ገዢው ፓርቲ ከተለያዩ ክልሎች ያመጣቸውን ደጋፊዎች የአዲስ አበባ መታወቂያ እያደላቸው  ነው

ሐምሌ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመጪው ምርጫ የአዲስ አበባ ከተማን ለማሸነፍ ቆርጦ የነተሳው ኢህአዴግ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ነዋሪዎች ከትግራይ እና ከአማራ ክልሎች

ወደ አዲስ አበባ በማምጣት መታወቂያዎችን እያደለ መሆኑን የኢህአዴግ ምንጮች ገልጸዋል። ብዛት ያላቸው በተለይም ከትግራይ ክልል የመጡ የህወሃት አባላት የ13 ቱም ክፍለ ከተሞች የመኖሪያ

መታዎቂያዎች እየታደሉዋቸው ሲሆን፣ በምርጫው እለት በሁሉም ክፍለ ከተሞች እየዞሩ እንዲመርጡ ለማድረግ እቅድ ተዘርግቷል።

በክልሎችና በገጠር ያሉ ምርጫዎችን በተለያዩ መንገዶች እንደሚያሸንፍ እርግጠኛ የሆነው ኢህአዴግ፣ እሸነፋለሁ ብሎ በሚሰጋበት አዲስ አበባ በምርጫ 2002 እንዳደረገው በከፍተና ድምጽ

ለማሸነፍ አቅዷል። አሁን ባለው ግምገማ የአዲስ አበባ ህዝብ ኢህአዴግን እንደማይመርጥ የተረዳው ኢህአዴግ ፣ ደጋፊዎችን ከተለያዩ ክልሎች በማሰባሰብ መታወቂያ እያሰራ አንድ ሰው በ13 ክፍለ

ከተሞች ተዘዋውሮ እንዲመርጥ ለማድረግ ያዘጋጀው እቅዱ ካልተሳካ ሌሎች አማራጮችን ለመጠቀም ማሰቡም ተገልጿል።