(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 7/2010) በፍሎሪዳ የእግረኞች መተላለፊያ ድልድይ ተደርምሶ 6 ሰዎች ሞቱ።
ድልድዩ ሲደረምስ ከስሩ የትራፊ መብራት አቁሟቸው በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ ማረፉ ደግሞ አደጋውን የከፋ አድርጎታል ብሏል ዘገባዎች።
በ 8 ተሽከርካሪዎች ለይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው ይሄ አደጋ የተወሰኑት ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ በፍርስራሹ ውስጥ መቀበራቸው ታውቋል።
እንደመረጃው ከሆነ በአደጋው 5 ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ አንድ ሰው ደግሞ ሆስፒታል እንደደረሰ ህይውቱ ማለፉ ታውቋል።
ሌሎች 8 ሰዎች ደግሞ ለከፍተኛ የአካል ጉዳት መዳረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ድልድዩ ከአንድ አመት በፊት በስፍራው አንድ የፍሎሪዳ ዮኒቨርስቲ ተማሪ በመኪና አደጋ መሞቷን ተከትሎ ተጨማሪ አደጋን ለማስቀረት በሚል ለእግረኞችና ለብስኪሌት መተላለፊያ እንዲሆን በሚል የተገነባ እንደበርም ሲ ኤን ኤን በዘገባው አመልከቷል።
የፌደራሉ የምርመራ ቢሮ አደጋውን እያጣራ መሆኑን ሲገልጽ እስካሁን ባለው ሂደትም ድልድዩን ለመገንባት ሀላፊነቱን የወሰዱት ሁለት የኮንስትራክሽን ድርጅቶች ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስታውቋል።