ሚያዝያ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ 2000 ዓመት በፊት ኢየሱስ ክርስቶስ ኢየሩሳሌም -ቀራኒዮ ተራራ ላይ የተሰቀለበት እለት በመላው ዓለም በሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ ዛሬ ሲከበር ውሏል።
ስቅለት፤ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ የክርስቶስን ህማምና ስቃይ በሚያስታውስ መልኩ በተለየ ሀይማኖታዊ ሥር ዓት የሚከበር ታላቅ በዓል ሲሆን፤ እለቱን በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምእመናን በ የአጥቢያ
ቤተ ክርስቲያናቸው በመሄድ በጾም፣በጸሎትና በስግደት ሲያከብሩት ውለዋል።