መጋቢት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ባለፈው ወር በተካሄደው የኬንያ ምርጫ ፣ በስልጣን ላይ ያሉት ጠቅላይ ሚ/ር ራይላ ኦዲንጋ ምርጫው ተጭበርብሯል በማለት ያቀረቡትን ክስ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል።
ዳኛ ዊሊ ሙቲንጋ ምርጫው ትክክለኛ መሆኑን፣ አሁሩ ኬንያታም ምርጫውን ማሸነፋቸውን ገልጸዋል።
ተሸናፊው እጩ ፕሬዚዳንት ሚ/ር ኦዲንጋ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አከብራለሁ ብለዋል።
ዳኛው ሁሉም ኬንያውያን ለአገሪቱ ሰላምና ደህንነት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ መክረዋል።
አሸናፊው ፕሬዚዳንት ” በኬንያ የተካሄደው ምርጫ ዲሞክራሲ አሸናፊ ሆኖ የወጣበት ነው” በማለት መግለጻቸው ይታወሳል።