ታህሳስ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪክ ማቻር ከተደበቁበት ቦታ ሆነው ለአለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን እንደገለጹት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ተቃዋሚዎቻቸውን ለመምታት የተጠቀሙበት ዘዴ ነው ብለዋል። የፕሬዚዳንቱ ጠባቂዎች እርስበርሳቸው መጋጨታቸውን የገለጹት የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ማቻር፣ ይሁን እንጅ የሳልቫኪር መንግስት አጋጣሚውን ተጠቅሞ ተቀናቃኞችን እያሰረ ነው ሲል አክለዋል።
በአገሪቱ ውስጥ የሚታየው ውጥረት በማየሉ አዲሲቷ አፍሪካዊት አገር በእርስበርስ የጎሳ ጦርነት ትታመሳለች ተብሎ ይፈራል። ሪክ ማቻር ያሉበት ቦታ በግልጽ ባይታወቅም፣ በእርሳቸው መኖሪያ ቤት አካባቢ ተኩስ እየተሰማ መሆኑን መገናኛ ብዙህን ዘግበዋል።
ከ15 ሺ በላይ የደቡብ ሱዳን ዜጎች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ ባንኪሙን ለፕሬዚዳንት ሳልቫኪር በመደወል እርቅ እንዲያወርዱ ጠይቀዋል።