ጥቅምት ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአለማቀፍ የወንጅል ፍርድ ቤት 50 አመታት የተፈረደባቸው ቻልረስ ቴለር በዛሬው እለት ለእንግሊዝ ፍርድ ቤት ተላልፈው የተሰጡ ሲሆን፣ በሩዋንዳ እንዲታሰሩ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተድርጎባቸዋል። ፕሬዞዳንቱ በሴራሊዮን ለተፈጸመው የጦር ወንጀል እጃቸው አለበት በሚል ዘሄግ የሚገኘው የወንጀል ፍርድ ቤት አምና የ50 አመታት እስር እንደፈረደባቸው ይታወቃል።