደርጉት ውድድር ላይ ለመሳተፍ አውስትራሊያ ጎልድ ኮስት ከተማ ከገቡት 8 ሺህ ያህል አትሌቶች 205 ቱ ጥገኝነት ጠይቀዋል። ሌሎች 50 የሚሆኑት ደግሞ የመመለሻ ግዚያቸው ቢያልፍም ከአውስትራሊያ አለመውጣታቸው ታውቋል።ጥገኝነት የጠየቁት አትሌቶች ሃገራቸው በዝርዝር ባይገለጽም የሕንድ ዜጎች እንደሚገኙበትም ተመልክቷል።