ግንቦት ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢሳት ጋዜጠኞች በአዲስ አበባ፣ በደቡብ እና በኦሮሚያ ክልሎች በመዘዋወር የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማነጋገር እንደዘገቡት ዝቅተኛው የህብረተሰብ ክፍል በ ከፍተኛ ድህነት ውስጥ እየተሰቃየ እንደሚገኝ አመለክተዋል።
በጎዲዮ ዞን የሚገኙ አንድ በሽመና ስራ ላይ የሚሰሩ አዛውንት ” ኑሮ ከእጅ ወደ አፍ እንደሆነባቸው ተናግረው፣ ጊዜው አስቸጋሪ መሆኑን” ገልጸዋል። ( ጌዲዮ 00070)
ባለቤታቸውም እንዲሁ ” እሱ የፈጠረን ጌታ እስካሁን አልጣለንም” ብለዋል። ( ጌዲዮ 00070)
በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ ጎመን በመሸጥ የሚተዳዳሩ እናት በበኩላቸው፣ ኑሮ እንዴት ነው ተብለው ሲጠየቁ ” ከእግዚአብሄር ጋር ይበቃል” በማለት በምጸት መልሰዋል ( ኦሮሚያ አርሲ ዞን ሻሸመኔ 00103)
የ9 ልጆች አባት የሆኑት አንድ አባትም መሬታቸውን ለልጆቻቸው አከፋፍለው መጫረሳቸውን ተናግረው፣ የእርሳቸውም ሆነ የልጆቻቸው እታ ፋንታ ድህነት መሆኑን አክለዋል (133 )
አንድ ጎልማሳም እንዲሁ ስራ ፍለጋ ወደ ከተማ ቢመጣም መጨረሻው የጎዳና ተዳዳሪ መሆኑን ተናግሯል ። (67)
ብዙ ኢትዮጵያውያን ለመናገር ለመናገረ ቢፈሩም ገጽታቸውን አይቶ ስለኑሮአቸው መናገር እንደሚቻል ዘጋቢዎቻችን ገልጸዋል፡