ሐምሌ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ሰ/ሸዋ ዞን የመርሃ ቤቴ ወረዳ አለም ከተማ እና የሚዳ ወረሞ ወረዳ መራኛ ከተማን እንዲሁም አዋሳኝ የደራ ወረዳን ጨምሮ
24 ሰዓት የመብራት አገልግሎት እንዲሰጥ በአለም ከተማ የሚገኘውን ዋና የመብራት ማሰረጫ ትራንስፎርመር ተነቅሎ ወደ አቃስታ የመብራት ስቴሽን ጣቢያ ለማዛወር የነበረው እቅድ በህዝቡ ከፍተኛ
ተቃውሞ መክሸፉን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል ። የከተማው ምክትል አስተዳዳሪ ሰኞ ከሰአት በሁዋላ ህዝቡን በመሰብሰብ የመብራት ማሰራጫ ጋኑን ለማንሳት የነበረው እቅድ መሰረዙን ገልጸዋል።
ህዝቡ “ውሳኔያችሁን ከቀየራችሁ በከተማው የሰፈረው የፌደራል ፖሊስ ምንም ስለማይሰራ ከከተማችን ይውጣ” በማለት ጥያቄ ቢያቀርብም፣ ምክትል አስተዳዳሪውና የዞኑ ባለስልጣናት ፣ ” አሸባሪዎች በከተማው
ውስጥ በመግባታቸውና የጸጥታ ስራ ለመስራት አስፈላጊ በመሆናቸው አይወጡም፣ የፖሊሶቹ መምጣት ከእናንተ ተቃውሞ ጋር አይያያዝም ” የሚል መልስ ሰጥተዋል። የባለስልጣኖቹ መልስ ያላረካው ነዋሪ፣
ፖሊሶቹ ተቃውሞ ያሰሙትን አድነው አንድ በአንድ ሊይዙ ይችላሉ በሚል በንቃት እየተጠባበቀ ነው።
ሃምሌ 3 ቀን 2006 ዓም ከምሽት 12፡00 ጀምሮ የመብራት ሃይል ሰራተኞች በድብቅ አንድ ትልቅየጭነትመኪናክሬንበማዘጋጀትሊወስዱየነበሩትን ትራንስፎርመር ፣ የከተማውተወላጅየሆኑ
የጥበቃሃይሎችወዲያውኑለከተማውፖሊስ በመደወልትራንስፎርመሩን ከመነቀል አድነዋል፡፡
በሁለቱወረዳዎች 4 የከተማቀበሌዎችፌጥራ፣አለምከተማ፣ሬማ፣መራኛከተማንእናየደራከተማንጨምሮበድምሩበሁለቱወረዳከ40 በላይቀበሌዎችን ሊያገለግልየሚችለውን ከተተከለ 3 ዓመትእንኳን
ያልሞላውንትራንስፎርመር በመቋረጥ በምሽት ለመውሰድ የተደረገው ሙከራ ህዝቡ ባሳየው ከፍተኛ ተቃውሞ
ጉዳዩከተከሰተጀምሮየሰ/ሸዋዞንካድሬዎች/የዞኑምክትልአስተዳዳሪ፤የዞኑአስተዳደርጸጥታዘርፍኃላፊዎች፣የዞኑየፖሊስአዛዦችናልዩኃይልፖሊስንጨምሮየተለያዩአመራሮችን ወደ አካባቢው በመሄድ ህዝቡን
ለማሳመን ሲሞክሩሰንብተዋል።
እሁድሃምሌ 13 ቀን 2006 ዓ.ምበከተማውወደ 3000 የሚጠጋህዝብበተገኘበትስብሰባላይከፍተኛተቃውሞተነስቷል።
በከተማዋ የነገሰውን ውጥረት ለማርገብ በየቀኑ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፌደራል ጸጥታኃይል ሲላክመሰንበቱንእንዲሁምበህዝቡናበመንግስትየጸጥታኃይልመካከልየተኩስልውውጥተደርጎ ቁጥራቸው በውል ያልታወ የጸጥታኃይሎችና ነዋሪዎች ተጎድተዋል።