መጋቢት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድምጻችን ይሰማ ይጠራው የሳንቲም ማጠራቀም የተቃውሞ ሰልፍ በቀላልና በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ዘጋቢያችን ገልጿል። በአዲስ አበባ የተለያዩ የእስልምና እምነት ተከታዮችን አነጋግሮ እንደዘገበው በርካታ
ሙስሊሞች ሳንቲሞችን በማጠራቀም ተቃውሞአቸውን እየገለጹ ነው። አንድ መርካቶ አካባቢ የንግድ ድርጅት ያለው ግለሰብ ” ንጹህ የሆኑ የሙስሊሙ መሪዎች ፍትህ አጥተው በእስር በሚማቅቁበት ወቅት፣ እኔ ከማገኘው ገቢ የተወሰነውን ሳንቲም ማጣራቀሜ ጥቅም
እንጅ ጉዳት የለውም፤ በሙሉ ደስታም እያደረኩት ነው ” ሲል፣ ሌላ ነጋዴ ደግሞ ” የቤተሰቡ አባላት መልእክቱን ተግባራዊ እያደረጉት ነው” ብሎአል። ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ ሳንቲም የማጠራቀሙ ውጤት በሚቀጥሉት 2 ሳምንታት ሊታይ ይችላል ሲል አስተያየቱን
ሰጥቷል። ድምጻችን ይሰማ ሳንቲሞችን ከማጠራቀም በተጨማሪ ሌሎች ተጨማሪ እርምጃዎችን እንደሚወስድ መግለጹ ይታወቃል።