ነሃሴ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከኮሪያ ዘማች ቤተሰቦች ተውጣጥው ወደ ደቡብ ኮሪያ ለትምህርት ከተላኩት 59 ኢትዮጵያውያን መካከል 38ቱ ጥገኝነት ጠይቀዋል።
ኢትዮጵያውያኑ ለ8 ወራት የተሰጣቸውን ስልጠና ሊያጠናቅቁ የቀናት እድሜ ሲቀራቸው ነው ጥገኝነቱን የጠየቁት።
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ መበላሸት፣ ወጣቱ በአገሩ የሚሰራበት ሁኔታ ሊመቻች ባለመቻሉ ጥገኝነት ለመጠየቅ እንደተገደዱ ወጣት ሲሳይ ወልደገብረኤል ለኢሳት ገልጿል።