በከረዩና አርጎባ ብሄረሰቦች መካከል የተፈጠረው ችግር ተባብሶ ቀጥሎአል

ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ በሚገኙት በከረዩ ኦሮሞዎች እና አርጎባ ብሄረሰቦች መካከል በተፈጠረ ግጭት አርጎቦቹ   ከ200 በላይ የከረዩ ብሄረሰብ ከብቶችን በመዝረፍ ወስደዋል።  ባለፈው ማክሰኞ ግንቦት 27 ፣ 2005 ዓም ደግሞ ከረዩዎች ከ120 በላይ የአርጎቦችን ፍየል በመውሰዳቸው ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉ ታውቋል።

የፌደራል ፖሊስ አባላት ግጭቱን  እቆታጠራሉ በማለት ጣልቃ ቢገባም በአርጎቦቹ በኩል ተቀባይነት በለማግኘቱ ግጭቱ ሊበርድ እንዳልቻለ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በግጭቱ እስካሁን ምን ያክል ሰው እንደሞተ ለማወቅ አልተቻለም።

በኢትዮጵያ ውስጥ በብሄር ስም የሚደረጉ ግጭቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምታቱን ለማወቅ ተችሎአል።